>

ፈኖተ ዘመነ ካሴ፤ የዘመነ ካሴ ብአዴናዊ መንገድ

ፈኖተ ዘመነ ካሴ፤ የዘመነ ካሴ ብአዴናዊ መንገድ

መስፍን አረጋ

 

መንደርደርያ

እነ ታምራት ላይኔ በመለስ ዜናዊ ቀጭን ትዕዛዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን) ይሰኝ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ድርጅታቸውን አፍርሰው፣ መለሰ ዜናዊ ባወጣላቸው የትግረኛ ስም ብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብእዴን) መባልን መርጠው፣ ራሳቸውን ከኢትዮጵያዊነት አውርደው አማራን እንወክላለን እያሉ፣ የፀራማራ ወያኔ ጋሻ ጃግሬ (ሲጡሩት አቤት ሲልኩት ወዴት ባይ ሎሌ) ሁነው አማራ አበሳውን አስቆጠሩት፣ መከራውን አስበሉት፣ ፍዳውን አስፈደፈዱት፣ ፈጠቁን አስፈጁት።  እነ ዘመነ ካሴ ደግሞ ያሜሪቃ (ያማራዊት ጦቢያ መሠረታዊ ጠላት) ልዩ መልእክተኛ በሆነው በሚካኢል መዶሻ (Michael Hammer) ቀጭን ትዕዛዝ፣ መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ የሚለውን ኢትዮጵያዊ መፈክር በጽኑ ተቃውመው፣ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ በማለት ራሳቸውን ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ አድርገውበብአዴን መንገድ እነጎዱ፣ ባማራ ስም ሊነግዱ ተነሱ። አንዴ ብአዴን ሁሌም ብአዴን (once a wolf always a wolf)   

መለስ ዜናዊ ታምራት ላይኔን አላምጦ ሲጨርስ እንደተፋው ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድም ዘመነ ካሴን አላምጦ ሲጨርስ እንደሚተፋው አስቀድሞ ለመናገር ነብይ መሆንን አይጠይቅም።  የታምራት ላይኔ መጨረሻ የስኳር ሌባ ተብሎ ወህኒ መውርወር እንደነበረ ሁሉ፣ የዘመነ ካሴም መጨረሻ የጤፍ ሌባ ተብሎ ወህኒ መወርወር መሆኑን ከወዲሁ መገመት ይቻላል።  የዘመነ ካሴን ሞት እጅግ አደገኛ የሚያደርገው ግን ዘመነ ካሴ የተነሳው የፋኖ ዋና መሪ ሁኖ ፋኖንና አማራ ይዞ ለመሞት መሆኑ ነው፣ የጭራቅ አሕመድ ዋና ዓላማ ያማራ መድሕን የሆነውን ፋኖን በማጥፋት አማራን ከምድረ ገጽ ማጥፋት ነውና።              

ሙሉ ጥንካሬው አውሬነቱ ብቻ የሆነው፣ ጨለማን ተላብሶ ተከላካይ አልባ ሰላማዊ ሰወችን ከማረድና ከማወራርድ በስተቀር በታሪኩ አንድም ጊዜ እንኳን ፊት ለፊት ተዋግቶም ሆነ ድል አድርጎ የማያውቀው፣ የጦቢያን የመንግስት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ባይቆጣጠርና የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ የሸዋ ፋኖ ብቻ ደምጥማጡን ሊያጠፋው የሚችለው ሙትቻው ኦነግ ኢትዮጵያን በኦሮሙማ መልክ እሰራታለሁ እያለ ሲፎክርና ሲደነፋ፣ ኢትዮጵያን በደምና ባጥንቱ የገነባትንና ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ጠብቆ ያቆያትን፣ በጀግንነቱ ወደር የሌለውን፣ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረውን፣ ጎጠኝነትን የሚጸየፈውን፣ የሕዝብ ቁጥሩ የኦሮሞ ስም ስለተለጠፈበት ብቻ ኦሮሞ ነው የሚባለውን የሞጋሴና የጉዲፈቼ ድምር በብዙ ሚሊዮኖች የሚበልጠውን፣ ትልቁን የአማራን ሕዝብ እወክላለሁ የሚል ቡድን ግን፣ ኢትዮጵያ በሚገባት ደረጃ አማራ፣ አማራ የምትሸት አማራዊ ትሆናለች ይላል እንጅ፣ ትልቁን ያማራን ሕዝብ ከትንሹ ከኦሮሙማ በማሳነስ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ ባማለት በብአዴን መንገድ ሊነጉድ አይችልም።      

ጭራቅ አሕመድ፣ እስክንድር ነጋ እና ዘመነ ካሴ

ጭራቅ አሕመድ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በግልጽ የዛተው አንዴና አንዴ ብቻ ሲሆን፣ እሱም በእስክንድር ነጋ ላይ ብቻ ነው።  በሌላ በማንም ላይ ላይ አልዛተም።  ጭራቅ አሕመድ በእስክንድር ነጋ ላይ ብቻ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ የዛተው ደግሞ ለስልጣኑ የሚያሰጋው እስክንድር ነጋ ብቻ መሆኑን በደንብ ስለሚያውቅ ነው።   

ባሁኑ ሰዓት ከትግሬና ከኦሮሞ ጎጠኞች በስተቀር ጦቢያውያንን ሙሉ በሙሉ ባንድነት በማሰባሰብ የሚችል መሪ አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም አብዛኛው የጦቢያ ሕዝብ በሙሉ ልብ የሚያምነው፣ የእውነተኛነትየርተኧኛነት (ቀጥተኛነት)፣ የፍትኸኛነትየጽናትና ያይበገሬነት ተምሳሌት የሆነው ፋኖ እስክንድር ነጋ ነው።  የእስክንድርን ታማኝነት፣ ሰብዓዊነትና ጨዋነት እጅጉን የሚያጎላው ደግሞ ከኦሮሙማው መሪ ከጭራቅ አሕመድ ቀጣፊነት፣ አጭበርባሪነት፣ ቀላማጅነት፣ ባለጌነት፣ ነውረኛነት፣ ጋጠወጥነት፣ መሠሪነት፣ አውሬነትና አረመኔነት (ባጠቃላይ ደግሞ አጸያፊ ሰብእና) አንጻር ሲታይ ነው።  ስለዚህም በእስክንድር ነጋ የሚመራ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል አማራ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቀላሉ በዙርያው በማሰበሰብ የትግሉን ሜዳ አማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን መላዋን ጦቢያን የሚያጠቃልል ሰፊ ሜዳ አድርጎበመላዋ ጦቢያ ላይ በሰፊው የተሰራጩትን እልፍ አእላፍ አማሮች በስፋት አሳትፎ ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት መግቢያ መውጫ በማሳጣት ውድቀቱን በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያቃርበው ሳይታለም የተፈታ ነው። 

እነ ዘመነ ካሴ እንደሚሉት፣ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻውም አማራ ነው ማለት፣ የትግሉ አላማ አማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል በመቆጣጠር በቂ ኃይል ገንብቶ በቀረው የጦቢያ ክፍል ላይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ማለት ነው። እስክንድር ነጋ እንደሚለው፣ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ ነው ማለት ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድን በመገርሰስ ኦነጋዊ መንግስቱን ካፈራረሱ በኋላ በፍርስራሹ ላይ ጦቢያን ጦቢያ ለማድረግ ያንበሳውን ሚና የተጫወተው፣ በጦቢያዊነቱ የማይደራደረው፣ በቁጥር ደግሞ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ድምር በሚሊዮኖች የሚበልጠው ትልቁ ያማራ ሕዝብ በቁጥሩ መጠን ሚና የሚጫወትባትን፣ በተገቢው ደረጃ አማራ አማራ የምትሸትን፣ ሕብረብሔራዊት ጦቢያን እንዳዲስ መገንባት ማለት ነው።  ስለዚህም እነ ዘመነ ካሴ የሚታገሉት የጭራቅ አሕመድን ቆዳ ለማዳን ሲሆን፣ እነ እስክንድር የሚታገሉት ግን ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ለማድረግ ነው።   

ጭራቅ አሕመድ በዛቻው መሠረት በእስክንድር ነጋ ላይ የከፈተው ግልጽ ጦርነት ዋናው ዘርፍ ደግሞ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው፣ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ነውና።  ጭራቅ አሕመድ በእስክንድር ነጋ ላይ የከፈተውን ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲመሩለትና እንዲያስተባብሩለት የቀጠራቸው ደግሞ ለገንዘብ ሲል እ*ቱን የሚሸጠው ገንዘባደሩ የኤልያስ ክፍሌ በከፈተው መረጃ ቲቪ ሥር የተኮለኩሉትን ግርማ ካሳን እና ዘመድኩን በቀለን የመሳሰሉትን የአማራ ለምድ የለበሱ ፀራማራ ተኩላወችን ነው።  እነ ግርማ ካሳንና ዘመድኩን በቀለን በቀጥታና በተዛዋሪ የሚያግዙት ደግሞ እነ መዐዛ ሙሐመድን የመሰሉት ያሜሪቃው የነጩ ቤተመንግስት (White House) ተስተናጋጆች ናቸው፣ ያማራ ሕዝብ መሠረታዊና ዘላለማዊ ጠላቶች ያንግሎ ሳክሶን (Anglo-Saxon) ነጭ ላዕልተኛ (White Supremacist) (በተለይም ደግሞ ያሜሪቃና የንግሊዝ መንግስታት) ናቸውና።  

የእስክንድር ነጋን ስም ግን ባላዋቂነት፣ በሆዳደርነት፣ በነጭ አሽከርነት፣ በጎጠኝነት፣ በጠባብነት፣ በዘረኝነት፣ በፊሪነት፣ በሐይማኖት አክራሪነት፣ ባግላይነት፣ በውሸታምነት፣ ባስመሳይነትና በመሳሰሉት ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም።  ስለዚህም፣ የጭራቅ አሕመድ ቅጥረኞቹ የእስክንድር ነጋን ስም ለማጥፋት እየሞከሩ ያሉት እስክንድር ጦር የለውም ወይም የጦር አመራር አይችልም በማለት ነው።  እስክንድር ጦር የለውም የሚለውን ወሬ በዋናነት የምታናፈሰው፣ ጦር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በትክክል የምታቅ የማትመስለው፣ የነጩ ቤተመንግስት ቤተኛ የሆነቸው ሐና ሙሐመድ ስትሆን፣  “እስክንድር ነጋ ያመራር ብቃት የለውም” እያለ ነጋ ጠባ የሚጽፈው ደግሞ በወያኔ ዘመን የመለስ ዜናዊ አሳባቂ የነበረው፣ ባሁኑ ዘመን ደግሞ የጃዋር ሙሐመድ አድናቂ የሆነው፣ በበላበት የሚጮኸው የመረጃ ቲቪው ግርማ ካሳ ነው።  

እነ ግርማ ካሳና ዘመድኩን በቀለ እስክንድርን ጦር የለውም ወይም የጦር አመራር አይችልም እያሉ እስክንድርን ለማንኳሰስ የሚሞክሩት ደግሞ ባንጻሩ ዘመነ ካሴን ለማግነን ነው። ዘመነ ካሴን ከፍ ለማድረግ የሚሞክሩት በራሱ በዘመነ ካሴ ገድል ሳይሆን፣ እስክንድርን ዝቅ በማድረግ በዜሮ ድምር ጨዋታ (zero sum game) መሆኑ ደግሞ፣ ራሱን ዘመነ ካሴን ትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባው ነው። 

 ባማራ ሕዝብ ባሕላዊና ታሪካዊ ትውፊቶች በየለቱ የሚስቁትና የሚሳለቁት፣ የፋኖ ደጋፊ መስለው በመቀረብ ፋኖን ከፋፍሎ የማዳክም ልዩ ተልዕኮ የተሰጣቸው እነ ኦቦ ዮናስ ብሩን የመስሉ ቀንደኛወቹ ኦሮሙሜወች እስክንድር ነጋን አር የነካው እንጨት እያስመሰሉ፣ ዘመነ ካሴን አለቅጥ በመካብ ሰማይ ሲያደርሱት ሲመለከት ደግሞ፣ ያማራ ሕዝብ ቆም ብሎ ሊያስብና ለምን ብሎ ሊጠይቅ ይገባል።    

ኦሮሙማውያን በተለይም ደግሞ ጭራቅ አሕመድ አጥብቀው የሚመኙት እስክንድር ነጋ በስም ማጥፋት ዘመቻ ተወግዶ ዘመነ ካሴ ደግሞ በስም መካብ ዘመቻ አለቅጥ ገኖየፋኖን አመራር ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ነው።  ጭራቅ አሕመድ ይሄን የሚመኘው ደግሞ በለጠ ሞላ አብንን ለኦሮሙማ እንደሸጥ፣ ዘመነ ካሴም ፋኖን ለኦሮሙማ እንደሚሸጥ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ቢሆን ነው።  በዚህ ደረጃ ርግጠኛ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የሚያውቀውን ስለሚያውቅ፣ የያዘውን ስለያዘ፣ ያዘጋጀውን ስላዘጋጀ ነው።  ጭራቅ አሕመድ ለነ ግርማ ካሳና ዘመድኩን በቀለ የሰጣቸው ተልዕኮ እስክንድርን ከጨዋታ ውጭ አርጉልኝ እንጅ ዘመነ ካሴንና የቀሩትን ሁሉንም ለኔ ተውልኝ የሚል እንደሆነ ግልጽ ነው።  ጭራቅ አሕመድ እነ ታማኝ በየነን እግሩን እንዲስሙ ባደረገበት መንገድ ዘመነ ካሴንም እግሩን እንደሚያስመው ባለ ሙሉ እምነት ነው።      

በመጀመርያ ደረጃ ዘመነ ካሴ ለእስር የበቃው ፣ መቸም መታመን የሌለበትን ጭራቅ አሕመድን አምኖ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ለመሸማገል ቀርቦ ጭራቅ አሕመድ ስለካደው ብቻ ነው።  አንዴ ለመሸማገል የሞከረ ደግሞ ሁለቴም፣ ሶስቴም ለመድገምና ለመደጋገም፣ ለመሠለስና ለመሠላለስ አይመለስም፣ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅምና።  ስለዚህም ዘመነ ካሴ ሂዶ፣ ሂዶ፣ የሚያስጨረሰውን ሁሉ እስጨርሶ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ለድርድር መቀመጡ አይቀሬ ነው።  በዚህ ላይ ደግሞ  ዘመነ ካሴ ግንቦት ሰባትን ከመቀላቀሉ በፊት ብአዴን የነበረ መሆኑ መረሳት የለበትም።  አንዴ ብአዴን ሁሌም ብአዴን (once a wolf always a wolf).

የዘመነ ካሴ አዳናቂወች “መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ” ሲሉ ደግሞ ኢትዮጵያ በሚገባት ደረጃ አማራ፣ አማራ ትሸታለች ወይም አማራዊ ትሆናለች እያሉ ሳይሆን፣ ያማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ የኢትዮጵያ ክፍል ከተቆጣጠርን በኋላ በቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ላይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እንደራደራለን እያሉነው።  ባማራ ሕዝብ ላይ ይህን ሁሉ የመከራ ዝናብ ካዘነበው ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ቀርቶ ለመደራደር የሚያስብ ደግሞ ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ያማራ ሕዝብ ጠላት ነው ፣ ያማራ ሕዝብ የሚድነው ጭራቅ አሕመድን ጭርቅ በማድረግ ብቻና ብቻ ነውና።  

በዚያ ላይ ደግሞ ጭራቅ አሕመድ የሚደራደረው ለመደራደር ብሎ ሳይሆን በድርድር ሰበብ ጊዜ ለመግዛት ሲል ብቻ ነው።  ጭራቅ አሕመድ ማለት ሲያቃጡበት የሚጥመለመል ሲዞሩለት የሚናደፍ ዐሲል ዕባብ ማለት ስለሆነ፣ ከጭራቅ አሕመድ ጋር መደራደር ማለት አመችውን ጊዜ ጠብቆ የሚነድፍን ዐሲል እባብ በኪስ መያዝ ማለት ነው።  ለዚህ ደግሞ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እንደራደራለን ብለው በጭራቅ አሕመድ ከተነደፉት ከተዋሕዶ አባቶች የበለጠ ማስረጃ የለም።  የዘመነ ካሴ የመጨረሻ እጣ ደግሞ ከተዋሕዶ አባቶች እጣ የከፋ እንጅ የተሻለ አይሆንም።  

የዘመነ ካሴ የመጨረሻ እጣ ጭራቅ አሕመድ እግር ሥር መውደቅ ከሆነ ደግሞ፣ ዘመነ ካሴ በፋኖ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት፣ በለጠ ሞላ በአብን ላይ ካስከተለው ጉዳት እጅግ የከፋ ነው።  ዘመነ ካሴ የፋኖ መሪ ሁኖ፣ ፋኖን ይዞ ጭራቅ አሕመድ እግር ሥር ወደቀ ማለት፣ ፋኖ አከተመለት ማለት ነው።  ፋኖ አከተመለት ማለት ደግሞ ያማራ ሕልውና አከተመለት ማለት ነው።  ስለዚህም፣ በለጠ ሞላ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ተመሳጥሮ አብንን እንዳቀለጠው፣ ዘመን ካሴም ከጭራቅ አሕመድ ጋር ተደራድሮ ፋኖን እንዳይከሰክሰው ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የግድ ነው፡፡  

የዘመነ ካሴ አሁናዊ አኳኋን የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል እንደሚሉት ነው።  ካሁኑ እንቱ በሉኝ ማለት የጀመረው አጉል ትቢተኛው ዘመነ ካሴ የበለጠ ሞላን ፈለግ በመከተል ካማራ ሕልውና በላይ የራሱን ስልጣን እያስቀደመ መሆኑን በጉልህ እያሳየን ነው።  አሁን፣ አሁን ላይ ዘመነ ካሴ በግልጽ እየነገረን ያለው፣ ዋና ጠላቱ ጭራቅ አሕመድ ሳይሆን እስክንድር ነጋ እንደሆነና፣ እስክንድር ጦሩን ይዞ ወደ አራት ኪሉ ቢገፋ፣ እስክንድር ስልጣን ላይ ከሚወጣ ሁሉንም ነገር ልጣ ብሎ፣ ከጭራቅ አሕመድ ጋር ተባብሮ እስክንድርን ከኋላ ሳይወጋው እንደማይቀር ነው።   

ያማራ ሕዝብ ባመናቸው ፈረሶች በደንደስ እየተጣለ አያሌ ጊዜ ተክዷል።  ስለዚህም እነ ዘመነ ካሴ ቤት እየጨሰች ያለችው ጭስ ያማራን ሕዝብ ልትከነክነው ይገባል።  ያማራ ሕዝብ ሁሉንም እንቆላሎቹን አንድ ቅርጫት ውስጥ አስገብቶ (all your eggs in one basket)ማንነቱን በደንብ በማያውቀው በዘመነ ካሴ ላይ ሙሉ እምነቱን ጥሎ፣ ባለቤቷን ተማምና ላቷን ውጭ እንዳሳደረቸው የዋህ በግ ከሆነ፣ በኦሮሙማ ጅብ ቁርጥምጥም ተደረጎ ሊበላ እንደሚችል መጠርጠር አለበት፣ ያልጠረጠረ ተመነጠረ፣ የጠረጠረ ቤቱን አጠረ ነውና።   

 ዘመነ ካሴ በእሳት ስላልተፈተነ፣ ወርቅ ይሁን መዳብ በውል አልታወቀም።  እያሳየን ያለው ፍንጭ የሚጠቁመው ደግሞ ወርቅ ሳይሆን መዳብ መሆኑን ነው፣ በኦሮሙማ እሳት ለመቅለጥ ራሱን እያዘጋጀ ያለ መዳብ።    ስለዚህም ያማራ ሕዝብ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የወጣውን፣ ከእምነቱና ካቋሙ ዝንፍ እንደማይል በተግባር ያሳየውን፣ በስልጣን፣ በጥቅም ወይም በሌላ በማናቸውም መደለያ ሊደለል የማይችለውን፣ የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ ይሆናል ተብሎ የማይጥረጠረውን የቁርጥ ቀን ልጁን አርበኛውን እስክንድር ነጋን እንዳይኑ ብሌን እየተንከባከበ ሊጠብቀው ይገባል፣ ከጭራቅ አሕመድ ብቻ ሳይሆን ከነዘመነ ካሴም ጭምር።   

በመጨረሻም በዚህ ዘመነ ካሴን በሚተች ጦማር ከማንም በላይ ልቡ ቅቤ የሚጠጣው ጭራቅ አሕመድ ነው፣ ጭራቅ አሕመድን ከምንም በላይ የሚያስደስተው አማራና አማራ ርስበርስ ሲባላ ማየት ነውና፣ የኦነግና የወያኔ ጉልበታቸው የራሳቸው ጥንካሬ ሳይሆን፣ ያማራ ድክመት እንደሆነ ያውቃልና፣ አማራን ሊያሽንፈው የሚችለው ኦነግ ወይም ወያኔ፣ ወይም የኦነግና የወያኔ ጥምር እንዲሁም የምዕራባውያን ድምር ሳይሆን፣ አማራ ብቻ እንደሆን ተረድቷልና።  

ዘመነ ካሴ ሆይ፣ ፍንጭ እያሳየኸን እንዳለኸው የምትታገለው የብአዴንን መንገድ በመከተል ከጭራቅ አሕመድ ለሚወረወርልህ የስልጣን ፍርፋሪ ሳይሆን እውነትም ላማራ ሕዝብ ሕልውና ከሆነ፣ አፈሙዝህን ከእስክንድር ነጋ ግንባር ላይ አዙረህ፣ በጭራቅ አሕመድ ግንባር ላይ ብቻ በማነጣጠር ጭራቅ አሕመድን ባስቸኳይ ጭርቅ ለማድረግ የበኩልህን ተወጣ።  ትንሹን ሥዕል የምትመለከት ትንሽ መሆንህን አቁመህ፣ ትልቁ ሥዕል ላይ የምታተኩር ትልቅ ሁን።  ጭራቅ አሕመድ ከተወገደ፣ የቀረው ሁሉም ችግር በቀላሉ እንደሚፈታ ተረዳ።  ከእስክንድር ነጋ ጋር ችግር ካለህ፣ የቤተሰብ ችግር ነውና ገመናህን እያወጣህ ለኦሮሙሜወች አትዘክዝክ።  ኤልያስ ክፍሌ፣ ግርማ ካሳ፣ ዘመድኩን በቀለ፣ ሐና ሙሐመድ እና የመሳሰሉት ወደላይ የሚክቡህ መወጣጫ ሊያደርጉህ እንጅ ወደውህ አይምሰልህ። 

በተለይም ደግሞ፣ ዘመነ ካሴ ሆይ፣ መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ የሚለው መሪ መፈክር መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ የሚለውን ስለሚያጠቃልል፣ ከእስክንድር ጋር ሊያወዛግብህ እንደማይገባ ተረዳ።  መሪ መፈክርህ ሁሉም ነገር ወደ ዐራት ኪሎ ይሁን።  ኦሮሙማን እምብርቱ ላይ ወግተህ ቅንብቻውን አስተንፍሰውበመተከል ዙርህ በጀርባው በኩል አክርካሪውን ስበረውበሚንጃር ተጠምዘህ ጉሮሮውን እነቀው።  ለጭራቅ አሕመድ ስልጣን ይበልጥ የሚያሰጉት የቤታማራ (ላኮመልዛ) እና የሸዋ ፋኖወች እንጅ የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች አለመሆናቸውን ተገንዘብ።  ለስልጣኑ የሚያሰጉት የቢታማራና የሸዋ ፋኖወች ተዳክመው፣ ለስልጣኑ እጅግም የማያሰጉት የጎንደርና የጎጃም ፋኖወች እስከተወሰነ ደረጃ ተጠናክረው ከተማወችን እየተቆጣጠሩና እየለቀቁ ውሃ ቀዳ ውሃ መልስ መጫወታቸው ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ መልካም አጋጣሚ ስለሚፈጥርለት፣ የሚጠቅመው ለጭራቅ አሕመድ ብቻ መሆኑን አስተውል።   

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።  

 መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic