>

ጎረቤትህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ!

ጎረቤትህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ !

መምህር ፋንታሁን ዋቄ

FILE – Secretary of State Henry Kissinger briefs reporters, Oct. 12, 1973, at the State Department in Washington. Kissinger, the diplomat with the thick glasses and gravelly voice who dominated foreign policy as the United States extricated itself from Vietnam and broke down barriers with China, died Wednesday, Nov. 29, 2023. He was 100. (AP Photo, File)

ህ የአብ እማዎቻችን አባባል ጥልቅ ትርጉምና ማስጠንቀቂያ አለው። በአገራችን በደርግ፥ በሕወሃት፥ በኦፒዲኦ/ኦነግ፥ በብልጽግና፥ በማናፍቃን፥ በጽንፈኞች በግልጽ የተከፈተው የሕዝብ ጅምላ ጭፍጨፋ የሚያካሄደው ሥርዓት በምእራባውያን ለምን ይደገፋል?

 መልሱ ቀላል ነው፦
 ✒️በሥርዓቱ እየተካሄደ የሚገኘው ምዕራባውያኑ ሉፈጥሩት ዓለመው እየሠሩበት ከሚገኘው ፐሮጄክት ጋር የሚስማማ ብቻ ሳይሆን ይህን የሚፈጽሙት የእነርሱን አጀንዳ የተሸከሙ በመሆናቸው ነው፤
 ✒️አነርሱም ኦርቶዶክስንና ነባር እሤት ያላቸውን አምንቶች፥ ባህሎች፥ ታሪካዊ አሻራዎች በማጥፋት የአንድን ሉዓላዊ አገር ልዩ ማንነት መደምሰስና እና የዓለም አገራት ሁሉ በእንርሱ (በምእራባውያን በተለይ በአሜሪካ ላይ) ጥገኛ ማድረግ፥ ልዕለ ኃያልነታቸውን በማስጠበቅ በቅኝ የዓለም ሕዝቦችን ባርያ፥ ሀብታቸውን የግላቸው የማድረግ ግብ አስቀምጠው የዘመቱ ናቸው!
 ✒️ በራሱ የሚተማመንና በራሱ መንግድ የሚለማና ከጥገኝነት ነጻ ሆኖ የሚለማ አንድም አገር በዓለም ላይ ማየት አይፈልጉም! ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ብቻ የፈጸሙትን ብንመለከት፦
 ✒️ ቼኮዝላቫኪያን አፈረሱ
✒️ ሰርቢያን አወደሙ
✒️ ሶሪያን አመሰቃቀሉ
 ✒️ ሊቢያን ከአገርነት ውጭ አደረጓት
✒️ ኢራቅና ኢራንን አባልተው በመጨረሻ ራሳቸው መጥው አፈረሷት
✒️ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ኤርትራን አገር አደረጉ
✒️ወያኔና ኦነግን በባላ ደግፈው መንግሥት አደረጉ
✒️ዩክሬንን መረማመጃ እድረገው ራሸያን ላፍረስ አንጡራ ሀብታቸውን እያፈሰሱ ነው
✒️ የዓለምን የምግብ ምንጭና መሠረት የሰብልና የእንስሳትን ዘርያ ዘረ መል በሰውሰራሽ በመቀየር መቆጣጠር በትጋት መያዛቸው
 ✒️ ዛሬ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሚያርደውንና የሚሳርደውን ብልጽግና፥ ኦርቶዶክሳውያንን በማፋጀትና ከእምነት በማስወጣት የሚየዓወቀውን ሕወሃትን እስከነ ወንጀላቸው እያስተባበሩ፥ እያስታረቁ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚደረገውን ግልጽና ሰውር የማጥፋት ጥፋታቸውን ቀጥለዋል። የትግራይ ሕዝብ ከእምነት እንዲወጣ፥ የኦሮሞ ሕዝብ ኦርቶዶክሳዊነቱን አንዲጥል፥ የአማራ ሕዝብ እንዲያልቅ ግልጽ ድጋፍ በሚኣሰኝ ደረጃ አጥፊዎችን ሲንከባከቡኡና ለህልውናቸው የሚራወጡት ሲያጣጥሉ ማየት በቂ ምልክት ነው።
 ✒️ ፊደል፥ ቋንቋ፥ ቅርሥ፥ ከተማ፥ ኪነ ጥበብ፥ እምነት ወዘተ ዒላማ የተደረገውና ለሕወሃት ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የግዕዝ ፊደልን ከኢትዮጵያ ማጥፋት ካልተቻለ ከአብዛኛው አካባቢ ማሰወጣ እንዲችል የለገሱት ምዕራባውያን ናቸው። ግን ለምን? ፖለቲሲያቸው ይህ ነው
👉🏿 የአሜሪካንንና የአውሮፓን የፖለቲካ አስተሳሰብ እጅጉን የዘወረው እና ዛሬም በዋና ዋና የምእራባውያን የውጭ ግኑኝነት ፖሊሲን የቀረጸው ሄንሪ ኪሲነጀር በአንድ የ1974 በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገለት የሽልማት ስነ ሥርዓት ላይ (ምንጩ፦ በ1997 የታተመ ዕለታዊ የቱርክ Turkish Daily News Nemesis magazine የተባለ ጋዜጣ ነው)
 👉🏿“የግሪክ ሕዝብ ለመግራት የሚያስቸግር ሕገወጥና አናርኪሰት ነው፥ Greek people are anarchic and difficult to tame.)” “ስለዚህም የባህከቻው ጥልቅ መሠረት መመታት አለበት፦
 👉🏿እናም በእኛ ፈቃድ ጋር ምናልባት እንዲጓዙ ማስገደድ ይቻላል። (“Fo this reason we must strike deep into their cultural roots: Perhaps then we can force them to conform.)። “ምን ማለቴ ነው ቋንቋቸው፥ ሃይማኖታቸው [ኦርቶዶክስ ክርስትና]፥ ባህላቸውና ታሪካዊ ጸጋዎቻቸው ሲመታ ወይንም ከመሠረቱ ሲነቀል ከሌላው የሚለዩበትን ምልክት [ስነ ልቦና፥ እምነት፥ ታሪክ፥ ስነ መንግሥት፥ ባህል ) እንሰብራለን፤
 👉🏿ግሪኮች እነዚህን ሲያጡ በራሳቸው ቆመው መልማትና ማደግ እንዳይችሉ ሽባ እናደርጋቸዋለን፤ ከዚያም የባልካን፥ የሚዴቴራንያን፥ የመካከለኛው ሥራቅ አገሮችን ለመከፋፈልና ለማሳነስ ለዘረጋነው ስትራተጂና እቅድ እንቅፋት መሆን አይችሉም።
 (I mean, of course, to strike at their language, their religion, their cultural and historical reserves, so that we can neutralize their ability to develop, to distinguish themselves, or to prevail; thereby removing them as an obstacle to our strategically vital plans in the Balkans, the Mediterranean, and the Middle East,” he allegedly said.)
 ይህ እውነት እያወቁ ከባእዳን ተልእኮ ተቀብሎ የገዛ ሕዝባቸውን በተለይ መእመናን ለማጥፋት የተላከውን የብልጽግና መንግሥት እያመሰገኑና ምእመናን እያዘናጉ የቀጠሉት ጳጳሳት ምንኛ የሕዝብ ጠላት፥ የሆድ ሎሌዎች ይሆኑ?
Filed in: Amharic