>
5:30 pm - Sunday November 1, 3108

ያንተን ስም ደልዘው የነሱን ሊፅፉ ..?

ያንተን ስም ደልዘው የነሱን ሊፅፉ ..? አንተን መሆን ቢያቅታቸውና ቢከብዳቸው .. እነሱ ተገልጥው አንተን ሊከልሉህ .. እነሱ ከፍ ብለው አንተን ዝቅ ሊያደርጉህ አሰቡ .. ! እንዴት ይሆናል ይሄ ..?

እውነት ይካዳል እንዴ ..?!

ነፃነት ይቀማል ወይ ..?!

ምልክት ይሸፈናል እንዴ?!

ፍቅር ይነጠቃል ወይ ..?!

አፍ አውጥቶ ይመሰክራል እኮ .. አንተን የሰበአዊነት ተምሳሌት የመልካም ነገር ሁሉ መገለጫ የመለአክ አምሳያ የሆንክን ሰው አፋቸው ውስጥ አስገብተው ሲያላምጡህ እንዴት አፋቸውስ ታዘዘላቸው ..? አማራዎች ሆነው የአንትን ስም በክፉ ካነሱ እውነት አማራ ተረግሟል .. ይብላኝ ለነሱ እንጂ አንተ’ማ ግዙፍ የሆነው አምላክህ ሳያንቀላፋ ሲጠብቅህ ውሎ ሲጠብቅህ ያድራል ..!

ጠላቶች ሁሉ ማንም ሳይነካቸው ተሰባብረው ሲጠፉ አይተናል ..! አሁንም ይጠፋሉ ..!!!

ያንተን ስም ደልዘው የነሱን ሊፅፉ ..?! ማሪያምን አይቻላቸውም።!

 የአንተን የተባረከ መንገድ በመምረጤ ፈጣሪዬ ምን ያክል እንደሚወደኝ አውቄያለሁ!!!

@LiyuFkir
Filed in: Amharic