>

ለመኖር መዋጋት! (ጌጥዬ ያለው)

ለመኖር መዋጋት! 

ጌጥዬ ያለው

የኦሮሞ የወረራ አገዛዝ ከመጣ ጀምሮ የቀጠለው የአማራ ትግል በጎ የዕድገት ደረጃዎችን እያሳየ ነው። ስርዓቱ በማጭበርበር እምዬ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በገባባቸው የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ገደማ ያሳየው ስሁት ድጋፍ ወደ ሙሉ ተቃውሞ የተቀየረው ኦሮሙማ አማራን ለመበቀል ከነበረው ጉምጃት የተነሳ ራሱን በፍጥነት በማጋለጡ ነበር። 
በየመገናኛ ብዙሃኑ እና የስብሰባ አዳራሾች የተጀመረው ተቃውሞ በብርሃን ፍጥነት ወደ አደባባይ የተቃውሞ ሰልፎች ብሎም መጠነኛ ሕዝባዊ እምቢተኝነቶች አድጓል። ካለፈው ወር ጀምሮ ደግሞ ወደ ሕዝባዊ ውጊያ ተሸጋግሯል። በሸዋ፣ በቤተ አማራ (ወሎ)፣ በጎንደር እንዲሁም ሰሞኑን በጎጃም እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ውጊያ ነው። በጠላት በኩል ኦሮሞ መር የሆነው መከላከያ ሰራዊት የተሰለፈበት ሲሆን፤ ከፌዴራል እስከ ሰፈር ያሉ የአገዛዙ አንጋቾች እየተሳተፉበት ነው። 
በአማራ በኩል እየተዋጋ ያለው ፋኖን አስቀድሞ ራሱ የአማራ ሕዝብ ነው። ውጊያው አማራ ራሱን ከጅምላ ፍጅትና ወረራ ለመከላከል የሚያደርገው ቅዱስ ጦርነት ነው። ጠላት የኦሮሞ ወራሪ ሰራዊት ተኩሱን ሲያቆም ይቆማል፤ ሲተኩስ ይቀጥላል። የመከላከል ውጊያ እንዲህ ነው። የጦርነቱ ማብሪያና መጥፊያ በወራሪዎች እጅ በመሆኑ ብሎም በቂ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ባለማግኘቱ የሚፈሰው ደም የሃምሌ ካፊያ መስሎ ከመጤፍ አልተቆጠረም። 
በመሃል ጎጃም ገዳም በሞርታር ጋይቶ፣ መነኩሳት፣ የአብነት ተማሪዎች እና ሌሎች ገዳማውያን ሰውነታቸውን እንደ ጎመን በሚቀረድድ፣ እንደሽንኩርት በሚከትፍ፥ ስሙንም ሆነ ድምፁን በማያውቁት ከባድ የጦር መሳሪያ ጋይተው ቅዱስ ሲኖዶስ በአርምሞ አልፎታል። አንዳች ‘ተናግሯል ‘ወይም ‘አድርጓል’ እንኳን ቢባል በአንድ የደወል ጥሪ ትዕዛዙን የሚፈፅምለትን ምዕመን ራሱን ከጥፋት እንዲከላከል አልጠራም። ይህ ከታሪካችን ውጭ ነው። 
. . . አቡነ ሚካኤል ቅድሥት ቤተ ክርስቲያንን በፋሽስት ጣልያን ላለማስደፈር ብሎም ሀገራቸውን ላለማስወረር ጎሬ ላይ በጣልያን መትረየስ ተደብድበው ሰማዕት ሆኑ። በተመሳሳይ አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ ሰማዕትነትን በክብር ተጎነጩ። በአባቶቻችን ሰማዕትነት ንፅህት፣ ቅድሥት ቤተ ክርስቲያን ከእነክብሯ ቀጠለች። ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴያቸው ተፈሪ መኮንን (በኋላ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ) ይቺን ቤተ ክርስቲያን ከጥቃት ለመታደግ ከወንድማቸው ጋር ተዋግተዋል። ተሳክቶላቸዋልም። አጼ ቴዎድሮስ ለሃይማኖታቸው ብሎም ለሀገራቸው ህልውና ከቱርክ፣ ግብፅና ሱዳን ወራሪዎች ጋር ተፋልመዋል። በጎራዴ ተከታክተው ድል አድርገዋል። “ጣልያንን አባረርህ” ብለው አሉላ አባ ነጋን በማሰር፣ ከእንግሊዝ ጋር ተባብረው ቴዎድሮስን በመውጋት በባንዳነት ታሪክ የመዘገባቸው አጼ ዮሀንስ እንኳን አንገታቸውን የተቀሉት ከሀገራቸውም በላይ የሃይማኖታቸው መነካት ሰቅጥጧቸው ነበር። 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አጼ  አጼ ገላውዲዎስ፣ አጼ ልብነ ድንግል፣ ንጉሥ አንበሳ ውድም ወዘተ ከቤተ መንግሥቱም ሆነ ከቤተ ክህነቱ ጎራ በየዘመናቸው ዋጋ ከፍለው ከእኛ አድርሰዋታል. . . 
ታሪካችን ይህ ነው። ዛሬስ? በቤተ መንግሥቱ በኩል ስሙ የመንግሥት ቢሆንም ግብሩ የውጭ ወራሪ መሆኑን ቀድመን ተረድተናል። በተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት አቤ ጉበኛ “ጥቁር አውሮፓውያን” ሲል የገለፃቸው እነኝህን ነበር። እርሱ የጥፋታቸው ንድፍ ላይ ደረሰ፤ እኛ አፈፃፀሙ ላይ ደረስን። ስለዚህ የቤተ መንግሥቱን ጉዳይ ተረድተነዋል። ግርታ የለብንም። ቤተ ክህነቱስ? 

መንፈሳዊ ብአዴን-ዎች


ወያኔ በለስ ቀንቶት አራት ኪሎ ሲገባ፤ ኦነግ-ም የመንግሥቱ ተካፋይ ብሎም የድርሻውን ገንጣይ ለመሆን ቀርቦ ነበር። በዚህ ወቅት በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በአሰቦት ገዳም ወዘተ አማራን በጅምላ ማረድ ጀመረ። በየቦታው የአማራ እልቂት ተቀጣጠለ። እልቂቱን ለማስቆም ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅትን መሰረቱ። ወያኔ በበኩሉ መአሕድ-ን ለማራከስ ከአማራ ያልተወለዱ ሰዎችን አሰባስቦ በአማራ ስም ድርጅት መሰረተ። ከወያኔ ጋር ባላቸው ወዳጅነት ቀደም ብሎ ከኢሕአፓ ተገንጥለው  የወጡ የአማራ ጠላቶች አቋቁመውት የነበረውን ኢሕዴን በቀጥታ ወደ ብአዴን-ነት ቀየረው። ኢሕዴን~ብአዴን~አዴፓ~የአማራ ብልፅግና እያለ ይኸው የአማራ ጨፍጫፊዎች የባሕር ዳር ወኪል ሆኖ ቀጥሏል። ይህ ድርጅት ትግሬ ወንበር ላይ ሲሆን ትግሬ ነው። ኦሮሞ ሥልጣን ላይ ሲወጣም ኦሮሞ ነው። ነገ ሲዳማ ቤተ መንግሥት ቢገባ ሲዳማ ይሆናል። አማራ ሆኖ አያውቅም። ይህ በቤተ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን በቤተ ክህነቱ ያለ እከክ ሆኗል። 
ግርማዊ ቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሤ ኢትዮጵያን ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ወቀሳ ነፃ ለማድረግ “የባርያ ነፃ አውጭ ድርጅት”ን አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ ሳሉ ጥቂት የባርያ ልጆች በክህደት ተነስተው መንግሥታቸውን ገለበጡ። 1966 ዓ.ም. ከ3000 ዓመታት በላይ የዘለቀው የሰሎሞናዊ ስርዎ መንግሥት ተቋረጠ። አማራ ከፖለቲካ ሥልጣን ተገለለ። ራሳቸውን ‘ደርግ’ ብለው የሚጠሩ ወታደሮች ቅድሥት ቤተ ክርስቲያንን በከስክስ ጫማቸው ረገጧት። ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በመፃረር ደርግ ጣልቃ ገብቶ የወቅቱን ፓትርያርክ ቅዱስ ወ ሰማዕት አቡነ ቴዎፍሎስን ከመንበራቸው አንስቶ እስር ቤት ከተታቸው። ታላቁ አባት “ይህ መተተኛ ቄስ ብን ብለው ይጠፋሉ” በሚል ሰባት ቀንና ሌሊት አልጋለይ ተኝተው ሁለቱም እጅና እግሮቻቸው ከአልጋው እግር ጋር በገመድ ታስረው መንቀሳቀስ ሳይችሉ በአንድ ክፍል ውስጥ ብቻቸውን ሰነበቱ። ከዚያ በኋላም በምልጃ ገመዱ ተፈቶላቸው ከፍተኛ የፖለቲካ እስረኞች ወደታሰሩበት ክፍል ተዘዋወሩ። እንቅልፍ ሲጥላቸው ከማቋረጣቸው በቀር ሲፀልዩ ውለው እያደሩ ከሁለት ዓመታት በላይ ታሰሩ። በዚህ ስቃያቸው ያልረካው ደርግ 60 ምሁራንን ሲረሽን በአሰቃቂ ሁኔታ አብሮ ረሸናቸው። 
ገና ከመንበር እንዳነሳቸው በመንበራቸው አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተባሉ ካኪ ለባሽ ፓትርያርክ ሹሞ ነበር። አዲሱ ፓትርያርክ “አብዮቱ፣ ኢሰፓ፣ ኢማሌድህ፣ አምራች፣ ሰፈራ፣ ፊውዳል፣ መሬት ለአራሹ፣ ነጭ ሽብር” ገለመሌ እያሉ ቤተ ክርስቲያኗን በደርግ አስተምህሮ መምራት ቀጠሉ። ከእርሳቸው በተጨማሪ ደርግ “የተሀድሶ ጉባዔ” የተባለ የቀሳውስት ማህበር አቋቋመ። ጉባዔው በቤተ ክህነቱ ውስጥ የደርግ ፅህፈት ቤት ነበር ማለት ይቻላል። አገዛዙ “ፊውዳል” እያለ አማራን ሲረሽን፣ “የዘውድ ርዝራዥ” እያለ ምሁራንን ሲረሽን፤ ይህ ጉባዔ አብዮታዊ ርምጃውን ደግፎ መግለጫ ያወጣ ነበር።
ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት በኋላ የቀጠሉት ፓትርያርክ ብፅዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር ለመመለስ ቢሞክሩም ከደርግ የከፋው የአልባንያ ደቀ መዝሙር ወያኔ ደረሰባቸው። ሀገር ጥለው ተሰደዱ። በርግጥ ቅድሥት ቤተ ክርስቲያን አለም ዓቀፋዊት ነችና መንበር ቀየሩ እንጂ ተሰደዱ ማለት አሳሳች ሊሆን ይችላል። የሆነው ሆኖ ቅዱሥ ሲኖዶስ እንደ ባቄላ ፍሬ ከሁለት ተፈረከተ። በአዲስ አበባው መንበር ላይ አቡነ ጳውሎስ የተባሉ ትግሬ ተፈልገው በወያኔ ተሾሙ። ቤተ ክርስቲያኗንም “ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግሥት. . .” እያሉ መሯት። የዚህ ሁሉ ጥፋት መሀንዲስ መለስ ዜናዊ ሲሞት የተቀጣጠሩ ይመስል እሳቸውም ወደቁ። ከስርዓቱ ተጠቃሚዎች በስተቀር ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ “የእግዚአብሄር ቁጣ ታዬ፤ ከአለቃቸው ጋር ፓትርያርኩም ተቀዘፉ” አለ። ከዚህም በኋላ ፓትርያርክ ለመሆን በትግርኛ መንተባተብ እንደ መስፈርት ተቆጥሮ ዛሬም ቀጥሏል። 
“ትግሬ ተጨፈጨፈ” ብለው መንታ መንታ እንባ ሲያነቡ የከረሙት ፓትርያርክ ጎጃም ላይ ገዳም 3 ሞርታር በታጠቀ አራት ብርጌድ የመከላከያ ሰራዊት ሲጋይ ዝም አሉ። ምክንያቱም ይህ የተፈፀመው በአማሮች ላይ ነው። ከጭፍጨፋው የተረፉ መነኩሳት ያለቀሱት በትግርኛ አይደለም!  ማተብ ሽፋናዊ ማንነት ሆነ! 
የሲኖዶሱ ዝምታ ከዚህ ታሪካዊ ዑደት የተዋረሰ ነው ብየ አምናለሁ። 


 በወሽመጥ የገባ


(ሲኖዶሱን መተቸት እንደ አንጓጣጭነት፤ ግፋ ሲልም መንፈስ ቅዱሥን እንደ ማሄስ ተደርጎ ሲታሰብ አያለሁ። እንደ አማኝ መተቸት የማይቻለው ንፅህት እና ቅድሥት የሆነቺውን ቤተ ክርስቲያንን እንጂ አስተዳድሩን ማለትም ቤተ ክህነቱን መውቀስ ክፋቱ አይታየኝም። ሲኖዶሱ በመንፈስ ቅዱሥ መመራት ሲገባው በወሮ በላ ፖለቲከኞች ከተመራ ከመተቸትም በላይ በወንጀል መጠየቅ ይኖርበታል። ፓትርያርክ በፀረ ኢትዮጵያ ተገንጣይ ብሄርተኞች ሲሾምና ሲሻር እያዩ ዝም ማለት በራሱ ነውር ነውታሪካችንም ይህንን ያስረግጣል፦ አቤ ጉበኛ በድፍን ጎጃምና ጎንደር ስመ ጥር የነበሩት መርጌታ ገሠሠ ዘ ይስማላ ያጨበጨቡለት ጎበዝ የአብነት ትምህርት አዋቂ ነበር። የቤተ ክህነቱን ጉድፎች ግን በመፅሀፎቹ ሲተች ኖሯል። አጼ ቴዎድሮስ ራሳቸውን “እግዚአብሄር ከትቢያ ያነሳኝ የመድሃኒዓለም ባርያ” ብለው የጠሩ፤ ስለ ሃይማኖታቸው ከውጭ ወራሪ ጋር የተዋደቁ አማኝ ናቸው። የቤተ ክህነቱን የአስተዳድር እድፍ ግን ከማነወርም አልፈው በወቅቱ የነበረውን የቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት አንድነት ተጠቅመው ራሳቸው እስከ ማጠብ ደርሰዋል)

ስለ ቅድሥት ቤተ ክርስቲያን ከሲኖዶሱ ይልቅ አዲስ አበባ የሚገኙት የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን የኦሮሞ የወረራ አገዛዝን ሲሞግቱ ተደምጠዋል። በአማርኛ ቋንቋ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “የእናንተ መንግሥት ስለ አረንጓዴ አሻራ ይናገራል። ነገር ግን በአረንጓዴ አሻራ ቀዳሚዋ ቤተ ክርስቲያን ናት። ዙሪያዋን በዛፍ ሸፍና ነው ምትኖር” ነበር ያሉት። እሳቸው ይህን ሲሉ የእኛ ጳጳስ በበኩላቸው አማራን አግለለው ወያኔ እና ኦነጋውያን ደቡብ አፍሪካ ላይ የዶለቱትን በአውደ ምህረት ሲያስተጋቡ ነበር። ሬድዋን ሁሴን አዲስ አበባ ላይ የሰጠውን መግለጫ እሳቸው ባሕር ዳር ላይ ለተሰበሰበ ምዕመናቸው ደገሙለት።  ይህ አይነቱ ፖለቲካዊ ርክሰት ቤተ ክርስቲያኗን የእስክንድርያ ጳጳሳት ይመሩ በነበረበት ጊዜ እንኳን በዚህ መጠን ለመፈጠሩ ርግጠኛ አይደለሁም። 
አንድን የእባብ እንቁላል፤ ከእንቁላሎቿ ጋር ጨምረን ለዶሯችን ብናስታቅፋት መፈልፈሉ አይቀርም። የምናገኘው ግን ጫጩት ሳይሆን ያው እባብ ነው። ‘ብአዴን ለምን አማራ አልሆነም?’ ካልን መለሱ እንቁላሉ አማራ ስላልሆነ የሚል ነው። የሲኖዶሱም ከዚህ የተለየ አይደለም። ለዚህ ነው መንፈሳዊ ብአዴን የምለው። 
ብአዴን የአማራን ሕዝብ እጁን ይዞ ያስጨፈጭፋል። “በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ይሠራል፤ አይሳሳትም” ያልነው ሲኖዶስም ራሱን እንዳይከላከል እየገዘተ ሕዝበ ክርስቲያኑን ያስጨፈጭፋል። “ጥቁር ልበሱ፣ ምህላ አድርጉ፣ ሰልፍ ውጡ” ሲለን ሰንብቶ በደላችንን በአደባባይ ተቃውሞ ለዓለም እንዳናሳይ ከጨፍጫፊዎቻችን ጋር በጓዳ ተነጋግሮ “እቤታችሁ ተቀመጡ፣ ነጭ ልበሱ” ይለናል። የኦሮሞ የወረራ አገዛዝ ለቤተ ክርስቲያኗ ያሰናዳው ሁለንተናዊ ጅምላ ጭፍጨፋም ተጠናክሮ ይቀጥላል። 
“ወለጋ ላይ ምዕመናን ተገደሉ፣ ወራቤ ላይ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ” ስንባል ድርጊቱን ለማስቆም አንዳች ባለማድረጋችን ጎጃም ላይ ገዳም በጦር ሰራዊት እስከ መደብደብ ተደረሰ። 

የሥላሤው ጭፍጨፋ 


በምስራቅ ጎጃም፤ ደብረ ኤልያስ ወረዳ የአባይ ዥረት በረሃማ ስፍራ ውስጥ የሚገኘው የብሄረ ብፁዓን አጼ መልክዓ ሥላሤ አንድነት ገዳም ከሀሙስ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አመሻሽ ጀምሮ እስከ ሰኞ ግንቦት 23 ቀን ድረስ በኦሮሙማው መከላከያ ሰራዊት ተጨፍጭፏል። ከዚህ ቀን አራት ወራት ቀደም ብሎ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳድር አዘመታቸው የተባሉ የአገዛዙ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው 11 ጸበልተኞችንና ሌሎች ገዳማውያንን መግደላቸውን እንዲሁም 17ቱን ማቁሰላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በሪፖርቱ ገልጿል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ መሆኑን ገዳማውያኑ ገልፀዋል። ቁስለኞች ህክምና የተከለከሉ ሲሆን መንፈሳዊ ፈውስን ግን ከእግዚአብሄር እጅ ሊነጥቃቸው አልቻለም። ከዚህ በተጨማሪ ምዕመናን ወደ ገዳሙ እንዳይገቡ መንገዱን ዘግቶ በታጣቂዎች መጠበቅ ከጀመረ አራት ወራት ተቆጥረዋል። በዚህም ገዳሙ በግቢው ውስጥ አርሶና ቆፍሮ ያመረተውን አትክልትና ፍራፍሬ ለገበያ እንዳያቀርብ ተከልክሏል። 
ስለዚህ የሰሞኑ ጭፍጨፋ በድንገት የተፈጠረ ሳይሆን ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ ነው። አገዛዙ ለወራት ሲያደርግ የቆየውን ወታደራዊ ዝግጅት ነው ገቢራዊ ያደረገው። በዚህም የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችን፣ ስናይፐሮችን፣ መትረየሶችን፣ ዲሽቃዎችን፣ ሞርታሮችን፣ ብረት ለበስ ባለተሽከርካሪ ከባድ ጠመንጃዎችን ጨምሮ በርካታ ቦምቦችን ታጥቆ ዘምቷል። ስለሌለው እንጂ ኒውክሊየርም ቢሆን ከማዝነብ አይመለስም ነበር። 
በዚህም የንፁሃን ንፁሃን የሆኑ መነኩሳት፣ ዕድሜያቸው ከ8-13 ዓመት የሆኑ ሕፃናት የአብነት ተማሪዎችና ሌሎች ገዳማውያንን በግፍ ጨፍጭፏል።ከተጨፈጨፉት መነኩሳት መካከል ሴቶቹ ብቻ ከ200 በላይ እንደሆኑ ይነገራል። ከ80 ሕፃናት መካከል ሶስቱ ብቻ በሕይዎት መገኜታቸው ተዓምር ነው። ይህ በለየለት የጦርነት ዘመን ራስ ይማም ጎንደር፤ ቸንከር ተክለ ሃይማኖትን ሲወጋ ከጨፈጨፋቸው ሕፃናት ታሪክ ጋር የሚመሳሰል ነው። በወቅቱ በደብሩ ከነበሩ የአብነት ተማሪዎች መካከል የሾላ ዛፍ ላይ ተንጠላጥለው በየተረፉት አጼ ቴዎድሮስ ማለትም የያንጊዜው ልጅ ካሣ ኃይሉ ብቻ ነበሩ። 
የኦሮሙማ መከላከያ በሥላሤ ገዳም ላይ የፈፀመው አጠቃላይ ጅምላ ጭፍጨፋ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚያስቀጣ የጦር ወንጀል ነው።  የዘር ማፅዳት ነው። ፋሽት ጣልያን በ5 ዓመቱ ወረራ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ ከፈፀመው ጭፍጨፍ የሚስተካከል ነው። እንዳውም ጣልያን ውድ ከሆኑ ንዋየ ቅዱሣት በቀር ጥቃቅን የገዳሙን ንብረቶች አልዘረፈም። ወራሪው የኦሮሞ አገዛዝ በግቢው ውስጥ የተረፈረፉ የራሱን ሬሳዎች እንኳን ቅጠል ከማልበሱ በፊት ከተሰጣ ኮቸሮ ጀምሮ የገዳማውያኑን የቀለብ እህል በካሚዮን ጭኖ ወስዷል። ከሞርታር ያመለጡ ላምና በሬዎችን እያረደ በልቷል። ከዕለት ሆዱ የተረፈውንም ተሸክሞ ሄዷል። በተመሳሳይ ንዋየ ቅዱሳትን ዘርፏል። 
ይህንን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም “ሃይማኖታችንን አናስነካም”  ያሉ ነበልባል ፋኖዎችና የአካባቢው ገበሬዎች ተፋልመውታል። በተለይም በመጀመሪያዎቹ ሁለት የውጊያ ቀናት ለየብቻ ያስገባቸው ሁለት ብርጌድ የሰራዊት አባላቱ ተደምስሰዋል። ገዳሙን መቆጣጠር የቻለውም በድንገት ተጠራርተው ለመከላከል የገቡ ፋኖዎችና ገበሬዎች ጥይት በመጨረሳቸው ማፈግፈጋቸውን ተከትሎ ነው። 
ኢትዮጵያ ተቀብላ የፈረመችበትን ዓለም አቀፍ የጦር ሕግ በመጣስ የፈፀመውን የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸፈን እየተጠቀመበት ያለው “በገዳሙ ሽፍታ ተደብቋል” የሚል ነው። 
ጉዳዩ ሽፍታን የማጣፋት ቢሆን ኖሮ የአካባቢው ፖሊስ ከበቂ በላይ ነበር። በአንድ ጠባብ ግቢ ውስጥ ሞርታር እስከ መተኮስ የሚያደክም አልነበረም። አስለቃሽ ጭስ ተኩሶ ገዳሙ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ እያስነጠሳቸው እንዲወጡ ማድረግ ይችል ነበር። ‘ይህን ሳደርግ በታጣቂ እመታለሁ’ የሚል ፍርሃት አድሮበት ቢሆን እኳን ሊሞት የሚችለው አንድ ጭስ ተኳስ ወታደር ብቻ ነበር። ሞርታር ታጥቆ ከገባው መካከል ግን በሺህዎች የሚቆጠር ወታደር የፋኖን ጥይት በግንባሩ ቀርቅሯል። 
በመሰረቱ “ሽፍታ” የሚሉት ነገር ወያኔ የአማራን የነፍጠኝነት ባህል ለማጥፋት የፈጠረው ትርክት እንጂ ወንጀል አይደለም። ለተላላኪ የቀበሌ ካድሬ አልገዛ ብሎ ጫካ የገባ የጎበዝ አለቃ ሁሉ አርበኛ እንጂ ሽፍታ አይባልም። የወታደራዊ ዘመቻው አላማ ግልፅ ነው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ፥ በአንድ በኩል አማራን፤ በሌላ በኩል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ማፅዳት! ይህም ኦነጋውያን እየሄዱበት ላለው ሀገር አፍርሶ ሀገር የመሥራት እንቅስቃሴ ወሳኝ ሂደት ነው። 

መፍትሔ


የወረራ ስርዓቱ አማራና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል። ይህ አዲስ ፖሊሲ አይደለም፤ የአባቶቻቸው የ500 ዓመታት ውርስ ነው። ዝም ከተባሉ ከማጥፋት አይመለሱም። ለዚህ መፍትሄው አንድ ነው። ለመኖር መዋጋት! 
አማራ ራሱን ከጅምላ ጭፍጨፋ ለመከላከል የጀመረውን ሕዝባዊ ውጊያ አጠናክሮ በመቀጠል የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተባለን ወታደር በጠቅላላ ጠርጎ ከአማራ “ክልል” ማስወጣት አለበት። የትግል መሪዎቹን መጠበቅ ይገባዋል። ምንጊዜም የሕዝብ ሃይል አሸናፊ መሆኑን አውቆ ይህንን ለማድረግ ማቅማማት የለበትም። ዓለም ፀንታ የምትኖረው ተመጣጣኝ የሃይል ሚዛን በመፍጠርና በመዋጋት እንጂ ጊዜ በሰጣቸው ቅሎች ቸርነት አይደለም። 
ኑሮ ማለት ከተፈጥሯዊ ሞት በስተቀር የሕይዎት ዋስትናን ማረጋገጥ ማለት ነው። ከፈጠረን መድሃኒዓለም በስተቀር አንድም አካል በነፍስ የመኖራችንና ያለመኖራችን አዛዥ፤ ናዛዥ መሆን የለበትም። 
ሕዝበ ክርስቲያኑ ከምንጊዜውም በበለጠ የአንገቱን ማተብ ማጥበቅ አለበት። ብሄርተኛው ብቻ ሳይሆን አማኙም ለመኖር መዋጋት ይጠበቅበታል። በየቤተ መቅድሱ ግድግዳ ላይ ከሚታዩ ቅዱሳን ስዕላት ጎን የምናየው ሰይፍ መንፈሳዊ አባቶቻችን ርኩሳን፥ ሰይጣናትን የሰየፉበት እንጂ ሽንኩርት የከተፉበት አይደለም። መንፈሳዊነት የጦር መሳሪያ አንስቶ ሃይማኖትን ከጠላት ወረራ መከላከልን አይከለክልም። ለማተብ ሰማዕት መሆን በምድር ክብር ነው። በሰማይም ፅድቅ ነው ብለን እናምናለን! 
ስለዚህ በሥላሤ ገዳም የሰፈረውን የወራሪ ሰራዊት በድንጋይም፤ በጠመንጃም መድረሻ አሳጥቶ ማስወጣትና ገዳሙን ወደ ቀደመ ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎቱ መመለስ ይገባል። ይህ የማይቻል ቢሆን እንኳን ስንሞክር መሰዋት ክብር ነው።

Filed in: Amharic