>

ብርሃኑ ጁላ ቀበቶውን ፈትቶ ተንበረከከ - ግን የአማራ ፋኖ ይህንንም የአፍ ''ጌም'' ማሸነፍ አለበት !!!

ብርሃኑ ጁላ ቀበቶውን ፈትቶ ተንበረከከ – ግን የአማራ ፋኖ ይህንንም የአፍ ”ጌም” ማሸነፍ አለበት !!!

ወንድወሰን ተክሉ

አማራውን ኡይደለም ትጥቁን ቀበቶውን አስፈትተን እናንበረክከዋለን ብሎ የፎከረው ብርሃኑ ጁላ እንደ ፎከረው በሶስተኛ ወሩ የራሱን ቀበቶ መፍታቱን አሳይቶናል-  ጉዳዩ አዲስ የትግል ስልት መሆኑን አውቀን ለሁለንተናዊ ድል ይበልጥ ለመታገል እንነሳ!!!

  አንቺም ተጫዋች ሆነሽ ተጫውተሽ ሞተሻል – አለ ሰውዬው።

ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ ጁላ ፖለቲካ መስራቱ ነው « እኛ ከፋኖ ጋር መዋጋት አንፈልግም። ከፋኖ ጋር ለመዋጋት ምንም ዓይነት አጀንዴ የለንም » ብሎ በአለቃው ሲለፍፍ – በግርድፉ  እውነት መስሎ ግን ዋና ዓላማው  በጦር ሜዳ ያልቻለውን ውጊያ በፕሮፖጋንዳ ለመናድ የመጣ ነው።

————-

ከሶስት ወር በፊት – « አማራን አይደለም ትጥቁን ቀበቶውን አስፈትተን እናንበረክከዋለን»

ከሶስት ወር ዘመቻ በሃ « እኛ ከፋኖ ጋር መዋጋት አንፈልግም»

፠ ከፋኖ ጋር ጦርነት አንፈልግም ኑዛዜ መንስኤ

ሰሞኑን በአቢይ አህመድ መሪነት የጦር አዛዦች ጄኔራሎች የመረጃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ዝግ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር።

የውይይቱ አጀንዳ አምስት ዋና ዋና ጭብጦችን ለማስረጽ ያለመ ሲሆን፦

፨ የቀይ ባሕር ፖለቲካ – የኢትዮጲያ ወደብ ፈላጊነት

፨ የወልቃይት ጠገዴ ራያ ጉዳይ

፨ በአማራ ላይ የተከፈተውና ሶስተኛ ወሩን የያዘው ወታደራዊ ዘመቻ

፨ የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አቅምና ብቃት የታቀኘበት ዝግ ስብሰባ ነበር።

በዚህ ወታደራዊ ዝግ ስበስባ ላይ የጦር መኮኣንኖቹ ለዋናው የጦር ሃይሎች አዛዥ አቢይ አህመድ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተው እቅጭ እቅጩን ነግረውታል።

1ኛ – ከአማራ ፋኖ ጋር መዋጋት አንችልም። አልቻልንም። በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈትነው ጦርነት አክሳሪ ነው

2ኛ – የመከላከያ ሰራዊት አቅም ተዳክሞ ተንኮታኩቶ ሳለ እያስተጋባን ያለው ግን ተቃራኒውን ነው

3ኛ – በቀይ ባሕር ጉዳይ መዋጋት አንፈክግም  እና መሰል የሆኑ  እውነታዎች የተነገሩት ሆነ።

ይህ ስብሰባ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ አቢይ አህመድ  የኦሮሞ ኤሊቶችን እና ካድሬዎችን ሰብስቦ  የአማራን ትግል ውስጡ ገብተን ካልከፋፈልነው በፋኖ ተሸንፈን ልንዋረድ ነው ብሎ ግዳጅ መስጠቱን መረጃዎች ደርሰውናል።

ከእነዚህ ውይይቶች – ማለትም  በአቢይ መራሹ ከተካሄደው የጦር መኮንኖች የጦር አዛዦችና የደህንነት ባለስልጣናት የግምገማ ስብሰባ በሃላ ይህንን ሶስት ወር ሙሉ  በውጊያ ሊያንበረክከው ያልቻለውን የፋኖን አደረጃጀት  ለመከፋፈል የሚያስችል እቅድና ስልት ነድፎ በይፋ ይዞ ብቅ ማለትን አማራጭ አደረገ።

ያም ውሳኔ « እኛ ከፋኖ ጋር ለመዋጋት አንፈልግም። ከፋኖ ጋር የሚያዋጋን አንድም አጀንዳ የለንም » ተብሎ ፋኖ ጽንፈኛ ነው አይደለም መሳሪያውን ቀበቶውን አስወልቀን እናንበረክከዋለን ብሎ በደነፋው ሃምሳአለቃ ለእነሱ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አንደበት እንዲታወጅ አድርጎ የፋኖን ተዋጊ ሃይል መከፋፈልን ስልት ይዞ ሊወጣ ችሏል።

ከፋኖ ጋር ለመዋጋት የሚያበቃ አንዳችም አጀንዳ የለንም የሚል ስርዓት በመላው አማራ ያሰማራውን ሰራዊት ሰብስቦ በማውጣት በተግባር እኔ ከአማራ  ጋር መዋጋት ሳይገባኝ ውጊያ ለከፈትኩት ይቅርታ ብሎ ክልሉን ለቅቆ በመውጣት ያውጃል ወይንስ ጨፍጫፊ ሰራዊቱን እንዳሰማራ ከፋኖ ጋር መዋጋት አልፈልግም ብሎ ይደነፋል ብለን ስንጠይቅ የመዋጋት አንፈልግም ዓላማ ተዋጊዎቻችንን ለመከፋፈል ያለመ መሆኑን እንረዳለን።

ሃምሳ አለቀ ብርሃኑ ጁላና አለቃው አቢይ አህመድ አሊ አማራን አይደለም ትጥቁን ቀበቶውን አስወልቀን እናንበረክከዋለን ብለው በመፎከር ጦርነት ባወጁ ሶስተኛ ወር ላይ ሁለቱም ሁለቱም ቀበቶ መፍታታቸውን ያወጁበት ሆናል። ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ በአማራ ሃይሎች አሸናፊነት አልተደመደመም።

ስልትና እስትራቴጂውን ቀይሮ በአዲስ መልክ ጦርነት አንፈልግም በሚል መከፋፈያ ሽፋን የተጀመረ አዲስ የትግል ምእራፍ ሆናል።

አማራው ከጠላቱ በኩል የሚሰጠው አንድም በጎነገር እንደሌለ ያውቃል። ወይም አውቌል። ነፍጡን ወድሮ ትጥቁን አጠንክሮ ተዋጊውን አበርክቶ የብልጽግናን መንጋ ጠራርጎ እስከሚነቅል ድረስ ትግሉን አጠንክሮና አቀጣጥሎ ያጧጡፋል እንጂ በዚህን ሰዓት መንግስት ተብዬው ጦርነት አይፈልግም ብሎ የሚጃጃልና የሚዘናጋ አማራ ይኖራል ብሎ ማሰብ አይቻልምና ትግላችንን እስከ ድል አጠንክረን መግፋት ይጠበቅብናል።

Filed in: Amharic