>
5:16 pm - Wednesday May 24, 0333

ወያኔ አለማጣ ገባ፤ ተውት ይግባ!

ወያኔ አለማጣ ገባ፤ ተውት ይግባ!

ጠላትህ ራሱን እያጠፋ ስታየው አታውከው።

“Never interfere with your enemy while he is in the process of destroying himself.”

(ናፖሊዮን ቦናፓርት፣ Napoleon Bonaparte)

መስፍን አረጋ

 

 

ወያኔ ወደ ሞቱ እየገሰገሰ ያለ ሟች ድርጅት ነው።  እንዳገሳገሱ ደግሞ እንደ ድርጅት ግብአተ መሬቱ በቅርቡ መፈጸሙ አይቀሬ ነው።  እንደ ድርጅት ከሞተ በኋላ ደግሞ ልክ እንደ ኢሕአፓ አባላቱ እየተንጠባጠቡ ሙተው እስከሚያልቁ ድረስ አለሁ ለማለት ያህል ብቻ በየጊዜው መግለጫ እያወጣ መንገታገቱን ይቀጥላል።  ኦነግም እየተከተለ ያለው ያስተማሪውን የወያኔን መንገድ ስለሆነ፣ ዕጣውም የወያኔ ዕጣ ነው።  ስለዚህም መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ የሆነው ያማራ ሕዝብ ትግል ዋና ዓላማ እነዚህ ወያኔና ኦነግ የሚባሉ ይዞ ሟች ድርጅቶች አማራን ጨፍጭፈው ጦቢያን ይዘው ሳይሞቱ በፊት እንደ ድርጅት የሚሞቱበትን ቀን በተቻለ መጠን ማፋጠን ነው።      

የወያኔ የሞት ሂደት ብሎ በይፋ የጀመረው የወያኔ አመራሮች (የራሳቸውን ጓዶች ካስገደሉና በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችን ካስጨፈጨፉ በኋላ) አዲሳባ ሂደው፣ ከጭራቅ አሕመድ ጎን ተቀምጠው በቴሌቪዥን መስኮት የታዩ ዕለት ነው።  ከዚያች ዕለት ጀምሮ ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ያለው ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።  ለዚህ ደግሞ ለየካቲት ገለመሌ የሚባለው (ለወትሮው የከበሮ ድምጽ በታዳሚ የተጨናነቀን አዳራሽ ግድግዳ ይነቀንቅ የነበረበት) የወያኔ ምሥረታ በዓል፣ ዘንድሮ ግን ጥቂቶች ብቻ ታድመውበት፣ ከመቆየት ብዛት ጨርሶ ሊረሳ የተቃረበ 49 የሙት ዓመት መስሎ ጭር ብሎ ማለፉን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።  

ሐበሻን ከምድረገጽ ሊያጠፋ ቆርጦ ከተነሳው ከጭራቅ አሕመድ ጋር የሚሞዳሞደውን ወያኔን አሁንም የሚደግፍ የትግሬ ሰው ካለ፣ ሰውየው ወይ በወያኔ ዘረፋ የተጠቀመ ዘራፊ ወይም ደግሞ ወያኔ በየዕለቱ ይገተው በነበረው ፀራማራ ትርክት የሰከረና ስካሩ አሁንም ድረስ ያልበረደለት ሰካራም መሆን አለበት።  ወያኔ ያማራን ክልል ዳግመኛ ለመውረር የተነሳበት አንደኛው ምክኒያት ደግሞ የነዚህን በፀራማራ ትርክት የሰከሩ፣ በዝቅተኝነት ስሜት የታወሩ ደጋፊወቹን ሞራል ለመገንባት ነው። 

ወያኔ ያማራን ክልል ለመውረር በድጋሚ የተነሳበት ሌላኛው ምክኒያቱ ደግሞ ከኦነግ ጋር በመተባበር እድሜውን ለማርዘም ነው።  የወያኔ ሂወት የተንጠለጠለችው በኦነግ ገመድ ላይ ስለሆነ የኦነግ ገመድ ሲበጠስ ወያኔ ተፈጥፍጦ ይሞታል።  በሌላ አነጋገር ወያኔ ራሱን በራሱ የኦነግ ተለጣፊ ድርጅት ስላደረገ፣ ወያኔን እንደ ድርጅት ለመግደል የሚያስፈልገው ኦነግን እንደ ድርጅት መግደል ብቻ ነው።  ስለዚህም ያማራ ፋኖ ሙሉ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት ጭራቅ አሕመድን አስወግዶ አራት ኪሎን በመቆጣጠር ላይ ነው፣ አራት ኪሎን መቆጣጠር ማለት ሁለቱን ፀራማሮች ኦነግንና ወያኔ ባንድ ዲንጋ መግደል ማለት ነውና።  

ባለፈው ወረራው ያማራን ሕዝብ ፍዳ እያስበላ ሐብትና ንብረቱን ያወደመውና የዘረፈው ያማራ ሕዝብ ዘላለማዊ ጠላት የሆነው ወያኔ እንደገና ተመለሶ አለማጣን ወይም ሌላ ያማራ ከተማን ቢይዝ ጠላት ወረዳ ዘው ብሎ ገባ ማለት ስለሆነ፣ ውጤቱ አማራን አሸነፍኩ ብሎ ባማራ ጥላቻ የሰከሩትን ጥቂት ደጋፊወቹን እያስጨፈረ የራሱን ሞት ማፋጠን ብቻ ነው፣ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነውና  በተጨማሪ ደግሞ ያማራ ሕዝብ ባሁኑ ጊዜ በደንብ ስለታጠቀና ቀንደኛ ጠላቱን ወያኔን በደንብ ስላወቀ ወያኔ የቱንም ያማራ ከተማ ቢቆጣጠር፣ ያማራን ሕዝብ እንደ ቀድሞው በቀላሉ ሊጨፈጨፈው፣ ልጆቹን ሊደፍር፣ ንብረቱን ሊያውድም፣ ሐብቱን ሊዘርፍ አይችልም።  

አብዛኛው የትግሬ ሕዝብ ደግሞ (ይህን ሁሉ መከራ ያወረደበትን) ወያኔን ቢደግፈውም የሚደግፈው አማራጭ ስላጣ ብቻ በመሆኑና በሙሉ ልቡ ስላልሆነ ባሁኑ የድጋሚ ወረራ ወያኔ ሊያሰልፈው የሚችለው ሠራዊት ቁጥሩ የመነመነ፣ ወኔው የደበነ የውሻ ሞት የሚሞት ደመ ከልብ ሠራዊት ነው።  የወያኔ ሠራዊት አዝማች የጻድቃን ገብረተንሳይ አንድና ብቸኛ ችሎታ ደግሞ ሠራዊቱን ፈንጅ እያስረገጠና እያስጨፈጨፈ የሚያልቅው አልቆ የቀረው ወደፊት እንዲገፋ ማድረግ ብቻ ስለሆነ፣ ፈንጅ ረጋጭ ካጣ ምንም አያመጣ  

ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሆይ ትንሹ ጅብ ወያኔ የትም ገባ የትም ለጊዜው ንቀህ ተወውና ሙሉ ትኩረትህን በትልቁ ጅብ በኦነግ ላይ አድርግ፣ ትንሹ ጅብ ሂወቱን እያራዘመ ያለው ትልቁ ጅብ ዋናውን ሥጋ በልቶ በሚያስቅርለት ቁሪሳ ነውና። ወደ ትልቁ ጅብ የምታደርገውን ግስገሳ ትንሹ ጅብ ከኋላ ሁኖ እያወከ ከበጠበጠህ ደግሞ ብዙ ጦር ሳትመድብለት ስልታዊ መከላከል በማድረግ ተመልሶ ወዳማይወጣበት ቀጠና እየሳብከው ለጊዜው አቆየው።            

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic