>

10 የፋኖ ድሎች!

10 የፋኖ ድሎች!

 1. በብርቱ ክንዱ በአገዛዙ ሚዲያ ፋኖ በሚለው ሐቀኛ ስሙ እንዲጠራ አስገድዷል።
 2.አገዛዙን 3 ክላሽ ይዘው 3 ቀን አይዋጉም ከማለት እባካችሁ እንደራደር ወደ ማለት አምዘግዝጎ አውርዶታል።
 3.በአንድ ቀን ብቻ ከ22 በላይ ዐውደ ውጊያዎች መምራት የሚችል ቁመና እና ንጥር ወታደራዊ የአመራር ጥበብ እና ክኂል ተላብሷል። በመዋጋት ብቻ ሳይኾን በመማረከ፤ ድል በመቀዳጀት።
 4. ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው እንዲሉ አገዛዙ ጦር ሜዳ ላይ ሲጠዘጠዝ በወሬ ፋኖን ለመከፋፈል ብዙ ርቀት እንዲጓዝ አስገድዷል።
 5.ከባዶ እጅ፣ ከጥቂት ኋላ ቀር እንዲሁም ከጥቂት ክላሽ ተነሥቶ እስከ ሞርታርና ዲሽቃ ከአገዛዙ በተረከበው የምርኮ በረከት ተምነሽንሿል።
 6.በዐማራ ሰማይ ሥር የገጠር አስተዳደሩን ከ75 በመቶ በላይ የሚኾነውን ተቆጣጥሮ ያስተዳድራል። ከተሞችን ለስልቱ ሲል ክፍት አድርጎ ይንቀሳቀሳል።
 7. ለህዝቡና ለተነሳለት ዓላማ ባለው ቁርጠኝነት እንዲሁ መንግስትን ያኮረፈ አማጺ ቡድን ሳይሆን ህዛብዊ ሀይል መሆኑን በምርኮኛ አያያዙ ፤ የህዝብን የአገልግሎት ተቋማት ባንክን ጨምሮ በመከላከል አሳይቷል፡፡
 8. አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከተበጣጠሰ የህዝብ ቁጣ ቅርጽ ወዳለው በብርጌድ ፤ ክፍለ ጦር እና እዝ የተዋቀረ ጦር መስራት ችሎ አሁን አንድ ማእከላዊ እዝ ለመስረት ጫፍ ደርሷል፡፡
 9. የራስን አቅም በማስተባበር ፤ ያለምንም የውጭ ሀይሎች እገዛ እስከአፍንጫው የታጠቀን ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ማንኮታኮት እንደሚቻል ምሳሌ ሆኗል፡፡
 10.የዓመታት የተደበቀውን የአማራ ህዝብ ጉዳይ ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ አድርጎታል።
 (ዲ/ን አባይነህ ካሴ እና ሲሳይ ሙሉ ( አሞራው)
Filed in: Amharic