>

‹‹የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኮስም!!!›

‹የቆላ አጋዘን የገደለ መቶ ከብት ወይም ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፍል አባ ገዳዎች ወሰኑ፡፡››

‹‹የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኮስም!!!›› Do not use a cannon to kill a mosquito. 

  ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

‹‹ወጡ ሳይወጠወጥ

ወስከንባው ላይ ቁጢጥ!!!››

‹‹ በዚያም ወራት በግንቦት አስር ቀነ በ1901 ዓመተ ምህረት ዳግማዊ ምኒልክ ሰፊ በሆነችው አደባባይ በጃንሜዳ ጉባዔ አደረገ፡፡ አዛውንቱን፣ መንንቱን፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ሁሉ ሰበሰበ፡፡ እንዲህም አላቸው፡- በአፄ ቴዎድሮስ ሞት ጊዜ የተደረገውን ልንገራችሁ ስሙኝ፡፡ አንዱ ሁለተኛውን እየገፋው፣ ሁለተኛው ሦስተኛውን እየገፋው ሠራዊቱ ሁሉ አለቁ፡፡ ከእነርሱም አንድ አልቀረ፡፡ በአፄ ዮሐንስ ሞት ጊዜም በየሀገሩ የሆነውን  አይታችኃል፤ ይልቁንም በትግሬ ምድር፡፡ በሀገራቸው ህመም /በሽታ/ ሳይገባ፣ጠላትም ሳይመጣባቸው ሁሉም እርስ በእርሳቸው አለቁ፡፡ ይህ ሁሉ እንዳይሆንባቸው ሁላችሁም በፍፁም ልባችሁ ተዋደዱ፡፡ ፍቅር ሁሉንም በደሎች ይደመስሳልና፡፡ አነዱ የሌላውን ሹመት አይመኝም፡፡ ለእርሱ በተሰጠው ይፀናል እንጂ፡፡ እርስ በእርሳችሁም አትቀናኑ፣ ቅንዓት የብዙዎችን ልብ በቁጣ ትበላዋለችና፡፡ በቅናትም የእግዚአብሔር ፀጋ አይገኝም፡፡ ልጄን አደራ ሰጥቻችኃለሁ፣ ፈቃዳችሁን ቢያደርግ ከእርሱ ጋር ኑሩ፡፡ ፈቃዳችሁን ባያደርግ፣ ምክራችሁን ባይሰማ ግን ወደ ውጭ አውጡት፤ እኔ ንቄዋለሁ፣ እንደ ጉድፍ ጥራጊም ጥየዋለሁና፡፡››….(1) 

‹‹የቆላ አጋዘን የገደለ መቶ ከብት ወይም ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፍል አባ ገዳዎች ወሰኑ፡፡›› አዲስ አበባ ግንቦት 16 ቀን 2013 ኤፍ ቢሲ (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) አማራ በማንነቱ የተነሳ፣ በእምነቱ የተነሳ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” እና ‹መጤ/ ሠፋሪ› በሚል የጥላቻ ትርክት ተገድለዋል፣ ታርደዋል፣ ተቃጥለዋል፡፡ ይህ ግፍ ዛሬም አልቆመም፡፡ የኦሮሞ አባገዳዎች አማራ እንዳይገደል በይፋ ያሉት ነገር የለም፡፡ የኦሮሞ አባገዳ አጋዘን እንዳይገደል ሲሞገት፣ ለምን በኦሮሞ ምድር አማራ እንዳይገደል አልተማፀነም? ለምን  የኦሮሞ ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች አላወገዙም? ለምን  የክልል መንግሥቶች ይህን ገደላ አላወገዙም?   ዛሬም የአማራ ልጆች መገንዘብ የሚገባቸው በዚህ የአማራ የህልውና ትግል  አማራ ከእንሰሳ ያነሰ ዋጋ እንደተሰጠው በመረዳት ትግላችንን ምንም ሳንከፋፈል በህብረት በወንድማማችነት ከመቀጠል ሌላ ለክፍፍል ቦታ መስጠት አይገባን እንላለን፡፡  የአማራን ህዝብ ከኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የሰው አልባ ድሮውን ጥቃት ሳናስጥለው፣ በመራዊ በግፍ ተረሽነው በየመንገዱ ለተጣሉት የአማራዎች ደም ሳይደርቅ፣ የአማራ ገድለው በጅምላ መቃብር በግሬደር ለተቀበሩት ረስተን፣ የተቃጠሉትን የታረዱትን አማራዎችቤቱ ይቁጠራቸው ብለን፣ የሴቶችን መደፈር ሳናስቆም፣ የአማራ ፋኖ ለበትረ ሥልጣን ሳይደርስ ለሥልጣን ተጣላ ቢባል አባቶች ምንኛ ያዝናሉ! ‹‹ወጡ ሳይወጠወጥ፣ ወስከንባው ላይ ቁጢጥ ›› ከማለት በስተቀር፣ ለቅሶችን ከመቼው ተረሳ! ሐዘናችን ከመቼው ተረሳና! እግዚአብሔር ልብ ይስጠን!!! 

የኮነሬል አብይ አህመድ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት መር ሽብርተኛነት በአማራ ህዝብ ላይ

‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ›  በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኔ :-   ሙሉውን ለማንበብ እባክዎ ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።   ⇒ ‹‹የወባ ትንኝ ለመግደል መድፍ አይተኮስም!!!› 

Filed in: Amharic