>

የሲሳይ እና የኤርሚያስ መንገድ (አብዮት ሰውነት)

የሲሳይ እና የኤርሚያስ መንገድ

አብዮት ሰውነት

ሲሳይ አጌና እና ኤርሚያስ በተለያየ ጎራ ሆነው አንድ ትህነግ ኢህዴግ ሲያገለግል ሌላው ሲቃወም ከርመው በመጨረሻ ለይ ሁለቱም በአንድ ጎራ ተሰልፈው አሜሪካ ላይ ተገናኙ አንድ በይቅርታ አንደኛው በትግል ታሪኩ ኢሳት ላይ ምርጥ ጥምረት በመፍጠር ትህነግ ኢህአዴግ ከ16 ጊዜ በላይ ከሳተላይት እንዲወርድ ሲታገላቸው ከረሙ። በመጨረሻም የአብይ መንግስ ለመምጣት ሲያኮበክብ የሲሳይ ትንተና አብይን እንደግፍ አይነት ሲሆን ዘግየት ብለው ሌሎቹ ቢቀላቀሉም በሰአቱ ከፍተኛ ተቃውም ይቀርብ ነበር።

ርእዪት በሀሳብ ልዩነት ብትቀጥልም ኤርሚያስ ከፍተኛ ድጋፋ ለአብይ መንግስት ይሰጥ ነበር። ሲሳይ ከጠቅላዩ ለውለታው በአደባባይ ምስጋና ሲቸረው ኤርሚያስ እውነትነቱ በማስረጃ ባይረጋገጥም ሀገር ውስጥ ገብቶ አብሮ ለመስራት ያቀረበው ሀሳብ ውድቅ እንደሆነበት ተወራ ። ኤርሚያስም ማርሽ ቀይሮ አብይን መንግስት መቃወም ዋና መርህ ሲያደርግ ሲሳይ ደግም ነጠላውን አደግድጎ ከአብይ ጎን ቆመ ።ጦርነቱ የራሱ ተጽኖ ኖሮት አብዛኛው ከአብይ ጎን ቆም ፓለቲካውን ሲተነትን ኤርሚያስ ደግም ወደ ቀደመው የትህነግ አማርኛ ክፍል ቃል አቀባይ ስራው ተመልሶ በተቃዋሚ ካብ አብይን ይቃወም ነበር። ኤርሚያስ እያንዳንዷን የአብይን ድክመት ለትህነግ በሚጠቅም መልኩ ሲተነትን ለምሳሌ ከጦርነቱ በፊት ጦርነቱ በትህነግ አሸናፊነት የመጠቃለሉ እድል ሰፊ እንደሆነ ሲያወራ ከርም  ጦርነቱ በአብይ አሸናፊ መሆኑ ሲረዳ ወደ ጀኖሳይድ ተገለበጠ ከዚያ የሰላም አቀንቃኝ ሆነ ሲሳይ ደግሞ ጭልጥ ብሎ አስተሳሰብም አነጋገሩም አተናተኑም የፋና እና የዋልታ ጋዜጠኞችን አስንቆ ቁጭ አለው።

አብይ መንግስት የሚሰራውን ስህተቶች እንዴት ትክክል እንደሆነ ለማስረዳት ይጥር ጀመር እግዚአብሔር ይስጣቸው አቶ ግዛው ባይኖሩ ኖሮ ኢኤም ኤስ ኢቲቪ 5 ይሆን ነበረ። ለምሳሌ ስብሀት መፈታት የአዲስ አበባ ሰንደቃላማ እና መዝሙር የትህነግ ስምምነት የቤተክርስቲያን ውዝግብ ለጌታቸው ንግግር የሰጠው ልበ ስሱነት ጌታቸውን የማያቀው አዲስ ጋዜጠኛ ይመስል ነበር።  በአሁኑ ሰአት ሁለቱም ቃል አቀባይ እንጂ ጋዜጠኛ መስፈርት አያሟሉም።

 ኤርሚያስ ቴድሮስ እስታሊን በተለያየ ማሊያ ለአንድ ብሔራዊ ብድን የሚጫወቱ ሲሆን በተቃራኒው ስዪም ሲሳይ አንዳንድ የአማራ አክቲቪስት ነን ባዪች ስማቸውን መጥራት ስላልፈለኩ ነው በተለያየ ማሊያ ለአንድ ቢሔራዊ ብድን የሚጫወቱ ሲሆኑ አላማቸው ለህሊናቸው የቆሙ ጋዜጠኛ እና አክቲቪስቶችን ሀሳብ ለመበረዝ ለማሸማቀቅ ዋና አላማ አድርገው ለሆዳቸው የሚጫወቱ ናቸው።እነኝህ እውነት ይነግሩኛል እውነት ይተነትናሉ ብለህ አጠብቅ የነሱ እውነት የሚነሳው እውነት ከምትተነተንበት መርህ ሳይሆን ቀለብ ከሚሰፍሩላቸው መነጽር ብቻ ነው። ያ ደግም የነሱ እውነት እንጂ የጋራ እውነት አይደለም። ግን ስንቶቹ ሳናውቃቸው ከፍ አደረግናቸው። ስንቶቹን ጀግና ጀግና እያልን አነገስናቸው።  ዶር አብይ ለዚህ ሳላመሰግንህ ማለፍ አልፈልግም። አንተ ራቁታቸውን ባታስቀራቸው ኖሮ እንዲሁ እንዳታለሉን ይኖሩ ነበር። ቸር እንሰንብት 

Email: abiyotsew@gmail.com

Filed in: Amharic