>

የአብይ አህመድ ቅጥፈቶች የሚነግሩን ሃቆች !! (አሥራደው ከካናዳ )

የአብይ አህመድ ቅጥፈቶች የሚነግሩን ሃቆች !!

አሥራደው ከካናዳ 

           መንደርደሪያ

 • « እጅግ ቀጣፊ ነሽ – አባይ ነሽ ይሉሻል፤ 

ማበል እንኳን አንቺን ምድር ያበላሻል » :: አገር በቀል ስንኝ

 • « የፖለቲካ ሰዎች ሁሉም አንድ ዓይነት ናቸው፤ ወንዝ በሌለበት ድልድይ እንሠራለን ይሏችኋል » ኒኪታ ኩርቼቭ
 • «  La seule chose qu’un dictateur ne peut pas dicter, c’est la vérité.
  [ Jean Rostand ]  
 • « አንድ አምባገነን ደፍሮ ፤ አድርጉ ብሎ የማይናገራት ብትኖር፤ እውነትን ብቻ ነው »ዣን ሮስታድ

መግቢያ

ከአብይ አህመድ የቅጥፈት ባህር ውስጥ በማንኪያ የተጨለፉ፤ 

 • « ሰው በሃገሩ በጠራራ ፀሐይ የሚሞትበት ሃገር ከመምራት በላይ  የሚሳፍር ነገር የለም »
 • « እኔ እኮ እስካሁን አንድ ሰው አፈናቅዬ አላውቅም « 
 • « ሬሳዎችን ስንቆጥር ያገኘነው መረጃ አብዛኞቹ ሟቾች ኦሮሞዎች መሆናቸውን ነው »
 • « አየር ላይ የተበተነ ዱቄት፣አድርገናቸዋል ከእንግዲህ ተሰብስቦ ለምንም ሊሆን አይችልም »
 • « በባዕዳን የሚደገፈውን ጁንታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንቀብረዋለን! »
 • « እንደ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን፤ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን: በዓለም ስመጥር መሆን ሲችል፤ባልተገቡ ጉዳዮች፤ በሠፈር ታጥሮ በድህነት ውስጥ የሚኖር ሕዝብ ለመኖሩ እርገጠኛ አይደለሁም » …… ወዘተ.

በዚህ እጅግ የዘቀጠና፤ ስነምግባር የጎደለው አባባል፤ የአስተሳሰብ ድህነትና የታሪክ መሃይምነት፤ የተጠናወተው ግለ ሰብ፤ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ህዝብ ሲሰድብ መስማት በእጅጉ ያሳዝናል ያስቆጫልም:: « ሰው አፉ ሲከፍት ጭንቅላቱ ይታያል » ይሏችኋል ይህ ነው :: 

እራሱ አብይ አህመድ ከነ መሰሎቹ በጎሣ በረት ውስጥ ታጥረው፤ ቀደም ብሎ በፈጣሪያቸው ህወሃት ለ 27 ዓመታት፤ አሁን ደግሞ (ኦህዴድ/ኦነግ ከነ ጃንደረባው ብአዴን) በዳቦ ስሙ ብልጽግና በማለት ለ 5 ዓመታት፤ በድምሩ ለ 32 ዓመታት፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ በጦርነት ከአንዴም ሁለት ሶስቴ፤ አሁን ደግሞ ለአራተኛ ዙር፤ « አየር ላይ የተበተነ ዱቄት፣አድርገናቸዋል »፤ ካላቸው ህወሃቶች ጋር በመሆን፤ በአማራው ላይ ጦር አዝምቶ፤ ሕዝባችንን በጦርነት እየማገደ ያለው፤ እራሱ አብይ አህመድ እና ተከታዮቹ አይደሉም ?!  

የኢትዮጵያ ህዝብ ከዕምዬ ምንኒልክ ጀምሮ፤ ለዘመናት በከፈለው ግብር የተቋቋሙትን፤ አንጡራ ሃብቶች፤ የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኪሽን፤ አየር መንገድንና ባንኮችን፤ የልማት ተቋማትን፤ የእርሻ መሬቶች……ወዘተ. ለድንበር ዘለል ከበርቴዎችና ለአረብ አገራት እየቸበቸቡ፤ ህዝቡን በኑሮ ውድነት እያሰቃዩ ፤ በንቅዘት ወይም በሙስና ተዘፍቀው፤ በሌብነት የሃገር ሃብት እየዘረፉ፤ ሕዝባችንን በችግር አጉብጠው፤ አገራችንን በዕዳ ብዛት ደፍቀው እያሰመጡ ያሉት እነሱ እራሳቸው አይደሉም ??!!

ኢትዮጵያን አፈራርሰው፤ በመበታተን፤ የነሱ ጌቶች የሆኑት ህወሃቶች ታላቋን ትግራይ፤ አሽከሮቻቸው (ኦህዴድና/ኦነጎች) ደግሞ ታላቋን ኦሮምያ እንመሠርታለን እያሉ የሚደነፉት፤ በጠራራ ፀሐይ ወለል ብሎ እየታየ፤ ኢትዮጵያ አትፈርስም የምትለዋ ፌዝ፤ እነሱ የሚፈልጉትን እየነገርናቸው፤ እኛ  ያሰብነውን እንሥራ፤  የምትለዋ የበሻሻዎች ፈሊጥ፤ ደርቃ ከቆረፈደች ከረምረም ማለቱን አልተረዱም ::

አፈ ጮማና ሆደ ጩቤው አብይ አህመድ፤ ቀን ቀን ኢትዮጵያ ! ኢትዮጵያ ! ይልና ፤ ማታ ማታ የኢትዮጵያ ህዝብ ምሶሶዎችና የማእዘን ድንጋይ የሆኑትን፤ የኦርቶዶክስ ኃይማኖትን፤ አማርኛ ቋንቋን፤ የታሪክ ቅርስ የሆኑ ህንፃዎችን፤ የትምህርት ተቋማትን፤ የድሃ ወገኖቻችን መኖሪያ ቤቶች ሳይቀር እየቆፈረ፤ ሲፈነቅልና ሲንድ እንደሚያድር ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ከሆነ ቆይቷል::

ለዘመናት አብረው በመኖር፤ ተጋብተው ተዋልደው፤ የጋራ እሴቶችንና ባህል በማፍራት፤ አብሮነትን  በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር የመረጡትን፤ አማራን፤ ጉራጌን፤ ወላሞን፤ ሲዳማን፤ሱማሌን፤ ከንባታን፤ ሃዲያን፤ጋሞን  ….ወዘተ. በተጨማሪ ( ከኦህዴድና/ኦነጎች)እንዲሁም ከህወሃት ጋር አብረን አናብርም ብለው ኢትዮጵያዊነታቸውን የመረጡትን፤ የትግራይና የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ጭምር፤ በጦርነት በርሃብና በበሽታ በማሰቃየት እየፈጁ ይገኛል::

ማሳረጊያ

የጥላቻ አቁማዳቸውን ተሸክመው፤ በቂም ከዘራ እያዘገሙ፤ ለዘረፋ መሃል አገር የገቡት፤ ወያኔዎችና አሽከሮቻቸው ኦህዴድና ኦነጋውያን፤ ባልጠበቁት መንገድ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ጨዋነት፤ ትግስና መስተንግዶ በተመለከቱ ማግስት፤ ዘርፈው ለመሄድ ያቀዱትን ሃሳብ ሰርዝው፤ ውለው ማመሻሸት፤ ማደርና መሰንበትን፤ ተለማመዱ :: ደጉ ህዝብ ተንኮላቸውን ባለማወቅ እንደ ቤት እንስሳ አለማመዳቸው፤ እነሱ ግን ከሰውነት ተፈጥሯቸው ይልቅ የአውሬነት ተፈጥሯቸው ያየለ በመሆኑ፤ ለውለታው የሰጡት መልስ « ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ » እንዲሉ በተቃራኒው፤ ዘረኝነት ጎሠኝነትና ጥላቻ ሆኖ ይኸው 32 ዓመታት ተቆጠረ :: 

እንግዲህ፤ መድረስ አይቀር መድረስ ከተባለ፤ አዎ ! እዚህ ደርሰናል ::

የመጣንበት መንገድ ጠማማነትና ወልጋዳነት፤ ልንሄድበት ያሰብነውን መንገድ ይበልጥ ስላንሻፈፈው፤ ሁላችንም አብረን ገደል ለመግባት አፋፍ ላይ ሆነን እንጠራወዛለን :: አወዳደቃችን የከፋ በመሆኑ ዳግም ለመነሳት ያለን ዕድል የተሟጠጠ ነው :: ገፊዎች ከኋላ ሆነው በገፊነታችው የሚቀጥሉ መስሏቸው ጧት ማታ እሽኮለሌ ቢሉ፤ ቀኑ ይባሱን እየጨለመ ይሄዳል እንጂ እንደማይነጋ ገና አልገባቸው :: 

ገፊዎቻችን እኛን ወደ ዳር ገፍተው ፤ ያገኙትን ሁሉ ብቻቸውን ለመዋጥና ለመሰልቀጥ አሰፍስፈዋል፤ እንዳውም ተጣድፈዋል ::  

ግና ያልገባቸው ነገር ቢኖር የተፈጥሮ ህግ እነሱ እንደቋመጡት አይሾርም :: የራሱ የሆነ ህግጋትና ሁነቶች (ድርጊቶች) አሉት ::

ለምሳሌ ያህል የመሬት ስበትን መጥቀሱ ብቻ በቂ ነው:: 

የገፊዎች ጭካኔ በከፋ ቁጥር፤ ተገፊዎች መሳሪያ ሳያስፈልጋቸው፤ ብቻቸውን ገደል ላለመግባት ሲሉ: ገፊዎቻቸውን ጭምድድ አድርገው በመያዝ፤ ጎትተው አብረዋቸው ገደል እንዲገቡ ማድረግ ይገደዳሉ :: የተፈጥሮ ህግ የሆነው የመሬት ስበትም፤ ወደ ገደል የሚያወርደው የተገፋን ፍጡር ብቻውን ሳይሆን፤ ተገፊው፤ ገፊውን ጭምድድ አድርጎ ከያዘ፤ የተፈትሮ ህግ የመሬት ስበት፤ ገፊን ከተገፊው ጋር አብሮ ይዟቸው ገደል እንዲገባ ያግዘዋል:: 

መሳሪያ ባይኖረውም እንኳን፤ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ የደመ ነብስ ስጦታውን፤ ከተፈጥሮ ህግ ጋር በማጣመር፤ ከደፈረ ጠላቱን ድል ይነሳል፤ ካልሆነም ብቻውን ሳይሆን ጠላቱንም ጎትቶ አብሮት ይሞታል :: ጎበዝ ! እንግዲህ ብቻህን አትሙት ! ለስንቅ እንዲሆንህ ጠላትክን ይዘህ ሂድ ::

የዛሬዎቹ ገፊዎቻችን፤ ከትላንቶቹ ገፊዎቻችን፤ የባሱ ጮማ ጭንቅላቶች ናቸው፤ (ምንም እንኳን ከዝንጀሮ ቆንጆ የሚመረጥ ባይኖርም) ካለፈው ከጌቶቻቸው ስህተት ምንም ያልተማሩ ከመሆናቸውም በላይ፤ የመማር ፍላጎትም የላቸው:: 

ከአሁን በኋላ አንዱ ወደ ገደል ተገፍቶ ሲገባ፤ ሌላው አፋፍ ላይ ሆኖ፤ ያቅራራል ወይም ያፏጫል ማለት ዘበት ነው፤ ወይ ሁላችንም አብረን ገደል እንገባለን፤ ወይ ሁላችንም አብረን እንድናለን ::

ምርጫው ለሁላችንም በጋራ ቀርቧል !!

ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ !!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !! 

 

 

Filed in: Amharic