>

ዮናስ ብሩ፤ የጭራቅ አሕመድ አዛኝ ቅቤ አንጓች 

ዮናስ ብሩ፤ የጭራቅ አሕመድ አዛኝ ቅቤ አንጓች 

 

ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ባጭር ጊዜ ውስጥ በትልቅ እመርታ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሶ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መነቅነቅ የጀመረው አርበኛ እስክንድር ነጋ ያማራ ሕዝባዊ ኃይልን ከመሠረተ በኋላ መሆኑን አሌ ማለት አይቻልም።  በተጨማሪ ደግሞ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል በውጭ መንግሥታት ተሰሚነትን ማግኘት የጀመረው የውጩን ጉዳይ ሻለቃ ዳዊት ከያዙት በኋላ መሆኑን መካድ አይቻልም።  

ከሁሉም በላይ ደግሞ እስክንደር ነጋ ያማራ ጥላቻ በደሙ የተዋሃደው የትግሬ ወይም የኦሮሞ ጽንፈኛ ካልሆነ በስተቀረ ከሞላ ጎደል ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያምነው ታማኝ፣ ሰብዓዊና ጨዋ ሰው ነው።  የእስክንድርን ታማኝነት፣ ሰብዓዊነትና ጨዋነት እጅጉን የሚያጎላው ደግሞ ከጭራቅ አሕመድ ቀጣፊነት፣ አውሬነትና ባለጌነት አንጻር ሲታይ ነው።  ስለዚህም በእስክንድር ነጋ የሚመራ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል አማራ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቀላሉ በዙርያው በማሰበሰብ የትግሉን ሜዳ አማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን መላዋን ጦቢያን የሚያጠቃልል ሰፊ ሜዳ አድርጎ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ውድቀቱን በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያቃርበው ሳይታለም የተፈታ ነው። 

ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ የኦነጋዊ መንግስቱን ዕድሜ ማራዘሙንና ያማራን ሕዝብ መጨፍጨፉን ለመቀጠል ያለው ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም የእስክንድር ነጋንና የሻለቃ ዳዊትን ስም በማጥፋት ባማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ማድረግ ነው።  ይህን ለማድረግ ደግሞ ፀራማራነት ወይም ሆዳደርነት ወይም ደግሞ ሁለቱም አለቅጥ ተፀናውተዋቸው እጅጉን ያጎበጧቸው መፃጉዕ (hunchback) ግለሰቦችን በማሰባሰብ ሰፊ የስም አጥፊ ሠራዊት መሥርቶ በተለያዩ ሚዲያወች ላይ በስፋት አሰማርቷል።  ከነዚህ ስም አጥፊ የሚዲያ ሠራዊት አባሎች ውስጥ አንዱ ደግሞ ዮናስ ብሩ ነው፣ አባልነቱ በፀራማራነቱ ወይም በሆዳደርነቱ ወይም በሁለቱ ምክኒያት መሆኑ በውል ባይታወቅም።  

ዮናስ ብሩ የጭራቅ አሕመድን ስም አጥፊ ሠራዊት የተቀላቀለው ለሆዱ ሳይሆን እንደማይቀር ለመገመት፣ ጭራቁን እባክህን የውጭ ጉዳይ አማካሪህ ልሁን እያለ የሚለማመጥጠው የሚያስመስልበት ረዣዥም የመማጸን ጽሑፍ ደጋግሞ ይጽፍ እንደነበረ ማስታወስ ብቻ በቂ ነው።  በፀራማራነቱ ሳይሆን እንደማይቀር ለመገመት ደግሞ ያማራ ልሂቃንን ቁሞቀር (hermitized) እያለ በያንዳንዱ ጽሑፉ ላይ የሚያዥጎደጉደውን የስድብ ጎርፍ መጥቀስ ብቻ በቂ ነው።  በዮናስ ብሩ ዕይታ የትግሬ ልሂቃን በወያኔነት፣ የኦሮሞ ልሂቃን ደግሞ በኦነግነት ተደራጅተው፣ ኢትዮጵያን ካልገነጣጠልን ሙተን እንገኛለን ብለው፣ ኢትዮጵያን አስተሳስሮ አንድ ያደረጋትን ያማራን ሕዝብ ሲጨፍጨፉ፣ ሁለቱም ወደፊት የሚያስቡ ተራማጆች (revolutionaries) ናቸው።  ያማራ ልሂቃን ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዳዘሉ፣ ያማራን ሕልውና ለማስጠበቅ ሲሉ ብቻ ሳይወዱ በግዳቸው ባማራነታቸው ሲታገሉ ግን፣ የዳህሩ (የኋለኛው) እንጅ የግንባሩ (የፊተኛው) የማይታያቸው አድሐሪወች (reactionaries) ትናንትና ላይ ተቸክለው የቀሩ ቁሞቀሮች (hermitized) ናቸው።  

ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ በዚህኛውም ሆነ በዚያኛው ምክኒያት ዮናስ ብሩ የጭራቅ አሕመድ ስም አጥፊ የሚዲያ ሠራዊት አባል ነው፣ ለዚያውም የክብር አባል።  በክብር አባልነቱ የተሰጠው ሚና ደግሞ ፋኖን የሚደግፍ መስሎ ፋኖን ማዳከም ነው።  አዛኝ ቅቤ አንጓች የተባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው።  

ዮናስ ብሩ እንግሊዘኛ በመጻፍ አዋቂነቱን ለማሳወቅ የሚጣጣር በሚያስመስልበት ሁኔታ የጉሲን (physics) እና የሒሳብሲን (mathematics) ጥቅሶችን አለቦታቸውና አላግባብ እየጠቀሰ፣ የተለያዩ ተመሳሳይ ቃሎችን (synonyms) በተከታታይ እየደረደረ፣ አንድን ዐረፍተ ነገር በተለያዩ ቃሎች አስር ጊዜ እየደጋገመ በሚጽፋቸው አለቅጥ በተንዛዙት ረጃጅም ጽሑፎች የሚያነሳው ነጥብ አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም እስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ፋኖን አዳከሙት የሚል ነው። 

ዮናስ ብሩ በየሶስት ቀኑ በተከታታይ በሚያወጣቸው ረዣዥም ጽሑፎቹ ላይ ያማራን ልሂቃን በጥቅል ከመዘለፍና ከመወረፍ ባሻገር እስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ፋኖን አዳከሙት እያለ ሺ ጊዜ ይደጋግማል እንጅ፣ እንዴትና ለምን አዳከሙት መፍትሔውስ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ቀርቶ አንዴም አንስቶት አያውቅም።  ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ በጭራቅ አሕመድ የስም አጥፊ ሠራዊት የክብር አባልነቱ ለዮናስ ብሩ የተሰጠው ሚና ስለ ፋኖ መዳክም አለመዳክም ማውሳት ሳይሆን፣ እስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ፋኖን አዳከሙት ተብለው ባማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጡ ማድረግ ስለሆነ ብቻ ነው።  

እስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ባማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጡ ለማድረግ ዮናስ ብሩ የሚጣጣረው ደግሞ፣ ከተመሠረተ አንድ ዓመት እንኳን ያልሞላው ያማራ ሕዝባዊ ኃይል ሁሉንም ያማራ ኃይሎች ባለማሰባሰቡ ጥፋቱ የአስክንድር ነጋና የሻለቃ ዳዊት ነው ብሎ የዋህ አማሮችን ለማሳመን በመሞከር ነው።  ይህ ጥረቱ የሚያሳየው ደግሞ ዮናስ ብሩ እንደማናቸውም ጥራዝ ነጠቅ ጸሐፊ የተለያዩ ጥቅሶችን መጥቀስ ስለሚችል ብቻ ራሱን አዋቂ ሌላውን አላዋቂ አድርጎ የማየት አባዜ እንደተጠናወተው ነው።  

ዮናስ ብሩ አወቀውም አላወቀውም ማናቸውም ትግል እየነጠረና እየጠነከረ የሚሄደው በሂደት ነው።  ጨቅላ ሕፃን በተወለደ ማግስት ቁሞ እንደማይሄድ ትግልም እንደዚሁ ነው።  ለምሳሌ ያህል ዮናስ ብሩ አንስቶት የማይጠግበውን ያሜሪቃን መንግሥት ብንወስድ፣ ጠንክሮ የወጣው ያንኪና ዲክሲ (Yankee and Dixie) ተባብሎ ላራት ዓመታት ርስበርስ ከተጨፋጨፈ በኋላ ነበር።  ሻቢያ ጠንክሮ የወጣው ከጀብሃ ጋር ለረዥም ጊዜ ተዋግቶ አያሌ ኤርትሬወችን ሰውቶ ነው።  የስብሐት ነጋና የመለስ ዜናዊ ፀረጦቢያ ቡድን ሕውሐትን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ጦቢያወዳድ ትግሬወችን በየጊዜው ወደ ተከዜ በርሐ እየወሰደ በየጊዜው ጨፍጭፎ ከጨረሰ በኋላ ነው።  ጨለማንና ውርማን ተግን አድርጎ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ በስተቀረ መሣርያ ከታጠቀ ባላንጋራ ጋር አንድም ቀን ተፋልሞ የማያውቀው፣ እድሜው ካምሳ ዓመት የሚበልጠው ኦነግ ደግሞ አሁንም ድረስ ለሃያ አንጃወች እንደተከፋፈለ፣ አሁንም ድረስ እርስበርስ እንደተገዳደለ ነው።  

በተቃራኒው ግን ያማራ ፋኖ የተለያዩ አደረጃጀቶች እንደ ወያኔና ኦነግ ርስበርሳቸው ደም ሳይፋሰሱ በሰለጠነ መንገድ ወደ አንድ አደረጃጀት እያመሩ ነው።  ዮናስ ብሩ ያማራ ፋኖን አሁኑኑ ለምን አላዋሃዱም እያለ እስክንድር ነጋንና ሻለቃ ዳዊትን የሚወቅሰውና የሚከሰው ደግሞ ፋኖወች እንዲዋሃዱ ፈልጎ ሳይሆን፣ የፋኖወች የውሕደት ሂደት እየተከተለው ያለውን የሰለጠነ ፈር ለቆ እንዲወጣና ፋኖወች እርስበርሳቸው እንዲጨፋጭፉ ነው።       

ስለዚህም አርበኛ እስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ሆይ፣ የጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ መንግስት ባስቸኳይ ተወግዶ ያማራ ሕዝብ ሕልውና ይረጋገጥ ዘንድ እናንተ በያዛችሁት መንገድ ትግላችሁን አጧጡፉ፡፡  ዮናስ ብሩና መሰሎቹ የጭራቅ አሕመድ ስም አጥፊ ሠራዊት አባሎች ደግሞ ትርኪ ምርኪያቸውን ይጻፉ፣ አርቲ ቡሪቲያቸውን ይለፍልፉ፣ ዝባዝንኬያቸውን ያራግፉ።  እናንት ግመሎች እነ ዮናስ ውሾች መሆናቸውን አትርሱ።  ውሾቹ በበሉበት ይጩሁ፣ ግመሎቹ መንገዳቸውን ይቅጥሉ።  ሙሉ ትኩረታችሁን በጭራቅ አሕመድ ላይ እንጅ ባሽከሮቹ ላይ አታድርጉ፣ ጌታቸው ሲወገድ አሽከሮቹ ብትንትናቸው ይወጣልና።  

መስፍን አረጋ 

mesfin.arega@gmail.com

 

Filed in: Amharic