በፍርሃት ሲርድ
መነጠል ሲጨንቀው
ለካንስ ባንዲራም
ይጮኻል እንደ ሰው ::

እንደተለመደው የታችኛው ሠፈር ሌቦች ለዘረፋ ወደ ላይኛው ሰፈር ይሄዳሉ በዚህን ጊዜ በጎበዝ አለቃ የተዋቀረው የላይኛው ሠፈር ስብስብ ሌቦቹን እያሯሯጠ ወደ ሠፈራቸው ይነዳቸው ይጀምራል :: ይሄ ዱላ የበዛበት የሌቦች ቡድን የድረሱልኝ የበዛ ጩኸቱን እያሰማ ወደ መንደሩ እሩጫውን ያስነካው ጀመረ።
በሥራቸው እጅጉን ያፈረውና ያዘነው አብዛኛው የታችኛው ሠፈር ህዝብ ዝም ሲል ጥቂቶች ግን ለእገዛ እየተጠራሩ ሌቦቹን ለመርዳት ይሄዳሉ። ነገር ግን የሌቦቹ ስብስብ ከላይኛው ሠፈር ስብስብ በቁጥርም ይሁን በልብ ጀግንነት ያነሰ ነበርና በከበባ ውስጥ ሆኖ ይቀጠቀጥ ጀመር። ያን ጊዜ የሌቦቹ ቡድን መከራውን ሲበላና ሲረግፍ ለቅሶና ጩኸቱ እጅግ የበረታ ሆነ።
የዛሬውም አዲስ አበባ ላይ በየ አደባባዩ ፣ ዛፉ ፣ ህንፃው ፣ አጥሩ ፣ በየጥጋ ጥጉ ፣ …. እየተሰቀሉ ያሉት የኦህዴድ ብልፅግና የኦሮሙማው ቡድን የተውሶ ሰልባጅ የግብፅ ባንዲራ ከመጠን በላይ መብዛት የታችኛው ሠፈር የሌቦች ስብሰብ ጩኸትን በትልቁ እያስገነዘበን ይገኛል። ጥቁር ቀይ ነጭ ባንዲራዎች በየ አደባባዩ እና በየ ቦታው ከመጠን በላይ ድምፅ አውጥተው እየጮኹ መሆናቸውን በ0ይኖቻችን ማየት የቻልነው በአይናችን፤ በርቀት ያሉ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እያይዋቸው ነው:: ግን እነዚህ በባንዲራዎች ብዛት ውስጥ የሚታዩና የሚሰሙ ከመጠን በላይ የሆኑ ጩኸቶች መነሻ ምክንያታቸው ምን ይሆን ብሎ የሚጠይቅ ብልህ የሚጠፋ አይመስለኝም።
ለዚህ የብልህ ሰው ጥያቄ መልሱ በአሁኑ ሰዓት ከላይኛው ሠፈር መከራ የበዛበት ህዝብ እራሱን በፋኖ የጎበዝ አለቃ አደራጅቶ እራሱን በመከላከል ይሄን የኦሮሙማ የሌባ ቡድን እየቀጠቀጠ እያሯሯጠው ስለሚገኝ ነው። ምትና ሞት የበዛበት በእጅጉ የተደናገጠው ይህ የኦሮሙማ የሌቦች ቡድን በመሸሽ እሩጫ ውስጥ ሆኖ የመጨረሻ ያለውን የድረሱልኝ ከፍተኛ የጩኸት ጥሪ በግብፁ ባንዲራ በየ አደባባዩ እና መንገዶች ላይ በማሰማት ላይ ይገኛል።
የኦሮሙማው የሌቦች ቡድን ጉልበትም ኃይልም አቅምም እያነሰው መሆኑን ስለተረዳ ኡ…. ኡ…. ኡ…. እያለ በከፍተኛ መጠን እየጮኸ የኦሮሞን ህዝብ ድረስልኝ እያለ በባንዲራ ብዛት እየተጣራ ይገኛል :: ነገር ግን ከጥቂቶች በስተቀር እንደ ህዝብ ብዙሃኑ በሌቦቹ ሥራ ያፈረው ነውና፤ ሥራችሁ ያውጣችሁ ብሎ የሌቦቹን ቡድን የመጥፊያ ቀናቸውን፤ እነ ጃገማ ኬሎና በቀለ ወያ አክብረው አስከብረው በክብር ለብሰው ያጌጠባትን የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ቀና አድርጎ የሚያውለበልቡበትን ቀን እየናፈቁ ይገኛል።
ጌንመ ዘብሔረ አዲስ አበባ