>

እውነት ልደቱ አያለው ተለውጧል? (አሸናፊ)

እውነት ልደቱ  አያለው ተለውጧል?

አሸናፊ

ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ፓለቲካ አወዛጋቢ ማንነት ካላቸው ቀዳሚ መስመር ላይ ያለ ሰው ነው። በእውነቱ በ1997 ዓ.ም ብርቱካን ሚደቅሳ ተቀዳሚ ሊቀመንበር ሆና ስትመረጥ ልደቱ ማግለሉ በጣም ተሰምቶኝ ነበር። ነገርግን የኢንጂነር ሀይሉ መኢአድ አባላት ከሆነ አንድ የቅርብ ሰው ስለልደቱ ከቅንጅት ቀደም ብሎ ስለ ትህነግ የደህንነት አባል መሆንን ያወራኝ ስለነበር ብዙም አልከፋኝም። መጨረሻም ይህው አባል ባለበት ቦታ ተገኝ። እኔ ያለፈ ታሪኩን ለማውራት አይደለም ምክንያቱም ያለፈ ነገር አልፍል። ነገር ግን ከለውጡ በኋላ ልደቱ ተለውጧል ወይ ? አይመስለኝም እንደውም ምርጥ የትህነግ አሽከር መሆኑን ማስረጃ አንድ በአንድ በምሳሌ ላስረዳ። ከዚያ በፊት ልደቱ መቼ የህወሀት ተቃዋሚ መቼ ደግም የህወሀት ደጋፊ እንደሆነ ልናገር። ልደቱ ትህነግ በመንበራ ስትቀመጥ ተቀዋሚ ሆኖ ከች ይላል። ወንበራ ሲንቀጠቀጥ ደግም አጥቂወቿን ወጥሮ ይይዛል።
ማስረጃ አንድ፥ በትህነግ ግዜ ፓለቲካው ጥርቅም ብሎ በተዘጋበት ወቅት ሶስተኛው አማራጭ ብሎ እየደገፉ መቃወም በምትል ስላቅ ከች አለ። አብይ ስልጣን ላይ እንደወጣ እልም ያለ ተቃዋሚ ሆነ ። የትኛው ለመሀከለኛ ፓለቲካ ይቀርብ ነበር ? መልሱን ላንባቢ።
ማስረጃ ሁለት :- ሀገር በየቦታው በትህነግ ሸር ተወጥራ የዶር አብይ መንግስት ከፍተኛ ችግሩ ውስጥ ባለ ሰአት በኮረና ምክንያት ስንት ሀገራት ምርጫ ሲሰርዙ እሱ ለምን ተሰረዘ ብሎ ከትህነግ ጎን ቆም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ሲል በአይን እንኳን የማይተያዪትን ጀዋር ጋር ባንድ ፓፓ አሉ። እኔን ገምት ብትሉኝ ትህነግ አዛው ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም። አላማው ብጥብጥ መፍጠር እና በጎን ጌቶቹን ወደ አራት ኪሎ መመለስ ነበር።
ማስረጃ ስስት:- ልደቱ ጦርነቱ መጀመሪያ ትርክቱ የሚያዘነብለው ትህነግ አትሸነፍም ነበር ከረመና የሽግግር መንግስት አጀንዳ ይዞ ብቅ አለ ። ይች ደግም የኢትዮጵያ ህዝብ አንቅሮ የተፋት የትህነግ አጀንዳ ነበረች። እሱ አስተካክሎ ያቀረባት ። እስቲ ልዪነቷን አስረድን? ለኔ ይችም የትህነግ በኩል የተላከች አጀንዳ ነች።
ማስረጃ አራት:-ጦርነቱ ወቅት ትህነግ ጦርነቱን አልጀመረችውም የምትል ስልት ከኤርሚያስ ጋር ያቀነቅኑ ጀመር እንደውም ጦርነቱ ጥይት የተተኮሰበት ቀን አይደለም እያሉ ሊያስተባብሉ ሞከሩ። ይችም የሴኮ ጋዜጣዊ መግለጫ  ማስተባበያ ማጣታቸው ነው እንጂ ጦርነቱ አብይ ነው የጀመረው ይሉ ነበር።
ማስረጃ አምስት :- በቅርብ ጊዜ ለምሳሌ በወሎ ህዝብ ላይ ትህነግ የሰራው ግፋ ለማስተባበል የሄደበት ርቀት የሚገርም ነበር። ትህነግ ለተሰራባት ግፍ ተናዳ ነው ያደረገችው ብሎ በደልን  ባላንስ ሲያደርግ ነበር። እንደውም ትህነግ የአማራን ህዝብ እንደህዝብ በጠላትነት ፈርጃ አታውቅም ብሎ ተከራክራል ጋዜጠኛው ማኔፌስቶ ሲያነሳበት ብልጭ ብላ የጠፋች የታረመ ነው ብሎ በሙሉ አፉ ትህነግን ደግፎ ቆሟል። በሱ ልክ ያለ ፓለቲከኛ የጌታቸው ከአማራ ኤሊት ጋር እናወራርዳለን አዲስ እና የድሮቹ አማራን እንደ ህዝብ እያንቋሸሸች የዘፈነችው ዘፈን እየዘፈነች መሸለሏ  አማራ ክልል ላይ ገብታ ዘርፋ ገላ የወጣችው እንዲሁም የተካሄደው የሰሜን እዝ የሚለውን መጸሀፍ ላነበበ ሰው በየዋህነት ነው የተናገረው ማለት ቂልነት ነው። ምክንያቱም እንዲ የሚል አማራ የትህነግ አሽከር አልያም ቂላቂል መሆን አለበት። መቼም ልደቱ ቂላቂል አይመስለኝም።
ማስረጃ ስድስት:- ትህነግ ከዶ/አብይ ጋር ስትፈራረም ወደ መንበሯ ስትመለስ የተቋሚ ካባውን ይደርባል። መጀመሪያ አዲስአበባ ቤቴ አይነት ጭውቶ ጀመረ። እንግዲ እስክንድርን አዲስ አበባ ላይ እንደዛ ሲቃወም አንድ ነገር ተንፍሶ የማያውቀው ልደቱ ከች ብሎ አዲስ አበባን እናድን አይነት ጭውቶ ጀመረ ለምን አትሉም ለአዲስ አበባ ህዝብ ብሎ ሳይሆን የአብይ ስርአት ነቅንቆ ትህነግን መደገፍ ነበር ። ልደቱ የፓለቲካ ምት ምቶ ሙት አመቱ የወጣበትን አዲስ አበባ ህዝብን ለመጨረሻ ግዜ ምከረ ከሸፈበት። አዲስ ህዝብ ነቄ ስለሆነ ላሽ አለው።
ማስረጃ ሰባት:-ባለፈው ፍርድ ቤት  ላይ ቀርቦ በወያኔው የደህንነት አለቃ መሳሪያ መታጠቁን እራሱ  መስክራል። እስቲ መረራ ነው ኢንጂነር ሀይሉን ነው ማሙሸትን ነው የሽዋስን ነው እስቲ የቱን ተቃዋሚ መሪ ወይ አባል ነው መሳሪያ ያስታጠቀው? ከተገኝ እታረማለሁ ለኔ ግን እነኝ ማስረጃዎች በቂ ይመስሉኛል። ዛሪ አፈር ልሶ ለመነሳት እየታተረ ነው ተስቦ ተስቦ መሳይ መኮንን ጋር ደርሷል።
ቸር እንሰንብት
Filed in: Amharic