>

ኮለኔል አብይ ለዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ኤግል ሒልስ ሪል ስቴት 360,000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ መሬት ሸልሟል !

ኮለኔል አብይ ለዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ኤግል ሒልስ ሪል ስቴት 360,000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ መሬት ሸልሟል !

በስድስት አመታት ምንም አልተሠራ!!!  

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢትኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

የፈረሰው የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት  Eagle Hills project – La Gare in Ethiopia

 

ኮለኔል አብይ ለዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ኤግል ሒልስ ኩባንያ (Eagle Hills) 360000 (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ መሬት በነፃ በማበርከት ኤግልስ ሂልስ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ፕሮክት ወጪ ህንፃዎች ለመገንባት ያለአንዳች ጨረታ ተሸልሞ  ምንም ሳይሰራ ስድስት አመታት አልፎታል፡፡   Eagle Hills is a private real estate investment and development company based in Abu Dhabi, United Arab Emirates. The company is headed by Mohamed Alabbar, founder and managing director of Emaar ለኤግልስ ሒልስ ፕሮጀክት ሲባል የፈረሱ ህንፃዎች ቦታው ድረስ ሄዶ በማየት ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት አብይ፣ አዳነች አቤቤ፣ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የአዲስ አበባን ከተማ ንዋሪዎች በማፈናቀል ላይ እንዳሉ መገንዘብ ያሻል፡፡

{1} በዳግማዊ ዐፄ ምኒሊክ ዘመን በ1917እኤአ የተገነባው የመቶ አመታት ታሪካዊው ፍራንኮ ኢትዮጵያ ምድር ባቡር  ይፈርሳል፣ ኮነሬል አብይ የምኒልክን ታሪካዊ ውርስና ቅርስ በማጥፋት ቤተመንግስታቸውን አንድነት ፓርክ፣ ከመቶ አመታት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ መንግሥት ምድር ባቡር ቅርስ አጥፍተዋል፣  

{2} የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ብዙ መቶ ሚሊዩን ብር የወጣበት አዲስ ህንጻ ፈርል፣

{3} የቡፌ ደ ላጋር ታሪካዊ ባህላዊና ዘመናዊ የመዝናኛ ሥፍራ ፈርል፣ 

{4} የቬርኔሮ ህንፃ ባለ ስድስት ፎቅ ህንፃ  ፈርል፣

{5} የሞዓ አንበሳ ሃውልት  ከጣልያን ሃገር የተመለሰው ሐውልት፣ በሮም የጀግናው ዘርዓይ ድረስ የተሠዋበት ታሪካዊ ሃውልት በደንብ አልተያዘም፣ ወዘተ

ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ (United Arab Emirates)የአቡ ዳቢ ኩባንያ፣ ኤግል ሒልስ  (Eagle Hills launches project – La Gare in Ethiopia) በአዲስ አበባ ከተማ ለገሃር  ሠፈር  ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት 360,000 sq metres  (ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ) ካሬ  ሜትር ባለ ይዛታ ሲሆን የቦታው የስፋቱ ትልቅነት ሃምሳ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ያክላል፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ በተሰጠው ቦታ ላይ ባለ አራትና አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ለመገንባት፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች ለመስራት፣ አራት ሽህ ቤቶች ለመስራት እቅድ ነድፎ ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ወጪ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት 27% (ሃያ ሰባት) በመቶ ድርሻ አለው ተብሎል ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ ስልሳ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ በጀት በመመደብ ለአንድ ሽህ ስድስት መቶ አባወራዎች የመኖሪያ ቤቶች እንደሚሰራና ምንም ዓይነት መፈናቀል እንደማይኖር ለንዋሪዎቹ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ ኤግልስ ሒልስ ኩባንያ የለገሃር ፕሮጀክት ለሃያ አምስት ሽህ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና በሰባት አመት ፕሮጀክቱ ተሠርቶ እንደሚያልቅ ተገልጾ ነበር፡፡ “Abu Dhabi firm, Eagle Hills has launched a massive integrated community development project, La Gare in Ethiopia. La Gare will cover 360,000 sq metres of the Ethiopian capital, Addis Ababa and would include multi-star hotels, leisure outlets, commercial units, and 4000 homes. The estimated value of La Gare is $2 billion and the Ethiopian government is reported to hold a 27% share in the project. According to the Ethiopian Prime Minister, Abiy Ahmed, Eagle Hills has set aside an additional budget of $68 million for 1600 households that would be uprooted during the development process……..Reportedly, apart from creating a new city center, La Gare would also lead to an increase of approximately 25,000 jobs. The project is said to finish its first phase of development, mainly the construction of malls, in three years. The overall estimated time for project completion is reported to be seven years.”………………………………….(1) 

ኤግልስ ሒልስ (Eagle Hills) የጡት አባታቸው ኮነሬል አብይ አህመድ በተገኘበት  አቡዳቢ መሠረቱን ያደረገ የግል ሪል ስቴት ኢንቬስተር ወደ ኢትዮጵያ ምድርና ንግዱ ህብረተሰብ ሠተት ብሎ ገባ፡፡ በአዲስ አበባ ለገሐር ባቡር ጣቢያ እንዲከትም ኮነሬል አብይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ተመቻቸለት፡፡ በለገሐር ባቡር ጣቢያ ሦስት ሽህ ስድስት መቶ ካሬ ሜትር ኩታ ገጠም ቦታ በኮነሬሉ ያለ አንዳች ጨረታ ገጸበረከት ተበረከተለት፡፡ የለገሃር አራት ሽህ ንዋሪዎችን ያፈናቀለ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት ለንዋሪዎች መኖሪያ ቤት ይሠራል ተብሎ በውሸት ተሰበከ፡፡ 

ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት በስድስት አመታት የግንባታ ጉዞው አንድ የመኖሪያ ኮንዶሚኒየም በመስራት ገና ተጠናቆ ሳያልቅ በሙሉ መሸጡ ታውቆል፡፡ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት የገነባውን እየሸጠ በሚያገኘው ገንዘብ ሌላ በመገንባት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ኤግል ሒልስ ፕሮጀክት ሌላ ቦታ አንድ አምስት የመሠረት ግንባታ የሠራባቸው ሥፍራዎች በተለያዩ ሳይቶች ይስተዋላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ጋዜጠኞች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የከተማችን የፓርላማ አባሎች ካሉ ይሄን ሥፍራ ጎብኝተው፣ የሚሠራውን የወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት  ላለፉት ስድስት አመታት የተሠራ  የኤግል ሒልስ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት በመመልከት ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ኤግል ሒልስ ሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ድርጅት ሥፍራውን ተነጥቆ  ለኢትዮጵያዊያን  አገር በቀል ሪል ስቴት ኢንቨስተሮች በጨረታ ቦታውን እንዲያለሙ እድል ቢያገኙ ተዓምር መሥራት ይችልሉ፡፡ አገር በቀል ሪል ስቴት ኢንቨስተሮች፣ ሦስት መቶ ስልሳ ሽህ ካሬ ሜትር  ቦታ ሊዝ ገዝተው እንዲያለሙና በግፍ ለተፈናቀሉ ደሃ የህብረተሰብ ክፍል ቤት ጨምሮ በመገንባት፣ ኤግል ሒልስ ከአገር እንዲወጣ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡  

አብይ አህመድና የሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ አል ናህያን ሚስጢራዊ ግንኙነት አገራችንን  ወደ ማያባራ ጦርነት በማሸጋገር ላይ ይገኛል፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ደግሞ ሰው አልባ ድሮውን በመስጠት  ንፁሃን ዜጎች እንዲጨፈጨፉ አድርገዋል፡፡ ሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ  የኮነሬል አብይ አህመድን መንግስት በመደገፍ ሰው ዓልባ አውሮፕላኖች በመስጠትና በመሸጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነት በማቀጣጠል ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃውሞውን ማሰማት ይጠበቅበታል እንላለን፡፡

ምንጭ

 Abu Dhabi Based Eagle Hills Invests in Ethiopia/By  D&B Bureau/  November 21, 2018

Filed in: Amharic