>

እንኳን ደስ ያለሽ! ለጋዜጠኛ መዐዛ መሐመድ

እንኳን ደስ ያለሽ!

       (ለጋዜጠኛ መዐዛ መሐመድ)

መዐዛ ሽታ ነው፤ 

መልካም ውሁድ ጠረን፣

በመላ አካል ሠርጾ፣

ሕዋሳት ቀስቅሶ፣

በፍጡራን ስሜት፣

እሚሞላ ሐሴት፤

አንቺም መዐዛ ነሽ፤

  በሰዎች ልቦች ውስጥ – ተስፋን እምትዘሪ፣

  የሕይወትን ትርጉም እምታስተምሪ፤

  ያፈራሽው ፍሬ አብቦ ጎምርቶ፣

  ለትውልድ ይተርፋል፣ ተራብቶ፣ ተባዝቶ፤

  በዚህች ከንቱ ዓለም እርካታ እሚገኘው፣

  ራስን በድሎም ለሌሎች ሲቆም ነው።

  አንቺ ተወጣሽው፣ ቤትሽንም ዘግተሽ፣

  የትውልዱን ዕዳ በጀግንነት ከፍለሽ!

  የከወንሽው ተግባር ማዕረግ አግኝቶ፣

  የምስኪን ዜጎች ድምጽ ከሩቁ ተሰምቶ፣

  ባለም ላይ አብበሽ፣ በርተሽ ስለታየሽ፣

   እንኳንም ደስ ያለሽ!!

ጌታቸው አበራ

የካቲት 2015 ዓ/ም

(ማርች 2023)

Filed in: Amharic