የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲህ ያሉ መሸጦዎችን ካላራገፈ የትም አይደርስም።
ኢሀፓ፣ ቀስተ ደመና፣ ቅንጅት፣ ግንቦት7፣ አርበኞች ግ7፣ ኢዜማ፣ ብልፅግና ወተረፈ…
”ፕሮፌሰር ብረሀኑ ነጋ ነክተውት የማይፈርስ ነገር የለም” የሚባልላቸው ፓለቲከኛ እንደብዙዎች ምስለኔ ተቃዋሚዎች ጡረታ ሚባል ያሳለፉትን የህይወት ተሞክሮ የሚዳሱስበት፣ እረፍትንም የሚያጣጥሙበት ነገር እንዳለ ማየት የሚፈልጉ አይመስልም። ፓርቲ መመስርት ፤የሱም ሊቀመንበርነቱን ማንም አይንካብኝ ማለት። ካልተሳካ በግራ ፓለቲካ ሴራ እየጎነጎኑና በደጋፊዎቻቸው በሚሰነዘር የስማ ማጥፋት አራክሶ መሪዎችን ከድርጅቱ ማስወጣት። ቀስ እየሉ የድርጅቱን እስትንፋስ መቁረጥ ይህ ሰውየው ከሚታወቁበት በጣም ጥቂቱ ነው።
ከአሲምባ እስከ አዲስ አበባ ከዋሽንግተን እስከ የኤርትራ በረሀ ሲያቦኩት የኖሩት መርዛማ ፓለቲካ ይሄው ነው። በእድሜ 70 ቢደፍኑም በትምህርቱም እስከ ፕሮፌሰርነት መአረግ ቢዘልቁም፣ ባለፀጋ አባታቸው ነጋ ቦንገር እየተጠቀሱ የቁስ ሰቀቀን እንደማይነካካቸው ቢወሳላቸውም ግን ከተራ መሸጦነት አልዘለሉም። የኢትዮጵያ ፓለቲካም እነዚህን ዓይነት መሸጦዎችን ካላራገፈ ስርየትን አያገኝም። የትም አይደርስምም!!
@LeulA4