>

"የተፈታነው በህዝቡ ትግል ነው!" እስክንድር ነጋ

“የተፈታነው በህዝቡ ትግል ነው!”

DW

«ፖሊሶቹ ሳይሆኑ እንድታሰር ያደረጉት የክልሉ ባለስልጣናት ናቸው እየደወሉ መመሪያ ይሰጡ ነበር ያስለቀቀኝ የህዝብ ማዕበል ነው። በዚህ ትግል ህዝቡ አሸናፊ ሆኗል»

 እስክንድር ነጋ

ከሁለት ቀናት በፊት አማራ ክልል ቡሬ ዳሞት ወረዳ በቁጥጥር ስር ውለው  የነበሩት የቀድሞ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት  አቶ እስክንድር ነጋ ከአንድ ቀን እስር በኋላ በዋስ መፈታታቸውን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። አቶ እስክንድር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ በኃላ በአማራ ክልል በደጀን እና በባሕር ዳር ከተማ በርካታ ወጣቶች ወደ ታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ  በመሄድ መታሰራቸዉን መቃወማቸዉን የባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኃይለሚካኤል ተናግረዋል ።

ለቀድሞ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ  ፕሬዝዳንቱ እስክንድር ነጋ ከባህርዳር ዘጠነኛ  ፖሊስ ጣቢያ በታሰሩበት ወቅት በሶስት ሰው መታወቂያ ዋስትና እንዲፈቱ  ዋስ ከሆኗቸው መሀከል አንዱ የሆነው ወጣት ኃይለሚካኤል ለዶቼ ቬሌ ሲናገር የተያዘበትን ሁኔታ እንደማንኛውም ሰው በሶሻል ሚዲያ ላይ ሲወጣ ነው የሰማሁት ያለው ወጣቱ በአካል ያገኘሁት ከእስር ሲፈታ ነው ብሏል«እንደ ታሪክ አጋጣሚ ለዋስትና የሶስት ሰው የቀበሌ መታወቂያ ሲያስፈልግ አንዱ ዋስ የሆንኩት እኔ ነኝ» ብሏል። አቶ እስክንድርን ለመቀበል ነዋሪው በነቂስ ነበር የወጣው ያለው ኃይለሚካኤል  «የባህርዳር እና የደጀን ከተማ ነዋሪዎች ፖሊስ ጣቢያውን ጨናንቆት ነበር ከእስር ሲለቀቅም  ከፍተኛ የሆነ ህዝብ በአክብሮት ነው የተቀበለው» ብለዋል 

የቀድሞ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ  ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ በቡሬ ከተማ ከሶስት ሰዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል «በዚህ አጋጣሚ የደጀንን ወጣት ማመስገን እፈልጋው» ያሉት አቶ እስክንድር አያይዘውም «በዚህ ትግል መንግስት ሳይሆን ህዝብን ያሸነፈው ህዝብ ነው መንግስትን ያሸነፈው አዲስ ታሪክ ነው የተሰራው» ብለዋል።

በምን ምክንያት በህግ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለጠየቅናቸው ጥያቄ  አቶ እስክንድር ነጋ ሲመልሱ ምንም የተነገረኝ ነገር የለም ብለዋል « ፖሊሶቹ አይደሉም እንድታሰር የሚወስኑት የክልሉ ባለስልጣናት ናቸው እየደወሉ መመሪያ ሚሰጡት ባለስልጣናት ናቸው ፖሊሶቹ በሙያቸው ከማገልገል ውጪ በዚህ ጉዳይ ውስጥ የሉበትም » ሶስት ነን ነበር  የታሰርነው ያሉት አቶ እስክንድር ሶስቱም በቀበሌ መታወቂያ ዋስትና እንደወጡ ተናግረው «ያስለቀቀን የህዝብ ሀይል ነው »ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

Filed in: Amharic