>

‹‹የቀደመውን ከይሲ›› በአካል ተገልጦ በኢትዮጵያ አየሁት (ከይኄይስ እውነቱ)

‹‹የቀደመውን ከይሲ›› በአካል ተገልጦ በኢትዮጵያ አየሁት

ከይኄይስ እውነቱ

 

የዐምሐራ ሕዝባዊ ኃይል ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ቀዳሚ ተግባርህ በፍጹም ኃይልህ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወያኔና ኦነግ የተባሉትን አካይስቶች ማጥፋት ነው፡፡ ጠላት ከውስጥም ይምጣ ከውጭ ያለ ማመንታት ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከርጉም ዐቢይና አገዛዙ እንዲሁም ህልውናው እያከተመ ካለው ከአሽከሩ ብአዴን ጋር ማናቸውንም ዓይነት ድርድር/ውይይት ማድረግ ከጥያቄ ውጭ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ትግልህ ህልውናህን በማስከበር የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ እንጂ ከአጋንንት ጋር ለመደራደር የሚያስችል ዐቅም ለማበጀት መሆን የለበትም፡፡

በተዋጊነትም ሆነ በደጀንነት ያለው መላው የዐምሐራ ሕዝብ ፋኖ ከርጉም ዐቢይና አገዛዙ እንዲሁም ሎሌው ከሆነው ብአዴን የሚወጡ ማናቸውም ማዘናጊያዎችን ባለማመን፤ ያልተደራጀው እየተደራጀ፣ ዕድሜው÷ አካላዊ ብቃቱና ጤንነቱ የሚፈቅድለት ወጣት ኹሉ ትግሉን በመቀላቀል የጀመረውን ፍትሐዊ የህልውና ተጋድሎ ከመከላከል ወደ ማጥቃት በማሸጋገር አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ የመጣብህ ጠላት ሕይወትህን፣ ነፃነትህንና ዐጽመ ርስትህን የሚቀማ እንደሆነ ለአፍታ መዘንጋት የለብህም፡፡

በክርስትናው አስተምሕሮ እግዚአብሔር አምላክን በባሕርይ ክብሩ ተገልጦ ያየው ከፍጡር ወገን ማንም የለም፡፡ ምክንያቱም በባሕርይው ክብሩ ቢገለጥ ከፊቱ ጸንቶ የሚቆም የለምና፡፡ 

በተቃራኒው የሐሰት አባቷ÷ የበጎ ኹሉ ጠላት የሆነው ዲያቢሎስ ርኵስ መንፈስ መሆኑ ቢታወቅም በጸሊም ገጹ በኅሡም/በከፋ አርአያው በከረፋ ሽታው የተከሠተባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ አባታችን አዳምን እና እናታችን ሔዋንን ባሳተበት ጊዜ ጸሊም ገጹን ሕሡም/የከፋ ጎስቋላ አርአያውን ፍጉግ/የከረፋ ሽታውን ይዞ አልሄደም። ይልቁንም በእባብ ተሰውሮ ሂዶ ድል ነሳቸው እንጂ። ዛሬም በተቀደሰችው ምድረ ኢትዮጵያ ዲያበሎስ ከቀደመው ከይሲ የተሻለ ማኅደሩን አግኝቶ በከይሲ በተመሰለው ርጉም ዐቢይ አድሮ ኢትዮጵያን እያመሳት ይገኛል፡፡ አብዛኞቻችሁ እንደምትገምቱት ግዘፍ ነሥቶ አካል ገዝቶ በኢትዮጵያ ምድር ያየሁት ‹የቀደመው እባብ› ሌላ ሳይሆን ርጉም ዐቢይ ነው፡፡

በርእሰ መጻሕፍቱ (ራእ.12) እንደተመዘገበው በሰማይ ሰልፍ ሆኖ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን እንደተዋጉ፣ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር እንደተዋጋ፣ ይሁንና ሚካኤልና መላእክቱን እንዳልቻላቸው፣ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ እንዳልተገኘለት፣ ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ከሠራዊቱ ጋር ወደ ምድር እንደወደቀ፣ ወንድ ልጅ የወለደችውን ያቺን ሴት (ወላዲተ አምላክን) እንደተከተላት፣ የምታመልጥበትና ወደምትጠበቅበት ቦታ ለመድረስ እንደ ታላቅ ንስር ያለ ኹለት ክንፍ እንደተሰጣት፣ ከአፉም ወንዝ የሚያህል ውኃ አፍስሶ ሊያጠፋት ቢሞክርም ምድሪቱም እመ አምላክን ረድታ አፍዋን ከፍታ ከዘንዶው አፍ የፈሰሰውን ወንዝ እንደመጠጠች ይነግረናል፡፡ ይህ ቃለ እግዚአብሔር በዚህ ጽሑፍ የተነሣበት ዓላማ ምስጢር ያዘለ መንፈሳዊ  የሆነውን ትርጕም ለማብራራት ሳይሆን አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ሠላሳ ሁለት ዓመታት ወያኔና ኦነግ/ኦሕዴድ በሚባሉ ወንጀለኞች አገዛዞች የገጠማትን፣ በታሪኳ አይታ የማታውቀውን አገርንና ሕዝብን ለማጥፋት ሆን ብሎ ታቅዶ፣ በመዋቅርና በሕገ ወጥ ‹ሕግ› ተደግፎ ሥርዓታዊ በሆነ መልኩ ለደረሰብን  ፈተና መውጫውን መንገድ ለማሳየት አብነት እንዲሆነን በማሰብ ነው፡፡

በቅዱስ ትውፊት እንደተላለፈልን ዘንዶው እመቤታችንን ባሳደደበት ወቅት ካረፈችባቸው፣ እግዚአብሔር ካዘጋጀላት ወይም ታላቁ መጽሐፍ እንዳለው ‹ከተጠበቀችባቸው› ቦታዎች አንዷ ቅድስት ኢትዮጵያ ናት፡፡ በዚህም ጊዜ አበው ቀደምት እንደሚነግሩን ልጇ ወዳጇ ለድንግል እናቱ ኢትዮጵያን ዐሥራት አድርጎ ሰጥቷታል፡፡ የዐሥራት አገሯ በመሆኗም ኢትዮጵያውያን (‹የአውሬው› ገንዘብ ከሆኑት በስተቀር) ለእመቤታችን ያላቸው ፍቅር የተለየ ነው፡፡ የድኅነታችን ምክንያት እና በመስቀሉ ሥር በራሱ በዓለም መድኃኒት ለሁላችን የተሰጠችን መንፈሳዊ እናታችን በመሆኗ፡፡ በተቃራኒው ፀረ-ማርያሞች የኢትዮጵያና የተዋሕዶ ጠላቶች መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፡፡ ‹የአውሬው› ማኅደር የሆኑ ኹሉ ኢትዮጵያን፣ ከቆመችባቸው ዐበይት አዕማድ ቀዳሚ የሆነችውን የኢኦተቤክ እና አገሩንና የኢትዮጵያ ቤክንን ለመጠበቅ ህልውናው ሊጠፋ እስኪቃረብ ድረስ ተነግሮ የማያልቅ ጸዋትወ (በየዓይነቱ) መከራ እየተቀበለ የሚገኘውን የዐምሐራ ሕዝብ በደም ጎርፍ ተወስደው እንዲጠፉ እያሳደዱ ይገኛሉ፡፡ 

ዛሬ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ የሆነውን ኹሉ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እየተፋጠኑ የሚገኙት ርጉም ዐቢይና የጥፋት ሠራዊቱ ‹በሴቲቱ› የመንፈስ ልጆች ላይ ውጊያ ከፍተዋል፡፡ እምነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ እውነትን፣ ተስፋን ይዘው ‹አውሬውን› ገጥመውታል፡፡ ‹ለሴቲቱ› እናታቸው እንደተሰጠውም እንደ ታላቅ ንስር ያለ ኹለት ክንፍም ይሰጣቸዋል፡፡ በዚህም ሚካኤልና መላእክቱ ከጎኑ እንደሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ወያኔ እና ኦነግ የተባሉ አካይስቶችን ቀጥቅጠውና ድል ነሥተው ወደ አንጦርጦስ ያወርዷቸዋል፡፡ ብአዴን የተባለ የአገርና የሕዝብ ባላጋራ ለፍርድ ይቀራል፤ ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብለው ከነፈሰው ጋር ለመቆም የተዘጋጁት ነውረኞች ብን ትን ብለው በአየር ይቀራሉ፡፡ ኢትዮጵያን የምትሉ በአራቱም ማዕዝናት የምትገኙ ወገኖቼ ሳይረፍድ ሰልፋችሁን አካይስቶቹን እየተዋጋ ካለው የዐምሐራ ሕዝባዊ ኃይል ጋር አድርጉ፡፡ ቢያንስ አካባቢአችሁን ከአካይስቶቹ አጽዱ፡፡ ርጉም ዐቢይ መጨረሻውን ዐውቆ የማይቆፍረው መሬት፣ የማይፈነቅለው ደንጊያና የማይቧጥጠው መንገድ የለም፡፡ ሆኖም የርጉም ዐቢይና ሠራዊተ አጋንንቱ ጊዜአቸው ተፈጽሟል፡፡ 

የዐምሐራ ሕዝባዊ ኃይል ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ቀዳሚ ተግባርህ በፍጹም ኃይልህ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወያኔና ኦነግ የተባሉትን አካይስቶች ማጥፋት ነው፡፡ ጠላት ከውስጥም ይምጣ ከውጭ ያለ ማመንታት ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከርጉም ዐቢይና አገዛዙ እንዲሁም ህልውናው እያከተመ ካለው ከአሽከሩ ብአዴን ጋር ማናቸውንም ዓይነት ድርድር/ውይይት ማድረግ ከጥያቄ ውጭ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ትግልህ ህልውናህን በማስከበር የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ እንጂ ከአጋንንት ጋር ለመደራደር የሚያስችል ዐቅም ለማበጀት መሆን የለበትም፡፡ አፅራረ ኢትዮጵያ ለሆኑት ወያኔና ኦነግ ግልጽ ድጋፍና አቋም በመያዝ የለበጣ ‹ሰላም› ለኢትዮጵያ እናመጣለን ከሚሉ ማናቸውም የውጭ ኃይላት ጋር መነጋገርም ሆነ በሸፍጥ በተሞላ ድራማቸው ላይ መገኘት አያስፈልግም፡፡ ዐምሐራውም ሆነ ኢትዮጵያ ሰላማቸውን የሚያገኙት ዓለምን ከሚያምሱ የጥፋት ኃይሎች/መንግሥታት ሊሆን አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ መዳን ‹የአውሬው› መጋለቢያ ፈረሶች ከሆኑት፣ በኢኮኖሚና ወታደራዊ ኃይላቸው ለጊዜው የበላይነት ካገኙት፣ በ‹ሰብአዊ መብት› ሽፋን ግበረ ሰዶምና ግብረ ገሞራን በማጽደቅ የለየለት ዕብደትን በዓለም በማሠልጠን ከፈጣሪ ጋር ከተለያዩት ምዕራባዊ መንግሥታት/አጋንንታዊ ኃይሎች ሊሆን አይችልም፡፡ በጭራሽ! አካይስቶቹን ማን አሠማራቸውና? ቅዱሳት መጻሕፍት ‹አጋንንትን በአጋንንት› ማውጣት እንደማይቻል በጎላ በተረዳ ነገር አስተምረውናልና፡፡ ፈረንጅ ጣልቃ ከገባበት የፕሪቶሪያው ድርድር መማር ካልፈለግህ የራስህ ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ያለ ውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ብሔራዊ ንግግር መደረግ ካለበት በቅድሚያ ይህ አገርንና ሕዝብን ያዋረዳ ቆሻሻ የወንጀለኛ አገዛዝ ሊወገድ ይገባዋል፡፡

ሌላው የዐምሐራው ሕዝብ በእጅጉ ሊጠነቀቅበት የሚገባው ጉዳይ ህልውናው እያከተመ ካለው፣ ላለፉት 32 ዓመታት ሕዝቡን ለእልቂት ከዳረገውና አሁን ለደረሰበት የህልውና ሥጋት ካበቃውና ግንባር ቀደም ጠላቱ ከሆነው ብአዴን ከሚባል ነውረኛ ቡድን ለሚሠነዘሩ ማዘናጊያ ሐሳቦች ዦሮውን ሳይሰጥ ራሱን በማደራጀት የጀመረውን የህልውና ማስከበር ትግል የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ እነዚህ የምድር ጉድፎች በመጨረሻውም ሰዓት ሕዝባችንን በማዘናጋት ጌታቸው ለሆነው ኦነግ ግዳይ ለመጣል ማቀዳቸውን ቀድሞ ሊነቃ ይገባል፡፡

ወገኔ! የሰልፍህ መነሻም መድረሻም ርጉም ዐቢይን እና የአጋንንት ሠራዊቱን አለማመን መሆን ይኖርበታል፡፡ አሸከሩንና ምውቱን ብአዴንንም እንደዚሁ፡፡ እነዚህ ድኩማን አሁንም ‹ቄስና ሽማግሌ› እንዲሁም ‹ውይይት› እያሉ አሳልፈው ሊሰጡህ መዘጋጀታቸውን የሰማህ ይመስለኛል፡፡ ሚካኤልና መላእክቱ ከዲያቢሎስና ሠራዊቱ ጋር ውጊያ ገጠሙ እንጂ ለድርድር አልተቀመጡም፡፡ የምንነጋገረው ፍጹም ሰብአዊነት ከራቃቸው ኃይለ አጋንንት ጋር ነው፡፡ ለደመኛ ባላጋራህ ጊዜ መግዣ ዕድል ከሰጠህ ጥፋቱ ያንተው ነው፡፡አሰተውል!!!

ወገኔ! ድርሻችን ቢለያይም መላው የዐምሐራ ሕዝብ ፋኖ ነው፡፡ ይህን ያልተቀበለ ከጭንጋፉ ብአዴን በምን ይለያል? የእናቴ ልጅ ፋኖ ወይም የዐምሐራ ሕዝባዊ ኃይል ሰልፉ በማን መካከል እንደሆነ በግልጽ ልትረዳ ይገባል፡፡ አይደለም ‹ቄስና ሽማግሌ› ከአካይስቶቹ ጋር የፖለቲካ ድርድር ለማድረግ ያሰብሕ ሰዓት የእስካሁኑ ድካምህ ኹሉ ከንቶ ሆኖ ወደ ‹አንጦርጦስ› የምትወርደው አንተና ሕዝብህ ትሆናላችሁ፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቅንጅት የተሞላበት ሊሆን ይገባል፡፡ ሰሞኑን በጎንደር ውስጥ የዐምሐራውን ሕዝባዊ ኃይል የሚወጋ ሠራዊት በሌለ የአገር መከላከያ ሽፋን የኦነግ ወታደራዊ አመራሮች እያሠለጠኑና አስተዳደሩን በኃይል ለመቆጣጠር እየተዘጋጁ መሆኑን ህልውናው እያከተመ ባለውና ዐምሐራ ከሚባለው ‹ክልል› ምክር ቤት ስብሰባ ሾልኮ በወጣ ከፊል መረጃ ሰምተናል፡፡ በሚቻልበት ቦታ ሁሉ ይህ ሠልጣኝ ሠራዊት ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሳይጀምር ለማምከን ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገር ያስፈልጋል፡፡ የጠላት  ኃይል  ቤታችን ገብቶ ሊያጠፋን ሲዘጋጅ በጭራሽ መፍቀድ የለብንም፡፡ እየቀደምን የተሸረበብንን ሴራ ልናከሽፍ ይገባል፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዐቢይ መልአክት፤ በተዋጊነትም ሆነ በደጀንነት ያለው መላው የዐምሐራ ሕዝብ ፋኖ ከርጉም ዐቢይና አገዛዙ እንዲሁም ሎሌው ከሆነው ብአዴን የሚወጡ ማናቸውም ማዘናጊያዎችን ባለማመን፤ ያልተደራጀው እየተደራጀ፣ ዕድሜው÷ አካላዊ ብቃቱና ጤንነቱ የሚፈቅድለት ወጣት ኹሉ ትግሉን በመቀላቀል የጀመረውን ፍትሐዊ የህልውና ተጋድሎ  ከመከላከል ወደ ማጥቃት በማሸጋገር አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ የመጣብህ ጠላት ሕይወትህን፣ ነፃነትህንና ዐጽመ ርስትህን የሚቀማ እንደሆነ ለአፍታ መዘንጋት የለብህም፡፡

በሞታችን ህልውናችንን እናስከብራለን፤ በሞታችን ኢትዮጵያን እናድናለን፡፡ ቃል ለሰማይ ÷ ቃለ ለምድር!!!

Filed in: Amharic