>

''ራስ መኮንንንም አወረሙልህ።'''

• ራስ መኮንንንም አወረሙልህ።

መምህር ዘመድኩን በቀለ

“…መተማን~ሞቱማ፣ አዲስ አበባን~ፊንፊኔ፣ ጥቁር ውኃን~ቢሻን ጉራቻ፣ ናዝሬትን~አዳማ፣ ደብረ ዘይትን~ቢሾፍቱ፣ ዝዋይን~ባቱ፣ አዲግራትን~አደጋራ፣ ሊማሊሞን~ለመለማ፣ ሱማሌን~ሲመሌ፣ ኬኒያን~ኬኛ፣ ዋሽንግተን ዲሲን~ዋንገተን ዲሲ፣ ሚኒሶታን~ሚኒ ሱሉልታ፣ መንዜውን አበበ ቢቂላን፣ ወላይቴውን አቡነ ጴጥሮስን፣ ጎጃሜውን በላይ ዘለቀን ቂልጡ የሚል የአያት ስም በሃጫሉ ሁንዴሳ በኩል አስጨምሮ ሁሉም ኬኛ ብሎ ሲያወርም የከረመው ሼምለሱ ኦሮሙማ በመጨረሻም የአፄ ኃይለሥላሴን አባት ራስ መኮንንን አወርሟቸው አርፏል።
 “…ኦሮሙማው ጨካኝ ነው። የራሱ የሆነ ታሪክ ስለሌለው ሁሉን ታሪክ የእኔ ነው ይላል። በአማርኛ በመንበረ ተክለሃይማኖት ብዬ አልጠቀምም ሲል ቆይቶ፣ ስንትና ስንት ኦርቶዶክሳዊ ለዋቃ ጉራቻው ሲያርድ ከርሞ በመጨረሻ የኦሮሞን መንበር ምን ብሎ ለያመጣ ነው ብለን ስንጠብቅ “ከቤርቤረሰቦች መንበር” በአንዴ ፍሬቻ ሳያበራ “መንበረ ጴጥሮስ” ብሎ ከች ብሎ አረፈው። መንበር ግእዝ ነው። ጴጥሮስንም እንዲሁ ተርጓሚው ግእዝ ነው። “በርጩመ ቶሎሳ” ብለው ይመጣሉ ስንል ጭራሽ በነፍጠኛ ስም ከች አላሉም?
 “…ኦሮሙማ ሐረር ላይ የራስ መኮንን ሃውልት አፍርሶ አዋረደ። ቆይቶ አዲስ አበባ ላይ የአያታቸውን ስም ቀይሮ አወርሞ ሃውልትም ሠርቶ ከች አይል መሰለህ? በኦሮሙማ ነውር፣ ኃጢአት፣ ግፍ፣ ማፈር፣ ሼም የሚባል ነገር በጭራሽ የለም።

“…ራሳቸው አጼ ኃይለሥላሴ የአያታቸውን ስም ወልደ ሚካኤል ብለው ጽፈው እያዩ። በዓለምም ሆነ በኢትዮጵያም ታሪክ እየታወቀ፣ በላይ ዘለቀን ቂልጡ እንዳሉት ሁሉ የራስ መኮንንንም አባት ጉዲሳ በማለት የታሪክ ጄኖሳይድ ፈጸሙልህ። ራስ መኮንን ነፍጠኛ ናቸው ብለው ሃውልታቸውን ካፈረሱ በኋላ አዲስ አበባ ላይ አወርመው ሃውልት አቆሙላቸው።u
• አይ ኦሬክስ…!
Filed in: Amharic