አማራ በቃ ካለ በቃ ነው
በቃሉ አጥናፉ ታዬ (ዶ/ር)
‘እብድና ዘመናይ እንደ ልቡ ይናገራል‘ እነዲሉ ልክ እንደ ስሟ በእድሜዋ እና በህይወት ልምዷ እውቀትን ያላካበተች ሚሚ ስብሀቱ የምትባለ ጋዜጠኛ “የአማራ ህዝብ የአዕምሮ ወስንነት እንዳለበት” ስትናገር በጊዜዋ ተደምጣለች ፡፡ ይህን የጋጠ-ወጥ አገላለፅ እየሰሙ በህወኃት ቤት ያደጉት እነ አብይ አህመድ አባባሉ እውነትነት ያለው ሳይመስላቸው አልቀረም፡፡ የብልፅግና ሊህቃን አማራን የሚያውቁት አዕምሮዓቸው ሆዳቸው በሆኑ በብአዴን አመራሮች እና በነ ሚሚ ስብሀቱ ንግግር ነው፡፡
በዘመናት መካከል ሰምተነው እና አይተነው የማናውቀው ግፍ ሲፈፀምበት የነበረው ህዝብ አሁን በቃኝ ማለት ጀምሯል፡፡ ይህንን ትግል ሊያስቆመው የሚችል ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል አይኖርም፡፡ እውነትን አንግቦ የሚታገልለት ዓላማን ታጥቋልና፡፡