>
5:26 pm - Thursday September 15, 1368

ጎጃም፤ የዘመነ ካሴ መነሻና መድረሻ

ጎጃም፤ የዘመነ ካሴ መነሻና መድረሻ

 

አጥናፉ አባተን መሰልኩት እንዴ?”  ዘመነ ካሴ

መስፍን አረጋ

 

ፈረንጆች እንደሚሉት አንዴ ተኩላ ሁሌም ተኩ (once a wolf always a wolf) ነው፣ ተመሳስሎ ማታለል ሲፈልግ የበግ ለምድ ይለብሳል እንጅ።  በተመሳሳይ መንገድ አምኖበትም ሆነ በጥቅም ተደልሎ አንዴ ብአዴን የሆነ ሰው ሁልጊዜም ብአዴን ነው፣ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ሰወች በስተቀር።  ብአዴን ደግሞ የወያኔን ፀራማራ አጀንዳ ለመተግበር በመለስ ዜናዊ ቀጭን ትዕዛዝ የተመሠረተ ፀራማራ ድርጅት ስለሆነ፣ አንዴ ብአዴን የሆነ ሰው ሁልጊዜም በምግባሩ ፀራማራ ነው።  አብዛኛው ብአዴን ደግሞ አማራ ሳይሆን ያማራ ለምድ የለበሰ ፀራማራ ተኩላ ነው።  የብአዴን አባል የነበረው አቶ ዘመን ካሴም ብአዴንነቱ መቸም የማይለቀው፣ ቢታጠብ የማይጠራ የዘላለም ብአዴን ነው።  በመሆኑም የሁልጊዜ ምግባሩ (ማለትም ቋሚ መመርያው) የፀራማሮች ጋሻጃግሬ ሁኖ ፀራማራ ዓላማቸውን ማሳከት ነው፣ ባማራ ሕዝብ ኪሳራ ግላዊ ትርፍ ማትረፍ ነው።  

በነገራችን ላይ አቶ ዘመነ ካሴን አማካሪ አድርጎ በ 2011 ዓም የሾመው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነው።  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ ያማራን መሬት ለወያኔና ለኦነግ የሸጠ፣ የጭራቅ አሕመድን ጭራቅነት እነ ስብሐት ነጋ በግልጽ እየነገሩትና በደንብ እያወቀ ጭራቅ አሕመድ ስልጣን ላይ እንዲወጣ ከፈተኛ ሚና የተጫወተ፣ በነ ጀነራል አሳምነው ግድያ ላይ ከደመቀ መኮንን ጋር የበኩሉን ድርሻ የተወጣ፣ ብአዴንነቱ መቸም የማይለቀው፣ ቢታጠብ የማይጠራ የዘላለም ብአዴን ነው።  

የነ ዘመነ ካሴ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ ጎጠኛ መፈክር የተፈጠረው ደግሞ ገዱ አንዳርጋቸው አሜሪቃ ገብቶ ከነ ሚካኢል መዶሻ (Michael Hammer) ጋር መዶለት ከጀመረ በኋላ ነው።  ባንግሎ ሳክሶን ነጭ ላዕልተኞች (Anglo-Saxon white supremacists)  በእጃዙር የሚዘወሩት ያሜሪቃና የእንግሊዝ መንግስታት ደግሞ ያማራ ሕዝብ መሠረታዊና ዘላለማዊ ጠላቶች ናቸው።  ያማራ ሕዝብ መሠረታዊና ዘላለማዊ ጠላቶች የሆኑት ደግሞ ያማራ ሕዝብ ባድዋ ድል ላይ ያንበሳ ድርሻ ያለው፣ ባፍሪቃ የነጻነት ትግል ላይ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ፣ ለነጻነቱ ቀናዒ የሆነ፣ ነጭን ከመጤፍ የማይቆጥር፣ በማንነቱ የሚኮራ ኩሩ ሕዝብ በመሆኑ ነው።  በዚህም ምክኒያት የነጮቹ ዓላማ ያማራ ሕዝብ ቢቻል ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ባይቻል ደግሞ ቁጥሩ በጭፍጨፋ፣ በጦርነት፣ በርሐብና በበሽታ ተመናምኖ፣ ብዛቱ ነጭን የማምለክ ዝንባሌ ካላቸው ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝቦች ብዛት እጅጉን ያነሰ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚጫወተው ሚና ኢምንት የሆነ  አናሳ ብሔረሰብ (minority) እንዲሆን ነው።  ጥቂት የትግሬ ሴቶች ተደፈሩ ከሚል በመረጃ ካልተረጋገጥ አሉባልታ (unconformed report) ተነስተው ኡኡታውን ሲያቀልጡት የነበሩት አሜሪቃና እንግሊዝ፣ ባማራ ሕዝብ ላይ በቪዲዮ የተደገፈ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሲፈጸም ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አይተው እንዳላዩ የሆኑት ያማራን ሕዝብ መጨፍጨፍ በቀጥታና በተዛዋሪ ስለሚደገፉ ነው።  

ስለዚህም ገዱ አንዳርጋቸው አሜሪቃ ገብቶ ካሜሪቃ መንግስት ሹመኞች ጋረ ከዶለተ በኋላ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ ከሚለው ታላቅ መፈክር ወርዶ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ ወደሚለው ጎጠኛ መፈክር መውደቁና፣ ነጭ አምላኪ የሆነው ጎጠኛው ኦነግ ደግሞ ጦቢያን በኦሮሙማ መልክ እሰራታለሁ የሚለውን ፉከራውን ይበልጥ ማጮሁ ሊያስገርም አይገባም።  ለማንኛውም የወያኔና የኦነግ ሎሌ የነበረውን የብአዴኑን የገዱን ጉድ ለገዱ እንተወውና በገዱ ወደተሸመው ወደ ብአዴኑ ዘመነ ካሴ እንመለስ።     

አንዳንድ ሰወች እንደዘበት ጣል የሚያደርጓት አጭር ንግግር ሙሉ አስተሳሰባቸውን ፍንትው አድርጋ ታሳየለች፣ ስለ ሰወቹ ማንነትና ምንነት ከሙሉ መጽሐፍ በላይ ትናገራለች፣ ከሺ ምስክሮች በላይ ትመሰክራለች።  አቶ ዘመነ ካሴ ደግሞ እስክንድር ነጋን በተቸበት በስፋት በተሰራጨ ንግግሩ ላይ “አጥናፉ አባተን መሰልኩት እንዴ?” በማለት እንደ ቀልድ ጣል ያደረጋት ዐረፍተ ነገር ቋሚ አስተሳሰቡ ብአዴናዊ ስለዚህም ፀራማራዊ መሆኑን በግላጭ ትመሰክራለች።  

በብአዴናዊው በዘመነ ካሴ ጎጠኛ አስተሳሰብ መሠረት አጥናፉ አባተን የገደለው ወይም ያስገደለው መንግስቱ ኃይለማርያም የሸዋ አማራ ሲሆን፣ አጥናፉ አባተ ደግሞ የጎጃም አማራ ነው። በሌላ አባባል ብአዴንነቱ እይታውን ላንሸዋረረው ለዘመነ ካሴ፣ በመንግስቱ ኃይለማርያምና ባጥናፉ አባተ ላይ የሚታዩት አንዱ ከሸዋ ሌላው ከጎጃም መሆናቸው ብቻ እንጅ ሌላ ምንም አይታየውም።  

በመሠረቱ የደርግ መሥራች የነበረውን የሆለታ ምሩቁን ሻለቃ (Major) አጥናፉ አባተን ለሞት ካበቁት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ፣ እሱን የሚበልጡ ሰወች ደርግ ውስጥ እንዳይገቡና በምንቸቶች መኻል ጋን ሁኖ ለመታየት ሲል ብቻ፣ “ከሻለቃ ማዕረግ በላይ የደርግ አባል አይሆንም፣ እንዲሁም የሐረር አካዳሚ ምሩቅም የደርግ አባል አይሆንም” የሚሉትን ሐሳቦች በዋናነት የሚያራምድ፣ የዝቅተኝነት ስሜት ሰለባ የነበረ መሆኑ ነው።  ዘመነ ካሴም እየተጣጣረ ያለው ካውራወች ጋር ተቀናጅቶ ጭራቅ አሕመድን ባስቸኳይ ጨርቅ በማድረግ ያማራን መከራ ለማሳጠር ሳይሆን፣ በጫጩቶች መኻል አውራ ዶሮ ሁኖ ለመታየት ነው።  ገና ካሁኑ ተከታዮቹን እንቱ በሉኝ የሚለውም በዚሁ ምክኒያት ነው።  ለማንኛውም ያለፈውን ያጥናፉ አባተን ጉዳይ ለታሪክ እንተወውና በዘመናቸን በዘመነ ካሴ ላይ እናተኩር። 

ዘመነ ካሴ በራሱ ባንደበቱ እንደተናገረው የሱና የእስክንድር ጉዳይ ከመንግስቱ ኃይለማርያምና ካጥናፉ አባተ ጉዳይ ጋር አንድ ዓይነት ነው።  እስክንድር ነጋ የተነሳው የሸዋ ፋኖን ይዞ እሱን (ማለትም ዘመነ ካሴን) እንዳጥናፉ አባተ ለማድረግ ሲሆን፣ እሱ እየታገለ ያለው ደግሞ የጎጃም ፋኖን ይዞ እንዳጥናፉ አባተ ላለመሆን ነው።  ስለዚህም በዘመነ ካሴ ብአዴናዊ እይታ መሠረት የሸዋ ፋኖ በተለይ፣ ሸዋ ደግሞ ባጠቃላይ የነዘመነ ቀንደኛ ጠላት ነው።  ዘመነ ካሴ ሸዋን በጠላትነት ማየቱ ደግሞ ሊያስገርም አይገባም፣ ዘመነ ካሴ ብአዴን የሆነው ሸዋን በቀንደኛ ጠላትነት የፈረጁትን የወያኔንና የኦነግን  ፀራማራ አጀንዳ ለማስፈፀም ነበረና።  

ወያኔና ኦነግ ሸዋን በቀንደኛ ጠላትነት የፈረጁት ደግሞ የስልጣናቸው ቀንደኛ ስጋት ሸዋ መሆኑን ስለሚያውቁ ነው።  ለጭራቅ አሕመድ ስልጣን ይበልጥ የሚያሰጋው የሸዋ ፋኖ እንጅ የጎጃም ፋኖ አለመሆኑን ለመገንዘብ የውትድርና ጠቢብ መሆንን አይጠይቅም።  ለምሳሌ ያህል የጎጃም ፋኖ እስካሁን ከፈጸማቸው ውስጥ ጥቂቶቹን እንኳን የሸዋ ፋኖ ፈጽሟቸው ቢሆን ኖሮ፣ ጭራቅ አሕመድ ከወራት በፊት ጨርቅ ሁኖ፣ ሙቶ፣ ተቀብሮ ነበር።   ጭራቅ አሕመድ ከሞላ ጎደል ሙሉ ኃይሉን በሸዋ ፋኖ ላይ ያሰማራውም በዚሁ ምክኒያት ነው። 

ለጭራቅ አሕመድ ስልጣን ይበልጥ የሚያሰጋው የሸዋ ፋኖ ተዳክሞ፣ ለስልጣኑ እጅግም የማያሰጋው የጎጃም ፋኖ እስከተወሰነ ደረጃ ተጠናክሮ ከተማወችን እየተቆጣጠረና እየለቀቀ ውሃ ቀዳ ውሃ መልስ መጫወቱ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ መልካም አጋጣሚ ስለሚፈጥርለት፣ የሚጠቅመው ለጭራቅ አሕመድ ብቻ ነው።  በተጨማሪ ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ጽኑ ፍላጎት ለስልጣኑ እጅግም የማያሰጉት የጎጃምና የጎንደር ፋኖወች፣ ለስልጣኑ እጅጉን ከሚያሰጉት ከሸዋና ከቤታማራ ፋኖወች ይበልጥ ጎልተው እንዲታዩና ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል መምራት ያለብን እኛ የጎጃምና የጎንደር ፋኖወች ነን ብለው እንዲያስቡና አልፎ ተርፎም በሸዋና በቤታማራ ፋኖወች ላይ እንዲታበዩ ነው።  ዘመነ ካሴም እያደረገ ያለው ይሄንኑ ነው፣ ከተማ ገብቶ እየወጣ ያማራን ሕዝብ ማስጨረሰና፣ የፋኖ መንገዶች ሁሉ ማለፍ ያለባቸው በኔ በኩል ብቻ ነው እያለ በትዕቢት መወጣጠር። 

ስለዚህም ዘመነ ካሴ ራሱን ከጦቢያዊነት አጥብቦ መነሻየ አማራ መድረሻየም አማራ እያለ ቢፎክርም፣ እውነታው ግን ካማራነትም የጠበበ መነሻውም መድረሻውም እንድ ክፍለሀገር የሆነ ክፍለሀገራዊ ጎጠኛ መሆኑ ነው።  በመሆኑም ዘመነ ካሴ በቀጥታና በተዛዋሪ እየፈጸመና እያስፈጸመ ያለው የወያኔንና የኦነግን ፀረሸዋ አጀንዳ ነው።   ከሸዋ በኩል ናቸው የሚባሉት እነ ዮሐንስ ቧያለው ሽንት መሽናት እየተከለከሉ፣ ከጎጃም በኩል ናቸው የሚባሉት እነ መስከረም አበራ የዘመነ ካሴን አጀንዳ የሚያራምዱ ረጃጅም ጽሑፎችን እንዲጽፉና በጭራቅ አሕመድ በተገዙ መገናኛ ብዙሃኖች (መረጃ ቲቪ፣ ግዮን ቲቪ፣ ሕብር ሬድዮ፣ ዘሐበሻ ድርገጽ ወዘተ.) ላይ በስፋት እንዲሰራጭላቸው የሚመቻችላቸው ደግሞ በዚሁ ምክኒያት ነው።

ዘመነ ካሴ የብአዴን ወጣት ሊግ ሆኖ ዳግማዊት ሞገስ ጋር  ስብሰባ ላይ

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic