>

ትላንትናም ዛሬም ወላጆቼ በቁሳቁስ የሚታለሉ አይደሉም!

ትላንትናም ዛሬም ወላጆቼ በቁሳቁስ የሚታለሉ አይደሉም!

ዶር ትእግሥት መንግሥቱ ኃ /ማርያም
አሁን ሃገራችን ባለችበት አስቸጋሪ ጊዜ እንደዚህ አይነት ግለሰብዊነት ጉዳይ ውስጥ ባልገባ እወድ ነበር :: ነገር ግን ውሸት ሲደጋጋም እውነት ይሆናል ይባላል:: ወይም ነገርን ሰምቶ ሰዉ ዝም ካለ ተሰማምቷል ማለት ነው ተብሎ ይወሰድበታል :: በመሆኑም የሚመራውን ውሸት ለማስተካከል ወስኛለሁ:: 
 ልጅ ሆኜ ስለ አባቴ ውሸት ሲወራ፤ አባቴን ” ለምን መልስ አትስጥም?” ስለዉ
 የሚሰጠኝ መልስ :-
 ” የኢትዮጲያ ህዝብ ማን መሆኔን ያውቃል ስራዬ ይመስክራል መናገር አያስፈልገኝም” ነበር የሚለኝ። አሁን ግን ሳየው ምናልባት አንዳንዴ መናገር ያስፈልግ ነበር የሚለው ሃሳብን አምኜበታለሁ::
ሁሉን ሃጥያት ወስዶ መንግስቱ ሃይለማርያም ላይ መዘፍዘፍ ፋሽን በሆነበት ዘመን አብረውት 17 ዓመት አጠገቡ ቁጭ ብለዉ ሲያሽቃብጡ የነበሩ ዓላማ ቢስ ውሸታሞች  ዛሬ የጡረታ ገንዘባቸውን ለማግኘት ህሊናቸውን ለመሸጥ እንደገና መዘጋጀታቸውን ሳይ አዝናለሁ::
 በመፅሃፋቸው እንደሚነግሩን ባላመኑበት አላማ 17 አመት ህሊናቸውን ሽጠው ኖረው ዛሬ ደሞ ውሸት ሲሸጡልን ትንሽ እንኳን ህሊናቸውን አይቆረቁራቸውም:: እንደዚህ አይነት የቀድሞ ባለስልጣናት የማይገባቸው ነገር ቢኖር እየሰደቡ ያሉት መንግስቱ ኃይለማርምን ሳይሆን ራሳቸውን መሆኑ ነው::
 እንዴት ያላመናችሁበትን ዓላማ 17 ዓመት ሙሉ አገለገላችሁ:: ከእናንተ ይልቅ አንደኛውን ጠላት ሆነው ላመኑበት ዓላማ ለታገሉት ሰዎች የበለጠ ክብር አለኝ;;
ፋሲካ ሲደልል በፍፁም ማስረጃ በሌለው ሁኔታ አባቴን ሲከሱ አዝናለሁ ::
 ፋሲካ ከስራ ግንኙነት በላይ ከአባቴ ጋር ቴኒስ የሚያዘወትሩ ሰዉ ነበሩ:: ሃብትና ቁሳቀስ ወደ ዚምባብዌ አሸሽቷል ማለታቸው ግን አሳፋሪ ንግግር ነው አንድ ቀን ይህንን በመፃፈቸው እንደሚያፍሩ እርግጠኛ ነኝ ::  ምክያቱም ይህ አልሆነምና:: ወላጆቼ በዚምባብዌ እርሻ የላቸውም:: ይህንን ማንም ሰዉ  ዚምባባዌ መጥቶ ሊያረጋግጥ ይችላል ::
 አባቴ ወደ ዚምባብዌ ሲመጣ እንግዳ ማረፊያ ነበር ያሳረፉ ት:: በቅኝ ግዛት ጊዜ በተሰራ ቤት ውስጥ ሳይሆን በ 1980 ዎቹ ጊዜ non-aligned movement ስብሰባ የተሰሩ ናቸው: :
‘ የተሻለ ቤት እንስጥህ’ ሲሉት ‘ግድየለም ይህ ቤት ይበቃናል ብሎ ነው የመለሰላቸው’:: ቤቱ አባቴ የገዛው አይደለም የዚምባብዌ መንግስት ንብረት ነው :: ወላጆቼ በመንግስት ደግነት ያለ ኪራይ ይኖሩበታል :: የሚያስፈልጋቸውን በሙሉ መንግስት ያቀርባል :: ሰራተኛ ጠባቂ መኪና እስከነሹፌሩ የመሳሰሉትን::
 ውባንቺ ቢሻው በ1983 ወደ ዚምባብዌ እየተመላለሰች ሃብት አሸሽታለች የሚባል ውሸት ያሳዝናል:: መጋቢት ላይ ኮሪያ ለህክምና ሄዳለች :: ከዛ ሌላ የ ዛን አመት የትም አልሄደችም አባቴ ደሞዙ 9oo ብር ነበር ::
የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳልያ ስለተሸለመ 300 ብር አለዉ :: ደሞዙን አምጥቶ በነጭ ፖስታ ለናቴ ነበር የሚሰጣት:: በልጅነታችን አንዳንድ ነገር ስንጠይቅ እናቴ ወር ጠብቁ ነበር የምትለን::
የሚያዛቸው ሚኒስተሮችና ጀነራሎች የሚመስዱትን ያህል ደሞዝ እንኳን በፍቃዱ ነው አያስፈልገኝም ብሎ የተወው::
 ሰዉ ለማለት እንደፈልገው ቤተሰቡን አስወጥቶ ሄደ አይደለም መንግስቱ ሃይለማርያምን ወደዳችሁትም ጠላችሁትም የማይሽር አንድ ሃቅ አለ በ1983 ሸንጎ ብዙ ንግግሮች ሰምተናል ::
እስከዛሬ በዩቱብ ተቀርፀው ይገኛሉ:: ያ ስብሰባ የተጠራበትም የሱም ንግግር ለዘላለም ተቀረፆ ይኖራል:: ታማኝነቴ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው ብሎ ነበር:: “የኢትዮጵያ ህዝብና የአንድነት ሃይሎች በዚህ ትውልድ ዘመን ኢትዮጵያን ለጠላቶቿ አሳልፈው እንደማይስጧት ተስፋ አደርጋለሁ” ብሎ ነበር
 ሽንጎው ራሱን አፍርሶ : ፕሬዝዳንቱን ሽሮ ነው የተበተነው የሽግግር መንግስት ወስኖ ነው የተበተነው ከ ጥሎ ፈረጠጠ’ የምትሉት? ” የሰዉ አይን እየገረፈኝ ገንዘብ እየለመንኩኝ አመጣለሁኝ እንጂ ‘ እንዳለው ከኢትዮጵያ ህዝብ እሱ አልዘረፈም  ደቡብ ሱዳን ና ኩዌት ን የመሳሰሉ አገራት እርዳታ አርገውለታል ::
 ትላንትናም ዛሬም ወላጆቼ በቁሳቁስ የሚታለሉ አይደሉም!  ይህ ምን ግዜም አይቀየርም
ኢትዮጵያ ትቅደም ! 
ድል ለፋኖ
Filed in: Amharic