አንጃጃል!!!
አንድም አያስቀሩልህም (ሽም)። በመጨረሻ ግን አንተን (ቺን) ባዶ እጅህን (ሽን) አስቀርተው ሜዳ ላይ ወድቀህ(ሽ) ስትንፈራፈር(ሪ) እነሱ የተነሱለትን እኩይ ዓላማ አሳክተዋል እና ተሰብስበው ይስቃሉ።
አዎ መቼ ነው መጃጃላችንን የምናቆመው?….መቼስ ነው ከትላንቱ የምንማረው?
ለምለሙ የአማራ መሐፀን ስንት ምሁራኖችን አፈራ? መልሱ እጅግ በጣም ብዙ ብዙ ነው። ታዲያ የታሉ? ምንስ እያደረጉ ነው?

አዎ በጣር ላይ ሆና ድምፅዋ በደንብ ስላልተሰማ ነው አትልም። ምክንያቱም የጣር ጩኸትዋን የገደል ማሚቶም አስተጋብቶታል!
ችግሩ ግን ብዙዎቹ ያፈራቻቸው ምሁራኖችዋ ጆሮዋቸውን የምቾት ጥጥ ደፍኖታል፤ ከፊሎችም ምሁርነቱን አራክሰው አድርባይ ሆነዋል፤ተሽጠዋል። ከፊሎቹም ሱፍና ከረቫታቸውን ገርግደው ሚዲያ ላይ ይቀርቡና ያለህበትን(ሽበትን) ሰቆቃ የሚገልፀው ቃል ባይኖርም ባለችው በሚችሉት መጠን እንኳን ከመግለፅ ይልቅ ፖለቲካል ኮሬክሽን ለማድረግ ሲዳክሩ ትመለከታለህ፤ እርር ድብን ያደርጉሀል። ያደርጉናል።
ብሶታችንን በሚነገረው መጠን ባለመናገራቸው ከፕሮግራሙ በኋላ ሌላ ህመም ይሰጡናል።
እጅግ በጣም በጣት የሚቆጠሩትም ገፍተው ወደፊት ሲመጡ ከወዳጅ መሳይ ጠላቶችህ ጋር ሆነህ ውርጅብኝ ስለምታወርድባቸው እና የሰሩትን ሁሉ ውሀ ስለምትከልስበት የጀመሩትን ሳይጨርሱ እንኳን ተሸማቀው ወደኋላ ይሸሻሉ ። ያኔ ጠላቶችህ (ሽ )ይስቃሉ ፤ አንተ (ቺ) ግን ባዶ እጅህን (ሽን) ታጨበጭባለህ (ቢያለሽ)።
ይህችን ፅሁፍ በቁጭት እንድመነጫጭር ያስገደደኝ በተለይ ካለፉት ስድስት ዓመታት ጀምሮ እስከዛሬ እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ሲደርሱ የምሁርነት ካባን ደርቤያለሁ የሚለው ሁሉ ሁሉንም አላየሁም ሰቆቃውንም አልሰማሁም ብሎ ለሽ ባለበት ዓመታት ሀያ አራት ሰዓቱ ተቀይሮ ጭማሬ ተደረገ ወይ?? እስክንል ድረስ ሊነገር በሚገባው መጠን የዲፕሎማሲ ስራውን ጨምሮ የሚደርስበትን ውርጅብኞች ሁሉ ተቋቁሞ ታላላቅ ስራዎችን በመስራት ላይ ያለው ፕሮፌሰር ግርማ ብርሐኑ ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተወረወረ ያለው ድንጋይ ነው ፤
ጠላት እርር ድብን እያለ የሚያወርድበትን ውርጅብኝ ተቋቁሞ ታላላቅ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ተዘንግቶ እንዴት ከወዳጅ መሰል ጠላቶችህ(ሽ) ጋር አብረህ(ሽ) ወርጅብኝ ታወርድበታለህ(ታለሽ)??? ፤ ከሱ ይልቅ ላንተ(ቺ) እነሱ ተቆርቋሪ ሆነው???
እንዴት ነው ትላንት ማን ምን ሲያደርግ ፤ምን ሲል ነበር ብለህ(ሽ) ሳትጠይቅ (ቂ) ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት መጠቀሚያ ለሚያደርጉን ለታሪካዊ ጠላቶቻችን:- ለፋሽስት ወያኔ፤ ለአራጃችን ለኦነጉ አብይ አህመድ እና ለተላላኪ ካድሬዎቹ ለዩቱብ እና ለቲክቶክ ሳንቲም መልቀሚያ ጭምር ለማድረግ የዩተበሮች እና የቲክቶከሮች ማሟሟቂያ የምታደርገው(ጊው)? ፤
እንዴት ነው አሰሱንም ገሰሱንም በየግሩፕህ ( ሽ )እያስገባህ(ሽ ) ሰድበህ (ሽ )ለሰዳቢ የምትሰጠው(ጭው)???፤ ሻለቃ ዳዊትን ያሳጡን እኮ ይቅርታ ወደመጠየቁ መጥተዋል ግን ምን ዋጋ አለው ጅብ ከሄድ ውሻ ጮኸ።

ምን ለማለት ነው የአማራ መሀፀን ካፈራቻቸው በብዙ ሺ ከሚቆጠሩ ምሁራኖች ውስጥ ብቻውን የምሁርነት ግዴታውን እየተወጣ ያለ የምናከብረው እና የምንኮራበት ትልቅ ሰው ነው።
ስለዚህ ሁልጊዜ እየተጃጃልን ለጠላቶቻችን መሳቂያ መሳለቂያ አንሁን!…ዘግተን እንምከር። ጥያቄ ካለን በውስጥ እንጠያየቅ። ፕሮፌሰር ግርማ በጣም ቅን፤ ምሁር ነኝ ብሎ የማይኮፈስ ቀና እና ነፃ ሰው ነው።ስለዚህ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ በውስጥ መጠየቅ ነው። የሚታትሩልንን ምሁራኖቻችንን እንጠብቅ። እንከባከብም። አንጃጃል!!!
የሺሐረግ በቀለ