ሰረቀች ከተባለው መኪና በላይ የመግዛት አቅም ያላቸው ሚሊየነር አባት አሏት።
ዶር ሰለሞን አማረ

መና ከበደ ትባላለች። እኔ እማውቃት ከሦስት ዓመት በፊት እንግሊዝ ሀገር እማውቃት አክስቷ ጋር እኔ እምሰጠውን አገልግሎት ለአባቷ አቶ ከበደ ለማግኝት እኔ ጋር ሲመጡ ነበር።
አባቷ አቶ ከበደ ከወጣትነት እስከ አሁን እስካሉበት እድሜያቸው ድረስ ታታሪ ሰራተኛ እና በሚልየን የሚገመት ሀብት እንዳፈሩ አጫውተውኛል። በተለይ ( መኪና ሰረቀች ) ስለተባለችው ልጃቸው ” መና ” ሲያወሩኝ፣ እጅግ የሚተማመኑባት፣በትምህርት ጥሩ ደረጃ ደርሳላቸው ከባህርዳር ዩኒበርስቲ እንደተመረቀችላቸውና በገዙላት መኖርያ ቤት ምንም ሳይጎድልባት የሚያኖሯት የሚወዷት ልጃቸው እንደሆነች አጫውተኛል።
እኔም እንዳየሁት ከሆነ ” መና ” በጥሩ ስነ-ምግባር ያደገች፣ ጉዳት የደረሰባቸውን አባቷን እምትንለባከብ ምንም ሳይጎድልባት በጥሩ ሁኔታ ያሳደጓት እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ።
ከዚህ ሁኔታ አኳያ እንኳን ሰረቀች የተባለውን መኪና ልትሰርቅ ይቅርና፣ ሰረቀች ከተባለው ” ቪትስ ” መኪና በላይ ሊኖራት ወይም ሊገዙላት የሚችሉ ታታሪ ጎበዝ፣ እና ጉዳት ያላሸነፋቸው አባት እንዳሏት ልመሰክር እችላለሁ።
ይሁንና ጠንካራ እና ታታሪ አባትሽን፣ ወንድምሽን እና እንቺን በቅርበት እማውቃችሁ እኔ ” ሰሎሞን አማረ” ስለ አንቺና ስለቤተሰቦቻችሁ ንፁህነት ስመሰክር ታላቅ ኩራት ይሰማኛል።
ስለሆነም አይዞሽ በርቺ ጠንክሪ በርቺ ለማለት እወዳለሁ።
ውድ ወንድምሽ ሰሎሞን አማረ።
ምንጭ ⇓
ሞዐ ሚዲያ