>
5:26 pm - Saturday September 15, 6373

የዘመነ ካሴና የብአዴን ጥምረት የወለደው የፋኖን ትግል ለማጨናገፍ እየተደረገ ያለው ዘመቻ አይሳካም

የዘመነ ካሴና የብአዴን ጥምረት የወለደው የፋኖን ትግል ለማጨናገፍ እየተደረገ ያለው ዘመቻ አይሳካም

በትግሉ ሰመረ 

ጀግናው የአማራ ፋኖ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ጠልፎ የአማራን ህዝብ የአውሬው መሳለቂያና ማላገጫ ለማድረግ የሚንቀሳቀሰው የብአዴን ኃይል፤  ተስፈኛው አድርጎ አስቀምጦት የነበረውን ዘመነ ካሴን  ወደፊት አምጥቶ አጠቃላይ የፋኖ መሪ አድርጎ ለማሾም በቃላቀባዩ ማርሸት ፀሐይ 1  በኩል ያደረገው ጥረት በፋኖ ብርጌድ መሪዎች ምርጫ ሲከሽፍበት፤  ከአውሬው የኦሮሙማ ኃይል ጋር በመጣመር በአማራ ፋኖ  ሕዝባዊ ድርጅት መሪ በኾነው ፋኖ አርበኛ   እስከንድር ነጋ ላይ የሃሰት ውንጀላዎችን  በመፈብረክ ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ  እያኪያሄደ ይገኛል።  ብአዴን ለፕሮፖጋንዳው ካሰማራቸው የሶሻል ሜዲያ በቀቀኖች/parroters በተጨማሪ ፤ ነውርን የማያውቁትን ለሆዳቸው ሲሉ ምንም ከማድረግ የማይመለሱ በዝቅተኝነት ስሜት የሚሰቃዩትን  የአማራ ህዝብ ወዳጅ መሳይ  ጠላቶች የኾኑትን  የመረጃ ቲቪዎቹ ዘመድኩን በቀለና ግርማ ካሳን እንዲኹም ‘ከአሰግድ ውጪ ወደ ውጪ’ 2  እያሉ አሰግድ መኮንንን ሲያማልሉትና  ሲዘውሩት የነበሩት  ‘አንድ አማራ’ በሚል በፋኖ አስተባባሪነት የእራሳቸውን የሰየሙ የወያኔ  ሰላዮች  ጭምር  በቀጥታና በተዘዋዋሪ  እየተጠቀመባቸው ይገኛል።   

ከዲያስፖራው በኩል በብአዴን ዙሪያ የተሰባሰቡት የ3A ብአዴናውያን፣ የሮሃ ሚዲያዋ መአዛ ሞሃመድ፣ ፣ የግዮን ቲቪው መለስካቸው ስማቸው እንዲኹም  እነ አቻምየለኽ ታምሩና ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ   እስክንድር ነጋን  ከትግሉ በማግለል ጎጃም ላይ  ብአዴን ያነገሠውን አንገራባጁን ዘመነ ካሴን ወደ አማራ ፋኖ መሪነት ለማምጣት  እያደረጉ ያሉት የተቀናጀ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በተመልካች ዘንድ አስተዛዛቢ ኾኗል። አቻምየለኽ ታምሩና   የፕሮፌሰር ሃብታሙ ከዚኽ ቀደም መሬት ላይ ያሉት ተዋጊዎቹ ፋኖዎቹ  እራሳቸው መሪያቸውን ይምረጡ እያሉ ሲወተውቱ እንዳልነበረ ሁሉ፤ ፋኖዎች መሪያቸውን በዲሞክራሲያዊ ስርአት ወዳጅም ጠላትም ጠንቅቆ የሚያውቀውን  ከ30 ዓመታት በላይ  በዲሞክራሲና በአማራ ትግል ዙሪያ ከፍተኛ የትግል ታሪክ  ያለውን ጀግናው እስክንድር ነጋን 3 መሪያቸው አድርገው ሲመርጡ ከመናደዳቸው የተነሳ፤  እስክንድር  ‘የአማራ ጠላት’ ነው 4 የሚል አሳፋሪ ንግግር እስከመናገር ደርሰዋል። በኢሕአፓና መኢሶን  መካከል የነበረውን ልዩነት የታሪክ መሃይሙና አውሬው አብይ አህመድ በ’ሸ’ና በ’ቸ’ ፊደል የተፈጠረ አስመስሎ እንዳቀረበው፤  ብአዴን የሚያራግበውን ‘መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ’ የሚለውን የአማራን ህዝብ ልእልና የማይመጥን ሃሳብ ካልተቀበላችሁኝ ብሎ የሚንጨረጨረው ፕሮፌሰር ሃብታሙ የእስክንድርን ሃሳብ ሞግቶ ማሸነፍ ሲያቅተው  ወደ  ቅጥ ያጣ   የ’ፈ’ና የ’ፋ’ ፊደል ስንጠቃ ና ተራ ውንጀላ ውስጥ ገብቷል4።    ከሁሉም በላይ ግን ፕሮፌሰሩ ትዝብት ውስጥ የጣለው እስከንድር ነጋ  መዳረሻችን ‘ኢትዮጵያ’  ማለቱ አሳምሞት  እየተንገሸገሸ ‘እቃቃ ጨዋታ’ 4 ሲል መግለፁ ነው፤  በርግጥ የአማራ ፋኖ ‘ኢትዮጵያን’ መዳረሻው አድርጎ ማለሙን እየተቃወመ ያለው ፕሮፌሰሩ አማራዊ ኢትዮጵያዊነቱ ላይ ሳይኾን ብአዴናዊ ማንነቱ ላይ ተንተርሶ ድብቅ የጎጥ ቡድንተኝነት ዓላማውን እያራመደ  መኾኑን ያሳየበት ክስተት ነው።

ፕሮፌሰር ሃብታሙ እስክንድርን እንዲኽ አምርሮ የጠላውና እስክንድር ላይ በግሉ ዘመቻ የከፈተበት ዋናው ምክንያት፣ ከአፀያፊዎቹ ብአዴኖች ጋር በመኾን ወጥኖት የነበረው የፋኖን ትግል የመጥለፍ ህልሙን ገና ከጥንስሱ ስለነቃበትና ሃሳቡን ውድቅ ስላደረገበት ነው። ለዚኽ ማስረጃ የሚኾነው ቀደም ሲል የድምፅ ቅጂው በሶሻል ሜዲያ የተለቀቀው5 ከእስክንድር ነጋ ጋር  የነበራቸው የዙም ውይይት ላይ እስክንድር  ከብአዴን ጋር እንሥራ የሚለውን የፕሮፌሰሩን ሃሳብ ባለመቀበል ‘ብአዴን አማራን ነፃ ሊያወጣው አይችልም፤ ብአዴን አማራው ላይ ከፍተኛ በደልን የፈፀመ ድርጅት ነው። ብአዴን ንስሃ እንዲገባ ነው የሚመረከረው5።’ ብሎ እቅጩን ስለመለሰለት ነው።  

በሌላ በኩል  የብአዴን ጊዜያዊ ፈረስ/frontman የኾነው  ዘመነ ካሴ  በአንድ ራስ ሁለት ምላስ  ከዚኽ በፊት በኢትዮ 360 ሜዲያ ቀርቦ  ”እኔና እስክንድር አንድ ዓላማ ነው ያለን   አማራን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው፤  እስክንድርና እኔን በፍፁም ይሄ ምድር ሊበጥሰው የማይችለው የመንፈስ  አንድነት አለን፤  ሁለታችንም የሥልጣን ጥም የለብንም ፤  ከፖለቲካ ፍላጎት ከፖለቲካ ግብ ርእዮትና ዓላማ በላይ ነው በኔና በእስክንድር መካከል ያለው ወንድማማችነት፤ በኔና በእስክንድር መካከል ማጋነን ካልኾነ ያለችው ማርያምና ልጇ ናቸው።”  ያለውን ረስቶ ዛሬ በምርጫ ሲሸነፍ  ‘እስክንድር ነጋ አብይ አህመድ ጋር አዲስ ፀረ አማራ ግንበር ፈጥረው በአማራ የህልውና ትግል ላይ ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ ይዘናቸዋል6 ሲል መክሰሱ ነው።   ዘመነ የብአዴኑ አይዶሎግ ፕሮፌሰር ሃብታሙ የጫረለትን ሃፍረተ ቢስ ንግግር  ያዳመጠ ማንኛውም የአማራ ፋኖ ዘመነ ካሴ   አእምሯቸው በቀነጨሩ በጥቅም በተሳሰሩ ብአዴኖች  ቁጥጥር ስር ኾኖ የሚንቀሳቀስ  ነፃነት የሌለው የተጠረነፈ ፋኖ  እንደኾነ ይረዳል። በተመሳሳይ ምሬ ወዳጆ የእስክንድርን ስም እያነሳ ሲቀባጥር ሲታይ በብአዴን የተጠረነፈ  የብአዴን ፈረስ መዀኑን አሳይቷል።

እስክንድር ነጋ አማራዊ ስነልቦና  የኾኑትን ጀግንነት፣ጽናት፣እምነት፣የሃሳብ ልእልናና ኢትዮጵያዊ አርበኝነት  በሙሉ የተላበሰ መኾኑን   በመላው የአማራ ጠቅላይ ግዛት የሚገኘው የአማራ ህዝብና  ፋኖ እንዲኹም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ  የሚያውቁት እንደ ወርቅ በእሳት የተፈተነ  በዓለም አደባባይ እውቅናንና ሽልማቶችን  ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው።   ዘመነ አዲሶቹ የብአዴን አይዶሎጎስ  እነ ፕሮፌሰር ሃብታሙ የፃፉለትን ብአዴናዊ  ፀያፍ ንግግር  የእስክንድር ነጋን ልእልና አንዲትም ቅንጣት ያኽል ዝቅ ሊያደርገው አይችልም። እንደ አለመታደል ኾኖ  እጅግ ብዙ ከሃዲዎች በሚፈራረቁበት በኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ እስክንድር ያለ  እውነተኛ ጀግና በአማራው የህልውና ትግል ላይ በመሪነት መከሰቱ የአማራን ህዝብ  የማይነጥፍ ዘላለማዊ ልእልና ያሳየ ነው። አማራ ጀግናውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው፣  በፕሮፖጋንዳና በቅጥፈት ጋጋታ በቀላሉ በወሬ የሚፈታና የሚነዳ ህዝብ  አይደለም። ለዚኽም ነው የዘመነ ካሴና የብአዴን ጥምረት የወለደው የፋኖን ትግል ለማጨናገፍ እየተደረገ ያለው ዘመቻ የማይሳካው።

ብአዴን ዘመነ ካሴን ከፊት እንደ ሽፋን እየተጠቀመ በአርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ እየነዛ ካለው የሃሰት የፕሮፖጋንዳ ዘመቻው ጎን ለጎን፤   ‘መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ’ የሚል የዝቅተኝነት ስሜት ተጠቂዎቹ ከህወሃት፣ ከኦነግና ኦሕዴድ  አስተሳሰብ የቀዳውን የጠባቦች ፍልስፍና  በአማራ ፋኖዎች በተለይም በጎጃም ፋኖዎች ላይ  ለማስረፅ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ለዚኽም ምስክር የሚኾነው የአማራ ህዝብ መለያ የኾነውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ  ዓላማ እስከማቃጠል የደረሰ  በብአዴናውያን የተደራጀ እጅግ አሳፋሪ ትእይንት መታየት መጀመሩ   ነው።  ጐጥን ያስቀደመ  ኢትዮጵያ ጠል   አስተሳሰብን  በተለይ ብአዴንን የሚጠየፉትን  በጎጃም የሚንቀሳቀሱ  የፋኖ ክፍለ ጦሮችን አሳዶ ለመምታት  ከአውሬው መከላከያ ሠራዊት ጋር ጭምር በመቀናጀት  ዘመቻ እያደረገባቸው ይገኛሉ። ወያኔ ዳንሺያ ላይ ሠርቶት የነበረውን ምሽግ ደርምሰው  ወያኔን ከአማራ ምድር አሳደው ካባረሩት ብርቅዬ የአማራ ፋኖዎች ውስጥ አንዱ የነበረውን ፋኖ ኮሎኔል ጌታሁንን በብአዴኖች የሚዘወረው ዘመነ  የላካቸው የብአዴን ታጣቂዎች ቢችሉ እጁን ይዘው ካልኾነም  በሽምግልና ሥም ጊዜውን በማባከን በመከላከያ ተከቦ እጁን እንዲሰጥ ለማስገደድ የሄዱበትን ርቀት የሚናገር የስልክ ድምፅ ቅጂ7 ሰምተናል።  

እነ አስረስ ማረ ዳምጤ የለየላቸው ብአዴናውያን  ለመኾናቸው  ሌላው ማሳያ በአማራነታቸው የአሸናፊነት ታሪክ የሚኮሩ በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩትን የቀድሞ ጓዶቻቸውን ጭምር ለመግደል ሲዝቱ መሰማታቸው ነው። በትምህርት ደረጃቸው ከፍ ያሉ በአስተሳሰባቸው የላቁ እንደ  ዶ/ር እንዳለማው  ያሉ ፋኖዎቸን ከጎጃም ምድር ለማፅዳት  በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደባቸው ያለው የአፈና ዘመቻ የዚኹ ብአዴናዊ ፀረ አማራና ኢትዮጵያ ዘመቻ አካል ነው። አስረስ ማረ ጋዜጠኛ ፋኖ ወግደረስ ጤናውን ያሳፈነው፣ ወግደረስ ለአማራ ትግል ስላልታገለ አይደለም፣ ፋኖ ወግደረስ ጤናው በአማራነቱ ኩራት የሚሰማው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ጎጠኝነትና ብአዴንን የሚጠየፍ አስተሳሰቡ አጼ ቴዎድሮሳዊና ምንሊካዊ የኾነ ልበ ሙሉ ጀግና ነው። ጎጃም ውስጥ በተደረገው ህዝብን የማንቃትና ፋኖን የማደራጀት ዘመቻ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ያከናወነው ሥራ ለዚኽ በቂ ምስክር ነው። ብአዴኖች ይህ ጎጃም ውስጥ የጀመሩት ዘመቻ  ከተሳካላቸው ነገ በተመሳሳይ በሸዋ፣ በወሎና  በጎንደር ያሉ ፋኖዎችን ለመቆጣጠር ከአውሬው ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ተጣምረው ተመሳሳይ  ድርጊት ለመፈፀም እንደሚሞክሩ ጥርጥር የለውም።

በመኾኑም በመላው አማራ ግዛት የሚገኙ የአማራ ህዝባዊ ድርጅት መሪዎች  እንዲኹም በመላው አማራ ጠቅላይ ግዛት የሚገኙ ፋኖዎች ፤ የዘመነና ካሴና አስረስ ማረ  ቡድን ከባንዳዊ ብአዴናዊ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ፋኖ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ሊሰጡት ይገባል።  ጀግናው የጎጃም ፋኖና ህዝብ በበኩሉ የነዘመነን በጎጃም ህዝብ ትከሻ ላይ ተንጠላጥለው ብአዴንን መልሰው ለማጠናከርና በአማራው ጫንቃ ላይ ለማንገሥ የሚያደርጉትን ህዝብን ፣ኢትዮጵያን፣ ሰንደቅ ዓላማን ፣ታሪክን የካደ ብአዴናዊ አኪያሄድ በመንቀፍ ከዚኽ በፊት ይሰጣቸው የነበረውን ድጋፍ ሊነፍጋቸው ይገባል። በአንፃሩ በአራቱም ጠቅላይ ግዛት የሚገኙ ፋኖዎች የመሠረቱት ‘የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት’ አባል  ኾነው ጎጃም ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ላሉት እነ ፋኖ ማስረሻ ሰጤ ለሚመሯቸው ክፍለ ጦሮችና ብርጌዶች እየሰጠ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠንክሮ በመቀጠል፣  የአውሬው ኦሮሙማ ቡድን ተላላኪውን የብአዴንን ሴረኛ አካኼድ በማክሸፍ  የአውሬውን የኦሮሙማ  መንግሥት  ከሥሩ መንግሎ  ለመንቀል የሚደረገውን ትግል መደገፍ ይጠበቅበታል። 

አማራ ነፍጡን አንስቷል!  በደም አማራ በመኾኑ ሊያጠፋው የሚችል ኃይል ከእንግዲኽ አይኖርም!።  አማራ ለጊዜው ሥልጣን የተቆናጠጡ የሃሳብና የአስተሳሰብ ድኩማኖች ኢትዮጵያን እንዲያጠፏት አሳልፎ ሊሰጣቸው አይችልም። የሃሳብ ልእልናው መገለጫ የኾነችውን ኢትዮጵያን የማዳን ታሪካዊ ግዴታውን  አዲስ አበባ የምኒልክ ቤተመንግሥትን ከአውሬው መዳፍ በማላቀቅና በመቆጣጠር የሚያረጋግጥበት ጊዜው እሩቅ አይደለም።

ድል ለጀግኖቹ የአማራ ፋኖዎች! 

ድል ለአማራ ህዝብ!

ድል ለኢትዮጵያ አንድነት!

አባሪ መረጃዎች፦

  1. አባ ዳምጠው ተመችቶኛል ምርጫ አልተደረገም ከምትሉ ለምርጫው ያዘጋጀነውሴራ ከሸፈብን ያዋጣል
  2. ነገሩ የማን ስራ እንደሆነ ያልታወቀ መስሏቸው ግልገሎቹ ድንገት እመር ብለው ባንዳ ባንዳ እያሉ ሌላውን አስቀድመው መክሰስ ላይ ተጠምደው ነበር ነበር ዛሬ ማለዳ::
  3. እስክንድር ነጋየአማራ ሕዝባዊ ድርጅትመሪ ማን ነው? | EthioReference
  4. የአማራ ፋኖ በአንድ ዓመት ትግል ጉዞ ውስጥ የተቀናጀው ድል እና ጉድለትበፕ/ ሃብታሙ መንግስቴክፍል ሁለት (2) (youtube.com)
  5. የታላቁ እስክንድር ነጋ ምላሽ የፕ/ ሀብታሙ ተገኝን የብዓዴን ፈረስነት አጋለጠበእነ እስክንድር ላይ የተከፈተው ዘመቻ ምስጢር ተደረሰበትልዪ ዘገባ.. (youtube.com)
  6. በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የአርበኛ ዘመነ ካሴ መግለጫ::
  7. ዘመነ ካሴ ሊበላኝ ነው ሲል የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ
Filed in: Amharic