>

መነበብ ያለበት የመምህር ዘመድኩን በቀለ ርዕሰ አንቀጽ

“ርዕሰ አንቀጽ”

“…የዐማራ ፋኖ ትግል የሃገሪቷን የፖለቲካ ቅርጽ ከመሠረቱ እየቀየረ መጥቷል። አሁን ከላይ እስከታች፣ ከግራ ቀኝ እንደ ድሮው የተከበረው የዐማራ ሕዝብ ላይ ግማታም ጥምብ አቦሬ አፍን መክፈት ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሁለቸውም ተረድተዋል። “…የትግሬ ነፃ አውጪዋ ህወሓት ባመጣችው ዳፋ ምክንያት በሕወሓት ሰበብ ሙሉ ትግሬ ይሰደብ፣ ይወቀጥ እንደነበረው አሁን ዐማራን በዚያ መንገድ መስደብ፣ ማንቋሸሽ፣ ማዋረድ፣ በሻሻ፣ ዱቄት ብሎ መወብራት እፉ እንደሆነ እንደማይቻልም ሁሉም ዐውቋል ተረድቷልም። የሃገሪቱ ቁንጮ ተሳድቦ አዳሪው አረመኔው አቢይ አህመድም የትግሬ እና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ላይ በየቀኑ ይላግድ እንደነበር አሁን ዐማራ ላይ ትንፍሽ ማለት አልቻለም። ጭራሽ ከነመኖሩም ነው የጠፋው።
“…የዐማራ ትግል እነ ሲሳይ አጌናን ያለምንም ተኩስ ድምጥማጡን ነው ከሚዲያ ያጠፋው። የዐማራው ትግል ምንም እንኳ ለሻአቢያ ድጋፍ ለመስጠት በዐማራው ትግል አሳብበው ቢወጡም እነ መሳይ መኮንንን፣ እነ አንዳርጋቸው ፅጌን፣ እነ ነአምን ዘለቀንም ፍሬቻቸውን ወደ ቀኝ አብርተው ከብልፅግና ጎዳና እንዲታጠፉ እና እንዲሸበለሉ የግድ ብሏቸዋል። እነዚህ የዐማራን ትግል መምራት የማይፈቀድላቸው የጦም ዕቃዎች ቢሆኑም የዐማራ ትግል ግን ቀላልና የዋዛ አይደለም።
“…የዐማራ ፋኖ ትግል ዕድሜው 4 ወር ቢሆነውም ድንፋታም፣ ሰካራም፣ መሃይም ምድረ ምርኮኛ፣ የሰው ልክ አያውቄ የብልፅግና ጀነራሎችንም ትእቢት ነው ያስተነፈሰው። የአበባው ታደሰን ያልተገራ ወጠጤ ድንፋታም ምላስ ሰከን ያደረገው የዐማራው ፋኖ ምት ነው። የምርኮኛውንና ቀባጣሪውን ለንግግሩም፣ ለአለባበሱም ለከት የሌለውን የማረሻ የብርሃኑ ጁላን ሽለላ፣ ጌረርሳ ረገብ ያደረገውም የዐማራ ፋኖ ነው። አዎ የአማራ ፋኖ ልክ እንደ ትግሬው ጊዜ ጀነራሉም፣ ኮሎኔሉም፣ ወታደሩም፣ ፖሊሱም፣ ሚሊሻውም፣ ደንብ አስከባሪውም፣ የታክሲ ተራ አስከባሪውም አፉን ሊከፍትበት አልቻለም።
“…ጃዊሳ ብሎ ዐማራን እንደ ትግሬ ለማሸማቀቅ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ፈጥኖ የመጣው ከሃዲው ዳንኤል ክብረትም አፉን ይዞ እንዲቀመጥ፣ ምላሱን እንዲውጥ ለማድረግ ጊዜ አልፈጀበትም ዐማራው። የዛሬው ቀን እንዲህ እና እንዲያ ይባላል እያለ ትግሬ ላይ ሲያላግጥ እንደነበረው ዐማራም ላይ ለማላገጥ ተንደርድሮ ቢመጣም በቦክስም በተግሳጽም አርፎ እንዲቀመጥ ተደርጓል። ብዙ የአቢይ አማካሪዎች ቢኖሩም ከመንግሥት በላይ መንግሥት ለመሆን የሚዳክረው እና ዝሆን ለመምሰል የሚንጠራራውን በቀለኛው ሦስት ጎራሹ ዳንኤል ክብረትን ቁጫጭ፣ ቢንቢ፣ ትንኝ አህሎ ዱዳ አድርጎ ያስቀመጠው የዐማራው ትግል ነው። ምንም እንኳ በሰዶማዊው ቶማስ ጃጀው (ሸጋው ጃጀው) ፌስቡክ ላይ ቢጠቀምም በራሱ ገጽ ግን ዐማራን መስደብ ትቷል። ( ደግሞ ለዘመዴ እልህ ብለህ ሄጵ ብለህ ጀምር አሉህ ትቀምሳታለህ)
“…የዐማራው ትግል ከትእግስት፣ ከዝምታ፣ ከመቻቻል፣ ከእግዚአብሔር ያውቃል ማእቀፍ ወጥቷል። ከመመከት ወደ ማንከትም ዙሯል። የዐማራው ፋኖ ትግል የግብርና ሚንስትር ደኤታውን ዐማራ ካሸነፈ እና 4ኪሎ ከመጣ ኬንያ ሄደን የትጥቅ ትግል ጀምረን እንመለሳለን አስብሏል። የዐማራ ፋኖ ትግል የሀገሪቱን መከላከያ በሙሉ ውጦ እየመከተ በመደምሰስ አይበገሬነቱን አሳይቷል። የዐማራ ትግል ከክልሉ ወጥቶ በኦሮሚያ ጠላቶቹን መደምሰስ ጀምሯል። ያሳረዱትን፣ ያስጨፈጨፉትን የገቡበት ገብቶ መደምሰስ ጀምሯል። መከላከያ ሚኒስትሩ ትግሬ ወያኔውን አብርሃም በላይን መኪና አስቀይሯል። ቅዘን በቅዘን አስደርጓል።
“…የዐማራ ፋኖ ትግል አዲስ አበባ ገብቶ የተቃውሞ ወረቀት በይፋ መበተን ጀምሯል። እሱ ነገር በጣም ተስፋፍቶም ይቀጥላል ነው የሚሉት ዐማሮቹ። የዐማራው ትግል በአዲስ አበባ ተቀምጠው ፀረ ዐማራ ክፍት አፋቸውን የሚከፍቱትን ለመኮርኮም መንገድ ጀምሯል። ዐማራ የሚያሳፍሱ፣ የሚያስሩ፣ የሚያሳድዱ ፖሊስ በለው ወላ ካድሬ ግማታሙን ሁሉ መመዝገብ ጀምሯል። በዐማራ ክልል ብአዴን ሆነው በዐማራ ላይ ሲያቀረሹ የነበሩትን እንዳስታገሰው ሁሉ በአዲስ አበባ ተቀምጠው ክቡር በሆነው የዐማራ ማንነት ላይ ክፍት፣ ጥምብ አፋቸውን የሚከፍቱትን ለማስታገስ ጉዞ ተጀምሯል። ለዐማራው ትግል ከአምቦ የሚነሣው ነፋስም ምልክቱን ማሳየት ጀምሯል። የአምቦው ነፋስ ኮድ ነው። ለሌሎች የማይገባ ኮድ። አትጨቅጭቁኝ ሌሎቻችሁ። የዐማራው ፋኖ ትግል በአዲስ አበባም በአጎራባች ከተሞችም በተጠንቀቅ ቆሞ ፊሽካ እየጠበቀ ነው። የዐማራው ፋኖ ትግል አብቧል። አይፈሬ፣ አይሸማቀቄ፣ አይደክሜ፣ አይዝሌ ሆኗል። አዳነች አበቤ ብታፍሰው፣ ብታስረው፣ ሲዳማና አዋሽ አርባ ብታፈልሰው፣ ብታግዘው አልደነግጥ ብሏል። የዐማራው ፋኖ ትግል ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ የሚፈነጥቅ ሆኗል።
“…አሁን አሁን የቲክቶክ፣ የዩቲዩብ፣ የፌስቡክን መንደር፣ የቴሌግራምን ሰፈር በኩራት የሚንጎማለሉበት ዐማሮች ሆነዋል። ይሸልሉበታል፣ ይደንሱበታል፣ ይፎክሩበታል አይገልፀውም። ዐማሮች በዚህ መንደር የሚሰድባቸውን አዙሮት እስኪደፋው ድረስ መልሰው ይሰድቡታል፣ የሚዝትባቸውን ይዝቱበታል፣ የሚከራከራቸውን በበቃኝ ይዘርሩታል። እያየሁ፣ እየታዘብኩ ነው። እሳት የላሰ የዐማራ ትውልድ እየመጣ ነው። ከፊት ወንበርም እየተሰለፈ ነው። የሚያሸማቅቅ እንጂ የማይሸማቀቅ፣ ደፋር፣ ዐዋቂ፣ ልበ ሙሉ ጀግና እየተፈጠረ ነው። በፊት ኢትዮጵያዊ ነን ብለው ከጓዳ ተጠርንፈው የነበሩ ሁሉ አሁን በአደባባይ ዐማራ ነኝ ምንአባህ ታመጣለህ ብለው መንጎማሸር ጀምረዋል። ብዙ የሌላ ነገድ የዐማራ ደጋፊም ተፈጥሯል። አቤት ሲያስቀኑ በማርያም።
“…ዐማራነት መሰደቢያ፣ ዐማራነት መሸማቀቂያ መሆኑ እየቀረ ነው። በሃገር ቤት ዐማራ አግቶ ሚልዮን ብር መጠየቅ ቀርቷል። አሁን የዐማራ ሞቱ ግድያው፣ መስለቡም፣ መደፈሩም፣ ወርቅና ብር፣ ሰዓትም መዘረፉም በክልሉ ውስጥ በተሰማራው በኦሮሞ የአባገዳ መከላከያ ጦር ሆኗል። ጦሩ አንድ ሰው በገደለ ቁጥር መቶ ከብት መከላከያ ይገደላል። ሰሜን ሸዋ በአደባባይ ወጣቶችን የረሸነው መከላከያ በሁለት ኤፍኤስአር ሬሳውን ጭኖ ወጥቷል። አዎ አሁን በወለጋ ዐማራን እንደ ዶሮ ማረድ፣ በኦሮሚያ ዐማራ ላይ ግም፣ ክርፋታም፣ በአረቄና በጫት በጠነባ አፍ መሳደብ ቀንሷል። ዐማራነት በክልሎች ክብር ሆኗል። ዐማራነት ውርደት የሆነው በዐማራ ክልል ነው እርሱም በቅርቡ ይተነፍሳል። ከዚህ የጅል፣ የመሃይም ስብስብ አገዛዝ የድሮው፣ የጥንቱ የዐማራ የአገዛዝ ዘመን ተናፋቂ ሆኗል። ብሔር ብሔረሰቦች የዐማራን ወደፊት መምጣት እንዲናፍቁ፣ በጉጉት እንዲጠብቁትም አድርጓል።
“…የትግሬ ነፃ አውጪ ሰዎች የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሰዎችን እንደከብት፣ እንደ እንስሳ እየቆጠሩ ከዐማራ ጋር በግድ እንዲላተሙ ለማድረግ ቢጥሩም እየተሳካላቸው ግን አይደለም። በትግሬ ነፃ አውጪ አክቲቪስቶች ሴራና እባብነት አብዛኛው ኦሮሞ እየነቃ ነው። እናም የትግሬ አክቲቪስቶች በመቀሌ የሞላውን ሌብነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ዋልጌነት፣ ግድያ፣ ኤድስ፣ ራብ፣ ሽፍታነት መፍታት ትተው በኦሮሞና በዐማራ መካከል እሳት ለኩሰው በመሃል እነሱ የበሬው ቆለ* ይወድቅልኛል ብለው እንገፍ እንገፍ፣ እንዘጭ እንዘጭ የሚሉትንም ነገራቸውን ነቅቶባቸዋል። ዐማራ ግን ለደንታችሁ ብሎ ትግሉን ቀጥሏል።
“…አሁን ዳንኤል ክብረት በጎንደሬው ሉጢ በቶማስ ጃጀው ፌስቡክ ገጽ ከሚጽፈው በቀር ፋኖን የሚሰድብ ሰው ገጥሟችኋል። ከ OMN, KUSH, ZARA, TMH በቀር እነ ETV, FANA, WALTA, OBN ዐማራን ሲሳደቡ፣ ፋኖን ሲወቅሱ አይታችኋል…? አላያችሁም። ከአገዛዙ ባለሥልጣናት መካከል ወያኔ ላይ ሲዘፍኑ፣ ሲያቀረሹ ከነበሩት ባለሥልጣናት መካከል ወላ ሬድዋን፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ደመቀ መኮንን ወዘተረፈ አሁን ዐማራ ላይ አፉን የሚከፍት ሰው አግኝታችኋል…? የለም። የዐማራው ትግል የፋኖ ጀብድ ለኦሮሞ ነፃ አውጪና ለትግሬ ነፃ አውጪዎች ተገርዶ፣ የቲክቶክ ጊፍት ጠሮበት የነበረውን የአገው ሸንጎ አባል ሆኖ የነበረውን ቀዌውን ዮኒ ማኛን ራሱ እስኪከረበት ድረስ ወደ ቀደመ ማንነቱ መልሶታል። የዐማራ ትግል ገና ጾታውን ያስቀይረዋል።
“…የዐማራ ትግል ሲኖዶሱ ለምን አላወገዘልኝም ብሎ አዋራ አያስነሣም፣ ቤተ ክህነት ላቋቁም አይልም። የዐማራው ትግል ከዜሮ ቢነሣም 100% እንደሚደርስ አማኝ ነው። የዐማራው ፋኖ ትግል የመሣሪያ አቅርቦት ክንዱ ነው የሚያሰጠው፣ ጠላትን ገድሎ፣ ደምስሶ ነው የሚታጠቀው። የዐማራ ታጋይ 3 ቀን ያለ እህል መዋጋት የሚችል ጿሚ ነው። ቀርስ በልቶ ምሳ ካልበላ እግሩን ማንሳት እንደሚያቅተው እንደ አረመኔው አቢይ አሕመድ ሠራዊት አይደለም። የዐማራው ፋኖ ሙስሊሙ ጿሚ ጸሎተኛ ነው፣ ክርስቲያኑ ዳዊት ደጋሚ፣ ውዳሴ ማርያም፣ የሰኔ ጎልጎታ፣ መልክአ ማርያም፣ መልክአ እየሱስ፣ ድርሳነ ሚካኤል፣ ድርሳነ ገብርኤል ደጋሚ ነው፣ ጸሎተኛ፣ ቅዳሴ ሳያልቅ ተኩስ የማይጀምር ሃይማኖተኛ ነው። ለዚህ ነው ክንዱ እሳት የሆነው። በአጭር ጊዜ የገነነው።
“…የዐማራው ፋኖ ገና ብዙ ታሪኮችን ያሳየናል። በቅርቡ ደግሞ እጅን ከአፍ የሚያስጭን ተአምራትም ያሳየናል። እኔ በበኩሌ እየተደመምኩ ነው። የጎጃም፣ የሸዋ፣ የደቡብ ወሎ፣ የላስታ፣ የራያ፣ የደቡብ ጎንደሮችን ተጋድሎ እያየሁ እየተደመምኩ ነው። በጎጃም “ልጆቻችንን ገድላችሁ እንደ ትግሬ ያለ ቀባሪ ልታስቀሩን ነው እንዴ? በማለት ሕዝቡ የጁላን ብልት ሰላቢ የአባገዳ ሠራዊት አራውጦ ሙትና ቁስለኛ ሲያደርግ እንደማየት ምን የሚያስደምም ነገር አለ። የኦሮሞ ልጆች በማይመለከታቸው ጉዳይ ዐማራ ክልል ገብተው የአፈር ማዳበሪያ ሲሆኑ ከማየት በላይ ምን የሚያስደነግጥስ ነገር አለ?
“…የዐማራ ትግል ትግሬ ላይ የሲጋራ ኩሽና አፉን ሲከፍት የነበረውን የዶር ዳኛቸው አሰፋን አፍ አስጠርቅሟል። የሸገር ፕሮጀክት የሚለውን ለሽመልስ አማክሮ የብዙ ዐማሮች ቤት እንዲፈርስ ያደረገው ዳኛቸው አሰፋ፣ ትግሬ ላይ ክፍት አፉን ሲከፍት የከረመው ዳኛቸው አሰፋ አሁን ለዐማራ ሲሆን ትንፍሽ እንዴት ይበል…? የዐማራ ትግል ለመከላከያ ስንቅ እናዘጋጅ፣ በዳያስጶራ ሰልፍ እንቃወመው የሚል ወንድ እናቱ የወለደችው ከየት አባቱ ይምጣ? ጎፈንድሚ ለመከላከያ ሠራዊቴ፣ ሰልፍ በስቴት ዲፓርትመንት፣ ሸኔ ጨፍጫፊ፣ ወያኔ ገዳይ ብሎ ሰልፍ ይወጣ የነበረው የኖሞር ሰራዊት አሁን እንደ ኤሊ አንገቱን ሆዱ ውስጥ ቀብሮ ጭጭ፣ ምጭጭ ብሎ እንዲደበቅ አደረገው።
• እመነኝ ዐማራ ያሸንፋል። 4 ኪሎም ይገባል። ያን የተግማማ ሥርዓት አስወግዶ ፍትሕ ለሁሉም ያሰፍናል። ቅር የሚልህ ካለህ ታነቅ። • እንደተለመደው 1ሺ ላይክ ከተለየከ፣ 10ም ሺ 20 ሺም ሰው ማንበቡን እንዳየሁ በቶሎ እመለሳለሁ። ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ታነቡ ዘንድ የቆለፍኩት የከረቸምኩትን የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁንም እከፍትላችሁና እናንተ ደግሞ በተራችሁ ትተነፍሳላችሁ።
• ድል ለዐማራ ፋኖ…
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…
Filed in: Amharic