>
5:26 pm - Monday September 15, 0070

ይድረስ ለዘመነ ካሴ እና ለአስረስ ማረ ዳምጤ

ይድረስ ለዘመነ ካሴ እና ለአስረስ ማረ ዳምጤ

(ክፍል አንድ)

ዘላለም ይግዛው

ፋኖነት ከእኔ ይልቅ እርሱ ይቅደም በማለት በወንድማማቶች መካከል ስልጣን የሚሰጣጡበት እንጅ ለስልጣን የሚጋጋጡበት ትግል አይደለም፡፡  እውነታው ይህ ሁኖ እያለ የጎንደር፣ የወሎ፣የሸዋ  ፋኖዎች ውስጥ ለውስጥ ስራቸውን እየሰሩ ባሉበት ጊዜ የጎጃም ፋኖ ተወካይ ነን የሚሉ ሁለት አጉራ ዘለሎች  ዘመነ እና አስረስ በየ ሚዲያው የሚፈነጩት ለምንድን ነው? እነዚህ ግለሰቦች ከተናገሩት ከብዙ በጥቂት የተወሰኑ ንግግሮች እንመልከት፦

➤ “እነ እገሌን(እነ እስክንድርን) አስፈላጊ ከሆነ እርምጃ እንወስድባቸዋለን” (የአስረስ ማረ ዳምጤ ንግግር)፡፡

➤ “እስክንድር እና አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ ሲዶልቱ ተገኝተዋል” የዘመነ ካሴ ንግግር፡፡

➤ “እስክንድር ከታየ አፅቀስላሴ እና ከአምባሳደር ስለሽ በቀለ ጋር በስልክ ሲነጋገሩ ተገኙ”፡፡ የማርሸት ፀሀይ (የዘመነ ካሴ ቃለ አቀባዩ)፡፡

➤”የእስክንድር ምስል ያለበትን ቲ-ሸርት ማቃጠል” በማህበራዊ ሚዲያ ሲዟዟር የነበረ መረጃ ነው፡፡

ህይወቱን ለመስጠት ወደ ትግል ሜዳ የወጣን አንድ እውነተኛ፤ የመርህ ሰው፣ የፅናት ተምሳሌት የሆነን ግለሰብ በዚህ ደረጃ ለማዋረድ መሞክር ራስን ማቅለል እንጅ እስክንድር ከሚበርበት ከፍታ ልታወርዱት አትችሉም፡፡ እስክንድርን አቀለልነው ብልችሁ እናንተው ቀላችሁ ከመገኘታችሁ በላይ ማንነታችሁን በትክክል ማሳየት ቻላችሁ፡፡ ዘመነ እና አስረስ እስክንድርን የሚቃወሙበት ምንም አይነት አመክንዮ የላቸውም፡፡ ከእስክንድር ጋር የሚወዳደሩበትም አቅምም ሆን ችሎታ የላቸውም፡፡ እስክንድር ላይ ጥላሸት ለመቀባት እንደ ምክንያት ያነሱት “መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጲያ” በሚለው እሳቤ ሲሆን የእነ ዘመነ መፈክር ደግሞ “መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ” የሚል ነው፡፡

“መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ” ምን ማለት ነው፡፡ ይህ ቡድን ከአማራ ስነ-ልቦናዊ ውቅር ወጭ ነው፡፡ አማራ በዚህ ደረጃ ወርዶ አያውቅም፡፡ አማራ የሚታወቀው ሀገሬን ሲል እንጅ በእናንተ አስተሳሰብ ደረጃ ጠቦ አያውቅም፤ ይህም አባባል የህወኃትን እና የኦነግን ጥንተ እሳቤ ይወክላል እንጅ አማራን የሚወክል አይደለም፡፡ ዳሩ ግን የብዓዴንነታችሁ እሳቤ ስለሚያሸንፋችሁ አሁንም በጎጥ ከማሰብ አልወጣችሁም፡፡ አማራ በአማራነቱ ተደራጅቶ ለህልውናው መታገሉ ከኢትዮጲያዊነቱ ማማ ሊያወርደው አይችልም፡፡ እናንተ ግን የሰፈር አውራ መሆን ስለምትፈልጉ በዚህ ደረጃ መጥበብን ፈለጋችሁ፡፡ ያልተዘመረላቸው ድንቅ ታጋዬች (እነ ዝናቡ፣ እነ ኢንጅነር ማንችሎት፣ እነ ታደሰ ሙሉነህ፣ ዶ/ር ጌትነት፣ እነ ዶ/ር መዝገቡ፣ እነ ወግደረስ ጤናው እና ሌሎችም) በጎጃም ውስጥ እያሉ ዘመነ እና አስረስ  ማን ሾማቸው? ማንስ መረጣቸው? ህዝባዊ ቅቡልነትስ አላቸው ወይ? ብለን ስንመረምር እንደ አብይ ራሳቸውን የሾሙ ሁነው እናገኛቸዋለን፡፡

ሌላው በእስክንድር እና በዘመነ መካከል ለተፈጠረው የግንኙነት መሻከር የህዝባዊ ግንባሩ መመስረት ነው፡፡ “ህዝባዊ ግንባር መፍጠሩን እስር ቤት ሁኘ ሰማሁ” ይላል ዘመነ፡፡ እስክንድር ይህን ማድረጉ ወይም ፋኖዎችን መሰብሰቡ ችግሩ ምንድን ነው? የተበታተነው ኃይል መሰብሰቡ ለትግሉ ከሚኖረው ጠቀሜታ አንፃር መመርመር ሲገባ ለምን ህዝባዊ ግንባር ተፈጠረ ብሎ ቡራ ከረዬ ማለት ለምን አስፈለገ? ከስሜት ይልቅ ስራችንን በምክንያት እና በእውቀት መምራት የተሻለ ነው፣ ጭራቁ አብይ በአማራ ደም እለት እለት እየታጠበ እናንተ ከግብረ አበሮቻችሁ ጋር ስለ ስልጣን ማሰብ ጤነኝነት አይደለም፡፡

ፋኖነት መስዋዕት የሚከፈልበት የትግል አውድማ እንጅ ታጋይ ወንድምን ጥላሸት የምንቀባበት ቦታ አይደለም፤ ፋኖነት በወንድሞቻችን ደም ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባበት ጉዞ እንጅ የገንዘብ መሰብሰቢያ ካዝና አይደለም፤ፋኖነት የነፃነት እና የፅድቅ ትግል እንጅ በሀሰት የታጋይን ስም የምናንቋሽሽበት መድረክ አይደለም፤ፋኖነት ለስልጣን ጥመኞች መሸሸጊያ ዋሻ ሊሆን አይገባም፤ፋኖነት በመግለጫ ጋጋታ ራስን ከህዝብ ጋር ለማስተዋወቅ የሚቻልበት ድልድይ አይደለም፡፡

ትግሉን ሊያግዝ፣ ህይወቱን ሊሰጥ ወደ ጫካ የወጣን ወንድም ይደገፉል፣ ይታገዛል እንጅ እንዴት በሚዲያ ስሙ ይብጠለጠላል? ይህ ድርጊት ማንን ነው የሚጠቅመው? እስክንድር እንኳን መጣህልን ብላችሁ የምትቀበሉት አርበኛ እንጅ የእናንተ ስድብና ውርጅብኝ የሚገባው ሰው አይደለም፡፡

ይህንን ጊዚያዊ አለመግባባት የምታራግቡ ሚዲያዎች  ስርዓት ብትይዙ መልካም ነው፡፡ የዘመድሁን በቀለ ሚዲያ፣ መረጃ ቲቪ፣ ግዮን ቲቪ፣ ሕብር ሬድዮ፣ ሮሀ ሚዲያ ብትጠነቀቁ ይሻላል፤ የተፈጠሩትን ጥቃቅን አለመግባባቶች ለሚዲያ ማቅረብ ትግሉን እንደሚጎዳው እያወቃችሁ አምስት አስር ለመለቃቀም ብላችሁ በምታቀርቡት መረጃ ለወደፊቱ ተጠያቂ እንደምትሆኑ ልትገነዘቡ ይገባል፡፡

ቸር እንሰንብት

በትግሉ ለተሰዉ ታጋዬች ዘላለማዊ እረፍትን ፈጣሪ ይስጥልን

Filed in: Amharic