>

ክፋት ሀይማኖታቸው ቋንቋ ህልውናቸው ከሆኑ አመራሮች ተጠበቁ (ይድረስ ለዳንኤል ክብረት) ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

ክፋት ሀይማኖታቸው ቋንቋ ህልውናቸው ከሆኑ አመራሮች ተጠበቁ (ይድረስ ለዳንኤል ክብረት)

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

በህወሐት የ27 ዓመት የአገዛዝ ዘመን በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የነበረውን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ወንጀል እንዳለ ሁኖ ለውጥ ከመጣ ከአምስት ዓመት ወዲህ እንኳን በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ የተፈጸመውን ያንን ኹሉ አሠቃቂ ግድያና የዘር ፍጅት ሲፈፀም የጠቅላዩ አማካሪ የት ነበሩ? አማራ በዶዘር በጅምላ ሲቀበር፣ ህፃን የአማራነት ብሄር ተሰጥቶት ፅንስ በቢላ ሲቀደድ እርሰዎ የት ነበሩ? አማራ በኦሮሚያ ምድር እንደበግ እየታረደ ሲያልቅ አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ዝም ያሉት አማካሪ ዛሬ ድምፅዎ እንዴት ተሰማ? ከደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ በማንነታቸውና በሃይማኖታቸው ምክንያት ታግተው ታፍነው ድምፃቸው ሲጠፋ የእርስዎ ድምፅ አልተሰማም? በኦሮሚያ ክልል ዜጎች ሲታረዱ፣ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ አንድ ቀን እንኳን ተሳስቶ መግለጫ ወይም ተቃውሞ ያላሰሙ አማካሪ ዛሬ ምነው ድምፅ ለማሰማት ሞከሩ? ላለፉት አምስት ዓመታት የተፈጸሙ ዘግናኝ ግድያዎችን፣ ዘረፋዎችን፣ መፈናቀሎችንና ያንን ሁሉ ግፍ አይቶ እና ሰምቶ ማስቆም ያልቻለ፣ ምላሽ ያልሰጠ አመራር ዛሬ በሚደረገው ትግል አስተያየት ለመስጠት ምን አቅም ተገኘ?  

የወገኑ ግፍና ሰቆቃ መቋቋም ተስኖት ባለ በሌለ አቅሙ የሚታገለውን ክቡር ትግል አለመደገፍ እና አለማድነቅ ይቻላል፡፡ ትግሉን ማንቋሸሽ ግን ንቁ ካልሆነ ከአዕምሮ ክፍል(unconscious part of the mind) የሚመነጭ እሳቤ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም:: ምክንያቱም ከዚህ የአዕምሮ ክፍል የሚመነጩ እሳቤዎች ያልተገሩ ናቸውና (They are primitive irrational impulses).

በማንኛውም ሰው ላይ በሚደርሰው ግፍ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁላችንም ልንታገለው ይገባል፤ ይህ እንኳን ባይሆን እንዴት ይህን ግፍ እና ሰቆቃ ለማስቆም በሚታገሉት ታጋዬች ላይ እንዴት እንቅፋት እንሆናለን? በየትኛው የሞራል ልዕልና ነው እነሱን ለመተቸት የበቃነው? ክፋት ሀይማኖታቸው ቋንቋ ህልውናቸው ከሆኑ አመራሮች ጋር ተጣብቀን፣ በምቾት እና በድሎት ቀንበር ተይዘን ለምንናገራት ቃል ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

 

Filed in: Amharic