>

የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት  የብር ኖት ህትመት በአገር ቤት!

 የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት  የብር ኖት ህትመት በአገር ቤት!

ዓለም ተሸዓተ በጦርነት!

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የቦርድ ዳይሮክተርስ ኮነሬል አብይ አህመድ ሰብሳቢ፣ አህመድ ሸዴ የፋይናንስ ሚንስቴር፣ ግርማ ብሩ የማክሮ ኢኮኖሚክስ አማካሪ፣  ተክለወልድ አጥናፉ የጠ/ሚ አማካሪ፣  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስቴር፣ ፍሬህይወት ታምሩ ኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶክተር ኢዬብ ተካልኝ የመንግሥት የፋይናንስ ሚንስቴር፣ ዶክተር ተገኝወርቅ ጌቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦርድ ሊቀመንበር፣ አብዱራህማን ኢድ  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ  ዋና ሥራ አስኪያጅ የቦርድ አባላት ናቸው፡፡ 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚቆጣጠረው የሃገሪቱ ኃብትና ንብረትና  $38bn (ሠላሳ ስምንት ቢሊዮን ዶላር)  ሲሆን ወይም ከኢትዮጵያን ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ)  ኃብት 34% (ሠላሳ አራት በመቶ) ይሆናል፡፡  ከዚህም የሚያመነጨው አመታዊ ገቢ $6.2bn.(ስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር) ገቢ ያስገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስምንት የቦርድ አባላቶች በኮነሬል አብይ ሰብሳቢነት አውዳሚ የጦርነት ኢኮኖሚ  በጋራ ሆነው በመምራት የትግራይን የአማራንና የኦሮሞን ርሃብተኞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት አግተው በአማራ ክልል በከባድ መሳሪያና በድሮውን እህል በማቃጠል፣ የእርዳታ እህል፣ መድኃኒትና ማዳበሪያ ወዘተ ለህዝብ እንዳይደርስ በማድረግ በርሃብ ቸነፈር የህፃናት እልቂት በሃገሪቱ እየተከሠተ ይገኛል፡፡ ርሃብን እንደ ጦር መሣሪያ በመጠቀም የዘር ፍጅት የፈፅሙ የፖለቲካ ወንጀለኞች ለፍርድ የሚቀርቡት ጊዜው ቅርብ ነው እንላለን፡፡ እነዚህ የቦርድ አባላቶች ለሚሊዮን ወጣቶች ሞት ተጠያቂዎች ሲሆኑ ለሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የመሰረተ-ልማቶች የጦርነት ውድመት  በተለይ በትግራይ፣ አማራ፣አፋር፣ ኦሮሚያ ክልሎች ተጠያቂ ናቸው እንላለን፡፡ ጦርነት መራሽ የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት የቦርድ ዳይሬክተሮች በአገር ቤት የብር ኖት ህትመት ፋብሪካ በመትከል  የኮነሬል አብይ አህመድ አንባገነናዊ አገዛዝ ብር እንደቅጠል በኢትዮጵያ ምድር የሚያትምበት ያነገሱት አሽቃባጭ ሚኒስትሮች እንደ ደርግ ሚኒስትሮች ለፍርድ መቅረባቸው የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡  

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ

  • ‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ይሆናል፡፡›› 
  • ‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተፈቀደ ካፒታል ብር አንድ መቶ ቢሊየን ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ሃያ አምስት ቢሊዮን በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሎል፡፡›› 
  • ‹‹ከአገር ውስጥና ከውጪ አገር ምንጮች ይበደራል፣ ገንዘብ ይሰበስባል፣ የእዳ ሠነዶችን ያወጣል፣ ዋስትና ይሠጣል እንደአስፈላጊነቱም ማንኛውንም እዳ ወይም ግዴታ ይሠርዛል፡፡›› 
  • ‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የዳይሬክተሮች ቦርድ በኢትዮጵያ ፌዴራዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር ሰብሳቢነት የሚመራ ይሆናል፡፡››………………………………….(1)

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሃገሪቱን አጠቃላይ ኃብትና ንብረት (መሬት፣ ፋብሪካ፣ ባንክ፣ ወዘተ) በቁጥጥሩ ስር ያደረገ በሞኖፖሊ የተያዘ ድርጅት ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት የማይቆጣጠሩት ሲሆን ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግሥታቸውን በጫካው ፕሮጀክት በብቸኝነት የሚወስኑበት የህዝብ ኃብት የሚባክንበት ሥርዓት መዘርጋቱን  የኢትዮጵያ የህግ አዋቂዎች ለህዝብ አላስተማሩም፡፡ ለኮነሬል አብይ አህመድ አሁን ገንዘብ የማተም ሥልጣኑንም ጠቅልሎ ሰጥቶታል፣ ይዞታል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ሥልጣንና ተግባሩን ተነጥቆል፡፡ 

ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ማተም (Money printing)፡- በ2020 እኤአ መንግሥት የባጀት እጥረቱን ለመግታት፣ ተጨማሪ የገንዘብ ኖት ለማተም ተገዶ ነበር፣ ብቸኛ ዘለቄታዊ  የወጪ አበዳሪዎች ድጋፍ ነበር፡፡ እንደ ኢትዮጵያ  ብሔራዊ ባንክ ሰፊ የገንዘብ አቅርቦት ስርጭት ሃያ በመቶ በየአመቱ በማደግ ላለፉት አስራአምስት አመታት  ሲያድግ ቆይቶ 104.4 ( መቶ አራት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ብር ደርሶ፣ በአሁኑ አመት አንድ ትሪሊየን ብር  አሻቅቦል፡፡ 

The government has in recent years been forced to print currencies to finance its budget deficit only sustained by foreign lenders. Broad money supply has been increasing by 20% annually according to the National Bank of Ethiopia over the last 15 years and skyrocketed from ……104.4 billion Ethiopian birr to almost 1 trillion birr this year…………………………………….…(2) 

  • በ2021እኤአ የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ መንግሥት ብሔራዊ ባንክን በማዘዝ በአዲስ እንዲታተም ያደረገው የብር መጠን 83.5 (ሰማንያ ሦስት) ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ 
  • በ2023 እኤአ( በ2015 ዓ/ም ) ግማሽ አመት 100 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር (ገንዘብ በማተም) መውሰዱ ታውቆል፡፡ 
  • ከ2021 እስከ 2023እኤአ የብልፅግና መንግሥት ብሔራዊ ባንክን በማዘዝ በአዲስ እንዲታተም ያደረገው የብር መጠን 183.5 (መቶ ሰማንያ ሦስት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ሌጣ ብር አትሞል፣ በምርትና በገንዘብ ዝውውር ውስጥ ያልነበረ የወረቀት ብር ነው፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ እየናረ ለመጣው የዋጋ ንረት አንዱ ዓይነተኛ ምክንያት ይህ በየጊዜው እየታተመ ወደ ገበያ ውስጥ እንዲሠራጭ የሚደረገው በምርትና አገልግሎት ያልተደገፈ ሌጣ ብር መሆኑን የኢኮኖሚ ጠበብት ይስማማሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (EIH))፣ በ2021እኤአ ተመሰርቶ በስሩ የሚቆጣጠረው ንብረትና ኃብት $38bn (ሠላሳ ስምንት ቢሊዮን ዶላር)  ወይም 34% (ሠላሳ አራት በመቶ) የኢትዮጵያን ጂዲፒ ኃብት ሲሆን በዚህም የሚያመነጨው አመታዊ ገቢ $6.2bn.(ስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር) ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ትልልቆቹ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን› ፖርትፎሊዮ ውስጥ የኢትዮጵያ አየርመንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮቴሌኮም መሳሰሉት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር ሆነው ኢኮኖሚውን ነፃና ክፍት በማድረግ ጎዳናውን በመጥረግ ትርፋማ የሆኑ መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶችን ጭምር በፕራይቬታይዤሽን ሽያጭ  (ለምሳሌ ኢትዮቴሌን በ850 ሚሊዮን ዶላር በመሸጥ) ድህነትን ያሳልጣል ተብሎ በኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥት ዘመን የተቆቆመ የሃገሪቱን ኃብትና ንብረቶች አጠቃሎ ለብቻው የያዘ የኮነሬሉ ሞኖፖሊ ድርጅት ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ የብር ኖት ህትመት ማሽን ፋብሪካ 

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና በጃፓን ቶፕፓአን ሆልዲንግስ ኢንክ (Japanese Toppan Holdings Inc.) የጨረታ ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአገር ቤት የብር ኖት ህትመትና ፓስፖርት እንዲከወን ይሆናል፡፡ ስምምነቱ የተደረገው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ማኔጅመንት፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በተካፈሉበት፣ እንዲሁም በጃፓን ቶፕፓአን ሆልዲንግስ ኢንክና የቀድሞው የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶሚኒክ ደ ቪልፒን ተገኝተዋል፡፡

Heads of the country’s nascent sovereign wealth fund are partnering with the Japanese Toppan Holdings Inc. in a bid to localize the printing of currency and passports. Sources disclosed the progress of the partnership was a topic during discussions between the management of Ethiopian Investment Holdings (EIH), central bank regulators (including Governor Mamo Mihretu) and Dominique de Villepin, former French Prime Minister. የኢትዮጵያ ኦህዴድ ብልፅግና መንግስት ከእንግዲህ ከአውሮፓ ኩባንያዎች  ከጀርመኑ ጂሴክ ዴቪየንት (German Giesecke+Devrient) ወይም ከእንግሊዙ ደ ላአ ሩዩ  (English De La Rue) ለብር ኖቶች ህትመት  ደጅ አይጠናም፣ ጥገኛ አንሆንም በእራሳችን ሃገር ብራችንን እናትመዋለን ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ኃላፊ መለከት ሳህሉ ከጃፓን ቶፕፓአን ሆልዲንግስ ጋር የሚደረገው  የህትመት ስምምነት ሦስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው ኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት (e-passports) ህትመት፣  ሁለተኛው የገንዘብ ኖቶች ህትመት (currency printing)፣ ሦስተኛው ልዩ ልዩ የንግድ ሴኩሪቲ ህትመቶች (various tradable securities) ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ (Ethiopian Capital Market) አገልግሎት የሚሆኑ ሚስጢራዊ ሰነዳች ያዘጋጃል፡፡ ከጃፓን ቶፕፓአን ሆልዲንግስ ካንፓኒ ከብርሃነ ሠላም ማተሚያ ቤትና ከትምህርት መገልገያ ማተሚያና አከፋፋይ ኢንተርፕራይዝ ጋር   የንግድ ሽርክና ስምምነት አድርገዋል፡፡ 

የቶፕፓአን ግራቪቲ ኢትዮጵያ  (Toppan Gravity Ethiopia (TGE) 51 (ሃምሳ አንድ ) በመቶ የሚስጢራዊ ህትመት የንግድ ድርሻ ሲኖረው፣ ሦስቱ ኢትዮጵያ ድርጅቶች 49 (አርባ ዘጠኝ) ከመቶ ድርሻ አላቸው፡፡የቶፕፓአን ግራቪቲ ኢትዮጵያ የ15 (አስራአምስት) ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት  የፓስፖርት ህትመት፣ የብር ኖቶች ህትምት፣ ኤቲኤም ካርዶች፣ ቼክና ብሔራዊ መታወቂያ ካርዶችና ልዩ ልዩ የንግድ ሴኩሪቲዎች ያዘጋጃል፡፡ 

The three comprise Toppan Gravity Ethiopia (TGE), which will hold a 51 percent stake in the security printing endeavor. Three other Ethiopian institutions will hold the remaining shares.

Berhanena Selam is one of 26 state-owned enterprises under the Investment Holdings. TGE will reportedly shell out a USD 15 million investment as part of the deal, providing capital for the printing of passports, currency, ATM cards, cheques, National ID cards, and tradable securities. 

ከጃፓን ቶፕፓአን ሆልዲንግስ ካንፓኒ ኢትዮጵያ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ድርጅትና የኢትዮጵያ ኢንደስትሪያል ሆልዲንግስ ጋር  የተናጥል ስምምነት መሠረት የኢፓስፖርት ህትመት (e-passports) በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪያል ፓርክ ለመስራት ታቅዶል፡፡ ዋና ጽህፈት ቤቱን በቶክዬ ያደረገው ቶፓአን ሆልዲንግስ ካንፓኒ 2022 እኤአ አመታዊ ገቢው አስራ ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ታውቆል፡፡……………………………(3) 

የአማራ ክልል ጦርነት በአስቸኳይ ይቁም!!!

የኦሮሚያ ክልል ጦርነት በአስቸኳይ ይቁም!!!

የፖለቲካ እስረኞች  በአስቸኳይ ይፈቱ!!!

ምንጭ
(1) https://www.lawethiopia.com › images › Reg 48…/PDF/Jan 31, 2022 — Republic of Ethiopia Proclamation No. 1263/2021

(2) Ethiopia is demonetizing its economy with new currency to tackle hoarding and illegal trade/ By Samuel Getachew/ September 14, 2020

(3) Ethiopia, Japan Venture Inches Towards Domestic Currency Printing [opinion]/December 17, 2023 / Official TOPPAN INC. press release

Filed in: Amharic