>

ታሪክን ለባለታሪኩ፤ በተደረገበት ቦታ፤ በተፈጠመበት ቀን !! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

ታሪክን ለባለታሪኩ፤ በተደረገበት ቦታ፤ በተፈጠመበት ቀን !!

አሥራደው ከፈረንሳይ

በዚች አጭር ጽሁፌ ፤ የቀደምት የግሪክ ታሪኮች ( Classical mytology) ስለ ሔርኩል (Hercule)  በተጠቀሰች አጭርና ውስጠ ወይራ በሆነች ጥቅስ መንደርደር መረጥኩ :: 

« On ne se baigne jamais deux fois dans le même fleuve »

« በአንድ ወንዝ አንድ ጊዜ እንጂ፤ ሁለት ጊዜ አንጠመቅም  » ይላል

ይህን ጥቅስ እንድዋስ ያስገደደኝ፤ በኢትዮጵያ የዘንድሮውን የ127ኛ የአድዋ ድል በዓል አከባበር፤ በተመለከተ፤ የሚደረገውን የታሪክ ሸፍጥ፤ « ተረኞች ነን » ባዮቹን፤ ህዝብ አደብ ግዙ እንዲላቸው ለማሳሰብ ነው :: 

ታሪክ፤ በአድራጊውና በተደራጊው መሃል፤ በአንድ ወቅት፤ በተወሰነ ቦታና : በተወሰነ ጊዜ፤ በበጎ ወይም በጎጂ መልኩ፤ በአሸናፊና በተሸናፊ መሃል የሚደረግ ግብ ግብ ሲሆን፤ በመጨረሻም በመኖር ወይም ባለመኖር መሃል ይቋጫል:: 

የአድዋ ድል፤ በእምዬ ምኒልክና እተጌ ጣይቱ  አዝማችነት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ጀግንነት፤ በወራሪው የጣሊያን ፋሽስት ላይ፤ የተገኘ የአብሮነታችን ድል ከመሆኑም በላይ፤ የመላው አፍሪካ የጥቁር ህዝቦች ድል እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል :: 

የዘመኑ የዘርና የጎሣ ፖለቲከኞች፤ የአድዋን ድል ከኢትዮጵያዊነት ማማው ለማውረድ፤ ከመሬት ስበት በከፋ መልኩ ቁልቁል ወደታች በመጎተት፤ 

  • ያለ ድሉ ባለቤቶች፤ እምዬ ምንሊክ፤ እተጌ ጣይቱና ጀግኖቻችን፤
  • ያለ ቦታው፤ የአድዋ ድል አደባባይ  ፊት ለፊት፤
  • ያለ አብሮ ዘማች ታቦቱ፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን 
  • ያለ ሰንደቅ ዓላማችን፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙ፤  እንዲከበር ወስነዋል ::

አይምሯቸው፤ በዘርና በጎሣ ከታጠረ ግለሰቦች፤ ማህበረሰ’ባዊም ሆነ አገራዊ ዕሳቤ ስለማይመነጭ፤  አብሮነትን በሚያቀጭጭ፤ ክብርን በሚያጎድፍ፤ ታሪክን በሚከልስ ሁኔታ፤ እንዲከበር የወሰኑትን አጠፊዎች፤ ህዝብ በአንድነት እንዲጠየፋቸው አደራ እላለሁ ::

እግረ መንገዴንም፤ በእስር ለሚጉላሉት :

– ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁር፤ ጋሼ ታዲዎስ ታንቱ፤

– በአዲስ አበባ አካባቢና በአማራ ክልል፣ ለሚፈናቀሉ ወገኖቻችን፤ 

– የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታይ ለሆኑት ወገኖቻችን፤

– ለአርበኛ ዘመነ ካሴና፤ ለመላው የፋኖ አባላት ፍትህን እጠይቃለሁ ::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !! 


Filed in: Amharic