>

- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚገኝ ድልና ሠላም፤ በሽልማት ሜዳሊያ የሚሸፈን ረሀብ የለም!

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚገኝ ድልና ሠላም፤ በሽልማት ሜዳሊያ የሚሸፈን ረሀብ የለም

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በውጪ ወራሪዎች፣ በውስጣዊ የእርስ በእርስ ሽኩቻ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የደረሱባትን ችግሮች ሁሉ ውድ የሆነውን የዜጎቿን ሕይወት እና የንብረት መስዋትነት ከፍላ ክብሯን አስጠብቃ እስካሁን ቆይታለች። ይህ እውነታ በተዎሰኑ የዓለም ሀገራት ሊባል በሚችል ሁኔታ የተፈጠረ ክስተት መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም። ይሁን እንጂ ሀገራችን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በባሰ መልኩ ደግሞ ላለፉት አምስት አመታት ከዓለም ሃገራት በተለየ መልኩ በነገድ ፖለቲካ የተነሳ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ነው።

በተለይም የሕወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝ በሕዝብ መስዋትነት እና ከባድ ተጋድሎ ከበትረ ስልጣን መልቀቁን ተከትሎ አልጋ ወራሽ የሆነው የኦነግ/ኦሕዴድ /ብልፅግና(ኦሮሙማ) ቡድን የገዥነት ቦታውን ከያዘ በኋላ ኢትዮጵያ በእሳት እየተጠበሰች ትገኛለች።
የኦነግ/ኦሕዴድ /ብልፅግና(ኦሮሙማ) ኢትዮጵያ የዜጎቿ ሁሉ እናትና ሀገር መሆንዋን ፈፅሞ በመካድ ብቻ ሳይዎሰን፣ የዜጎቿ መቃብር እና ምድራዊ ሲኦል እንድትሆን እያደረጋት ይገኛል።

የኦሮሙማ የገዥ ቡድን ባለፉት አምስት እና ስድስት ዓመታት ውስጥ በፈፀመው ህዝብን እርስ በርስ በማጋጨት ሀገር የመበታተን፣ በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እገዛ የሚከናዎን ሴራ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ዘግናኝ የሆነውን የእርስ በእርስ ጦርነት አካሂዳ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿን እንድታጣ ተደርጋለች፡፡

በንፁሐን ደም የሰከረው የነገድ አገዛዝ አሁንም የንፁሐን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት በጥይት አረር እና በረሀብ መቅጥፉን ቀጥሎበታል። የአማራ ሕዝብ የስርዓቱ መሰረታዊ ጠላት ተደርጎ በአገዛዙ በመፈረጁ፣ የነገድ ገዥዎች በቅብብሎሽ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀሙበት ይገኛሉ፡፡

የኦሮሙማ ቡድን ‘’አማራ ክልል’’ በሚኖረው ሕዝብ ላይ በወታደር የታገዘ ጦርነት የከፈተው ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን፣ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ግን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ ሕጋዊ ሽፋን ሰጥቶ የጥፋት ስራውን ቀጥሎበታል። የነገድ ፖለቲካ የወለደው የካድሬ ፅንፈኛ ፖለቲከኛን እና የሕወሀት/ኢሕአዴግን “ሕገ መንግስት’’ ሽፋን በማድረግ በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው ኢስብአዊ ጭፍጨፋ በህግ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን እንደቀጠለ ይገኛል።

ባልደራስ ለአውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በሕግ ሽፋን በአማራ ሕዝብ ላይ እንዲራዘም የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰላማዊ ሕዝብን የመፍጀት እና ሀገርን የማተራመስ ፈቃድ እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ የብልፅግና አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ከለላ በማድረግ በከባድ መሳሪያ እና በድሮን ንፁሐን ዜጎች መግደሉን እና አካባቢያቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ማድረጉን የተለያዩ ሃገር አቀፍ እና አልምአቀፍ ተቋማት ካወጡአቸዉ መረጃዎች እና ማስረጃዎች ማረጋገጥ ይቻላል።

ከዚህ በታች ከብዙ በጥቂቱ ተዘርዝረው የተቀመጡት ነጥቦች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከፀደቀበት ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የፈፀማቸው ግፎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፣የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ሌሎች ተቋማት ይፋ ባደረጓቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መገለጫዎች ተዘገበዉ ይገኛሉ።

➣ በድሮን ጥቃት ብቻ የሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሐን አማራዎች ሕይወታቸው አልፏል። ለምሳሌ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ መጥተህ ብላ ከተማ ፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ፣ በደንበጫ ከተማ ፣አማኑኤል ከተማ፣ ቋሪት፣ ፍኖተ ሰላም ከተማ ፣ አማራ ሳይንት ፣ አንኮበር እና ሌሎች አካባቢዎችን ጨምሮ በድሮን ጥቃት በርካታ ሰዎች ያለቁባቸው አካባቢዎች ናቸው።

➣ የአገዛዙ የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ያልታጠቁ ሲቪል ሰዎችን “ፋኖን ትደግፋላችሁ፣ ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ፣ መሣሪያ አምጡ፣ የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ” በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ አግባብ ውጭ በመንገድ ረሽነዋል፡፡በቅርቡ በጎጃም መራዊ ላይ ባልታጠቁ ወደ አንድ መቶ ሃምሳ በሚጠጉ ዜጎች ላይ የተፈጸመዉ የአደባባይ ርሽና ለዚህ አረመናዊ ድርጊት በማጣቀሻነት ሊነሳ ይችላል።ከሟቾቹ መካከል አንዲት መንታ ልጆች የወለደች እናት ከእነ ልጆችዋ ትገኝበታለች፡፡

➣ ፀበል ቦታ የሚገኙ ሕሙማን፣ የአብነት ተማሪዎች እና መነኮሳት የስርዓቱ ታጣቂዎች ኢላማ ተደርገው ተገድለዋል፡፡ ለአብነት ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ማርቆስ እና በሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ ፍልሰታ ደብረ ማሪያም እና ደብረ ኤልያስ ገዳም በርካቶች የተገደሉባቸው የእምነት ተቋማት ናቸው፡፡

➣ የአገዛዙ ሀይል ወደ ህክምና የሚሄዱ ህሙማን እና በሆስፒታል ውስጥ ሕክምና የሚከታተሉ ዜጎችን በሆስፒታል ከተኙበት አልጋ ላይ አውጥቶ ገድሏል፤ የተወሰኑትንም አድራሻቸውን አጥፍቷል፡፡

➣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ግንደወይን ከተማ ሞጣ በር ፣ባሕር ዳር፣ በፍኖተሰላም፣ በጎንደር እና በወልድያ ከተሞች ንፁሐን ዜጎች ህክምና ላይ የተገደሉባቸው እና ህክምና የተከለከሉባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ይህን ድርጊት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጭምር በመግለጫ ይፋ አድርጎታል፡፡

➣ በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ “በአማራ ክልል” የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሴቶች እና የጤና ባለሞያ ሴቶች ጭምር ተገደው የተደፈሩ ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ በተመዘገበ ዳታ ብቻ ቢያንስ 200 ሴቶች ተገደው ተደፍረዋል።

➣ የእርዳታ እህል ለተጎጅዎች እንዳይደርስ ተከልክሏል፡፡

➣ የሲቪል የንግድ እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ተዘርፈዋል፤የማሳ ላይ ሰብል ወድሟል፣ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል፤ የትምህርት ተቋማት ወታደራዊ ካምፕ ተደርገዋል፤ ሆስፒታሎች ተዘርፈዋል፡፡

➣ በደቡብ ጎንደር ወረታ ፣ እብናት ፣ በሸዋ ሮቢት ከተማ የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በጀውሀ ከተማ የጀውሀ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በብቸና የበላይ ዘለቀ መሰናዶ ትምህርት ቤት በወታደራዊ ካምፕነት እያገለገሉ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

➣ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንን ጨምሮ በርካታ የዕምነት ተቋማት ላይ የማውደም እና የመዝረፍ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ቅዱስ ላሊበላ ፣ደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ለአብነት የሚጠቀሱ አካባቢዎች ናቸው፡፡

➣ ሌላኛው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን የአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎችን በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች እገዛ ከመስከረም 6 /2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲካለሉ ተደርጓል፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ወረዳ የአውራ ጎዳና ከተማ ነዋሪዎች በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ሰብላቸው ወድሞ፣ ንብረታቸው ተዘረፎ፣ በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ጭምር ከተማዋ ፈርሳ እስከ ዛሬ ድረስ አካባቢው በኦሮሚያ ልዩ ሀይል እየተጠበቀ ይገኛል።

➣ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት “ለአማራ ፋኖ ድጋፍ ታደርጋላችሁ” “የጦር መሣሪያ ደብቃችኋል” “በአዲስ አበባ የሕዝብ አመፅ እንዲነሳ አድርጋችዋል“በሚል ምክንያት ለግፍ እስር ተዳርገዋል፡፡

➣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎችን በመተው ፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝና መከሰስ ልዩ መብትን (Immunity) በጣሰ መልኩ አምስት የሕዝብ እንደራሲዎች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

➣ የአማራ ተወላጅ ዜጎች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በአማራነታቸው ብቻ በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እስካሁን እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡

➣ በደቡብ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ግቢ (በተለምዶ አፖስቶ በመባል የሚታወቀው ቦታ)፣በአዋሽ አርባ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ፣ አዲስ አበባ የሚገኙ እስር ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች፣ በአማራ ክልል የሚገኙ እስር ቤቶች እና የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች የንፁሐን ማጎሪያ መሆናቸው የታወቃል፡፡

በአማራ ክልል አገዛዙ በአዋጅ ታግዞ በከፈተው ጦርነት በከባድ መሣሪያ ተኩስ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል በመንገድና በእርሻ ሥራ ላይ እንዲሁም በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጭምር የሚገኙ መሆኑን ቤተሰቦች እና የዐይን ምስክሮችን ዋቢ በማድረግ ባልደራስ ለአውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል።

 በርሀብ እያለቀ ስለሚገኘው ህዝብ

ከብልፅግና ሰራሹ ጦርነት በተጨማሪ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ብቻ ከ4 በመቶ በላይ ዜጎች በረሀብ አልቀዋል፣ በማለቅም ላይ ይገኛሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን ዓለም አቀፍ ተቋማት ይፋ አድርገዋል። በተባበሩት መንግስታት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በረሀብ አደጋ ላይ ካሉ ስድስት ሀገራት መካከል ውስጥ ትገኛለች። የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያሳየው ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ፈላጊ ናቸው፡፡ በርሀቡ ምክንያት በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግስት መር ጦርነት እና ድርቅ ሳቢያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አካባቢያቸው ለቀው ተሰደዋል። በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የቁም እንስሳት በድርቅ ሳቢያ አልቀዋል። ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች በተጨማሪም የተወሰኑ የኦሮሚያ እና ሱማሌ አካባቢዎች ከባድ የረሀብ አደጋ የተከሰተባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሀብ እና ጦርነት እያለቀ ባለበት ሰዓት የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት በቅርቡ በሀገረ ጣሊያን የ FAO Agricola award መረከባቸው ተሰምቷል። ከ20 ሚሊዮን በላይ እርዳታ ፈላጊ ሕዝብ ያላት ሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር ለሆኑት አብይ አህመድ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ እህል ላጠራት አገር ከአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ሽልማት መበርከቱ ትልቁ የአመቱ የፖለቲካ ስላቅ መሆኑን ለመረዳት አይከብድም። የሰላም ኖቤል በተሸለሙ ማግስት ኢትዮጵያን የባሩድ ማራገፍያ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር፤ የአምራችነት ሽልማት ሲሰጣቸው በሚሊዮኖች እልቂት ማላገጥ እንደሆነ አድርጎ ማየት ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥር 28/2016 አ ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ” በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አንድም ሰዉ በርሃብ አልሞተም“ ብለዉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠበቂ ተቋም ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ለአማራና ትግራይ ክልሎች ብቻ በድምሩ አራት መቶ ሰዎች መሞታቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከ1977 ዓ.ም በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ ተከስቷል፤ “በትግራይ ረሀብና ሞት እያንዣበበ ነው” ማለቱ አይዘነጋም፡፡

በመሆኑም ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ለሚመለከታቸው አካላት የሚከተሉትን ነጥቦች ማሳሳብ ይወዳል፡፡
1. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም፤

2. በግዴለሽነት እና በበቀል ስሜት ንፀሐንን የገደሉ እና የአስገደሉ የአገዛዙ ሀይሎች እና ሹመኞች አንድም ሳይቀር ለፍርድ እንዲቀርቡ፤

3. በረሀብ አለንጋ እየተገረፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓለም አቀፍ ትኩረት ተሰጥቶት፣ ሕዝቡ ከሞት እንዲተርፍ አገረአቀፍ እና አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ትብብራቸዉን እንዳይነፍጉ፤

4. የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውሳኔ በአስቸኳይ እንዲሻር ፓርቲያችን በጥብቅ ያሳስባል።

5. የኦሕዴድ ብልፅግና መንግስት የደረሰ ሰብልን በማቃጠል እና የእርዳታ እህል ለተረጅዎች እንዳይደርስ በማድረግ ረሀብን የጦርነት መሳሪያ ከማድረግ እንዲታቀብ፡፡

የነገድ ፖለቲካ ስርዓት ጊዜ ባገኘ ቁጥር የሕዝብ ደም እያፈሰሰ የሚቀጥል መሆኑ በመረጋገጡ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን አጠናክሮ በሰላማዊ ህዝባዊ እምቢተኝነት የትገል ስልት በመጠቀም ሃገሩን መታደግ እንዳለበት እናሳስባለን፡፡

የባልደራስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ጥር 29/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Filed in: Amharic