>

ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ ልዩ ወቅታዊ መግለጫ

ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ ልዩ ወቅታዊ መግለጫ

የዘር ማጥፋት ወንጀልን ሕዝብ ላይ ዘምቶ በመግለጫ ማድበስበስ አይቻልም

(ግንቦት 27/2015)

ሃገር ወዳድ ወገናችን ሆይ! ባለፈው 5 ዓመት በሕዝብ ድጋፍ የሃገሪቱ መሪ የሆነው አብይ አህመድ አምነህ ሥልጣን ከሰጠኸው በኋላ ሃገርህን እየበታተናት እንደሆነ አንተን መንገር አያስፈልገንም። በአማራ ወገንህ ላይ ብቻ የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ጧትና ማታ እያየኸው ነው። ሥርዓቱን የኦሮሞ ጥንፈኛ ብሄርተኞች ሙሉ በሙሉ ከመቆጣጠራቸውም በላይ በለፋህባት ከተማ ውስጥ እነሱ ብቻ እንዲኖሩባት ቤትህን በላይህ ላይ እያፈረሱ ሜዳ ላይ ወድቀህ ለረሃብና ለበሽታ እንድትጋለጥ እያደረጉ ነው። በአጭሩ ዛሬ በሃገርህ ባይታወር ሆነሃል።

ሃገር ወዳድ ወገናችን ሆይ! ይህ አብይ አህመድ የሚመራው ፋሽስታዊ ሥርዓት ሁሉን የኔነው እያለ አዲስ ካርታ አውጥቶ ከማሰራጨቱም በላይ በቤተእምነቶችህም ውስጥ ጣልቃ በመግባት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘርን ባገናዘበ መልክ ለሁለት እየሰነጠቃት ይገኛል። ቀደም ሲል የሙስሊሙን ተቋም መጅሊስን በፅንፈኛ የኦሮሞ ብሄርተኞች ሥር እንዳዋለው ይታወሰል።

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ሰሞኑን በተከታታይ የአብይ አህመድ አገዛዝ በሰላማዊ የደብረ ኤልያስ ገዳማውያን እና ጥንታዊ ገዳማቱ ላይ ያደረሰውን ፍጅትና ጉዳት ሲያጋልጥ መቆየቱና በተለይም በሥላሴ ገዳም ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዝ ጥቃት አድርሶ የጦር ወንጀል መፈጸሙን አጋልጠናል፡፡ የአብይ አህመድ ሠራዊት ሰላማዊ ገዳማውያን በሚያሳድጓቸው ወላጅ አልባ ህጻናት፣ ጸበልተኞችና ቤተ እምነታችን ሲነካ በዝምታ አናይም ባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ ርህራሄ የለሽ ድርጊቱ የጦር ወንጀል መሆኑን ሲረዳ የፈጃቸውን  መነኮሳትና ወላጅ አልባ ሕጻናቱን አስከሬን ጭምር ድብቆ በጅምላ መቃብር ከመቅበሩም በላይ  የገዳሙን ንብረት ከዘረፈ በኋላ የፋሺስትነት ተግባሩን ለማድበስበስ በትናንትናው ዕለት የተለመደ የቅጥፋት መግለጫ የኦህዴድ አገዛዝ መፈንጫ በሆነው የጸጥታና የደህንነት የጋራ ግበረ ኃይል በኩል አውጥቷል፡፡ መርካቶ ላይ በጠራራ ፀሐይ ተዘጋጅቶ ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ለሰላማዊና ሕጋዊ መስጊድ አይፍረስብን ጥያቄ ጥይት ያዘነብ ኃይል አማራ ክልል ጎጃም ደበረ ኤልያስ ላይ በጭካኔ ስለ ጨፈጨፋቸው ንጹሃን እውነት ይናገራል ብሎ የሚጠብቅ ባይኖርም መግለጫው በአጭሩ ራሱን ከፈጸመው የጦር ወንጀል ለመከላከልና በበሬ ወለደ አጅቦ ሌሎችን በተልይም ሕዝባዊ ግንባሩንና መሪውን እስክንድር ነጋን ለመግደል ተጨማሪ ጦር አዝምቶ አሰሳ እየደረገ እንድሚገኝ ለዚህም ሕጋዊ ቀለም ለመቀባት ሲውተረተር አይተናል፡፡

እስክንድር ነጋ ገና ከጠዋቱ የዘረኞቹን ሁሉን ጨፍላቂነት በመረዳት 

አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ናት በማለቱ ጦርነት ውስጥ እንገባለን ያለው ፋሺስቱ አብይ አህመድ ዛሬ ሥልጣኑንን ተገን አድርጎ የፈጸመውን የጦር ወንጀል ለመሸፈን አስር ምክንያት ቢደረድር ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ በጎጃም ይሁን ጎንደር፣ ሸዋ ይሁን ወሎ በሁሉም አቅጣቻ በአማራ ሕዝብ ላይ አብይ አህመድ የከፈተው ሕገ ወጥ ጦርነት ዋና ዓላማው አማራን ትጥቅ ማስፈታት፣ ማንበርከክ እና መጨፍጨፍ መሆንን ከሸዋ እስከ ደብረ ኤልያስ በመከላከያ ስም ያሰማራው የኦህዴድ ጦር በግልጽ አረመኔነቱን አስመስክሯል፡፡ ፋሽስቱ አብይ አህመድ በመግለጫ ጋጋታ በንጹሃን ደም የተዘፈቀውን እጁን መቼም ማጽዳት አይችልም። 

በጎጃም ከ600 ዓመት በላይ ባስቆጠረው የደብረ ኤልያስ ገዳም ላይ የተደረገው የአብይ አህመድ ሠራዊት ወረራና በመነኮሳትና በህጻናት አዳሪ ተማሪዎች እንዲሁም ለፀበል በሄዱ ምእመናን ላይ የተፈፀመው ግድያና በገዳሙ ላይ ያደረሰው ውድመት እንዲሁም ሰሞኑን በአዲስ አበባ በነሽመልሥ አብዲሳ ትእዛዝ ከ20 በላይ መስጊዶች መፍረሳቸው የሚያመላክተው ሁለቱ ታላላቅ እምነቶች በሥርዓቱ እንዲፈርሱ የተፈረደባቸው መሆኑን ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሁለት አርቦች በታላቁ የአንዋር መስጊድና በሌሎችም መስጊዶች በዚህ አገዛዝ የተፈጸሙት ግድያዎች ተጨማሪ ማስረጃ ናቸው። ሥርዓቱ በማንነትህ፣ በንብረትህ እና ከሁሉም በላይ በእምነትህ ላይ የመጣ ለመሆኑ አንተን ማሳመን የሚያስፈልገን አይመስለንም።

ውድ የአማራ ሕዝብ ሆይ! ዛሬ ህልውናህን ለማረጋገጥ ቆርጠህ በተነሳህበትና እንዲሁም  በተቀናጀ መልክ እንድትታገል ለማድረግ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ሃላፊነቱን እየተወጣ ባለበት ሰዓት ፋሽስታዊው የአብይ አህመድ መንግሥት አጋጣሚውን ተጠቅሞ አንተን ለማጥፋት ያለ የለለውን ሃይሉን የመከላከያ ዩኒፎርም አልብሶ ከዘመተብህ ዋል አደር ብሏል። ያወጣው መግለጫ ሥርዓቱ ትልቅ ጭንቅ ላይ መሆኑን የሚያንፀባርቅ ከመሆን አልፎ መሬት ላይ የወረደ አንድም ሃቅ አያሳይም። ሆኖም የመግለጫው ዋና ዓላማ እና በይበልጥ ትኩረት የሰጠው ተስፋ የተጣለበትን ድርጅት የአማራ ሕዝባዊ ግንባርን ለመበታተን እና በአመራሩ ላይ ጉዳት ለማድረስ በፋሽስቱ አብይ አህመድ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው። በመግለጫው ላይ ከአመራሮቹ ውስጥ የእስክንድር ነጋን ስም ብቻ ቢጠቆምም  ዋናው የአብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ ዓላማው አንተን መሪዎች በማሳጣት የህልውና ትግልህን ለማኮላሸትና ከምድር ገጽ እንድትጠፋ ለማድረግ ስለሆነ በየአካባቢህ የሚንቀሳቀሰውን ገዳይ የአብይ አህመድ ሠራዊት  መንገዱን እየዘጋህ የመከላከል እርምጃ እንድትወስድበትና ወደመጣበት እንዳይመለስ እንድታደርገው ወይም በዛው እንድታስቀረው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ጥሪ ያቀርብልሃል።

ድል ለአማራ ሕዝብ!

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር

Filed in: Amharic