መሽቶ በነጋ ቁጥር እያነሰ ያለው መረራ
አሸናፊ
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በተማርኩባቸው አመታት ሁላ ነገን በተስፋ እንዳይ እምቢ ባይነትን ነጻነትን አለማጎብደድን አጮልቄ ከማይባቸው ሰዋች መካከል መራራ ጉዲና ነበረ። የሆኑ አመታት ቢሮውን ናቅ አድርጎ ከጎብዳጅ መምህራን ናቅ አዶርጎ መኪናው ውስጥ ሲያነብ ሳየው ልቤ ትሞላለች። በተለይ የሚያስተምራቸው ተማሪዋች አዋቂነቱን ሲያወሩ እደሰት ነበር። ዶር ዳኛቸውም እና እሱን እዚያ ዪንቨርስቲ ማየት ለነገ ለምናፍቀው ነጻነት መስታወት ነበሩ። በተለይ ለብዙ ተማሪ ሲምቦል ነበሩ። እንደዛ ከዛፍ ቅጠሉ የተመለመለ የተማሪ ካድሪ መሀል መንጎራደድ እንዴት ደስ እንደሚል አትንገሩኝ።
አንድ ጊዜ ከአንድ የህወሃት ካድሪ ጋር ላውንጅ ላይ ስናወራ ላናደው ብዪ መረራ እንዴት እንደማደንቀው ስነግረው ። ”ኦሮሞ ነህ” አለኝ ”ብሔር የለኝም” አልኩት ፈገግ ብሎ ”ታዲያ ምን ታደንቀዋለህ እሱ እኮ ከኦነግ የሚለየው አዲስ አበባ መሆኑ ነው” አለ። እኔ ደግሞ አሁን በኢትዮጵያ ስም ቢታገል ለኦሆዲድ እልል በቅምጤ ይሆንለታል። ማህበራዊ መሰረት ያሳጣዋል ለዚያ ነው። ምቹ ሁኔታ ቢመጣ መረራ በእኩልነት የሚያምን ነው አስተሳሰብ እንኳን ለኦሮሞ ለአማረ የሚጠቅም ነው አልኩት ።ያኔ የሳቀብኝ ዛሪም አልረሳውም። ቃል በቃል መረራ አንተ የምትለው አይነት ሰው ቢሆን እመነኝ ወይ እስር ቤት ወይ ውጭ ነበር የሚኖረው አለኝ።
ዛሪ እውነት ሆኖ አገኝሁት። አብይ ሳይላስ ሳይቀመስ ”ኢትዮጵያ” በሚልበት ሰአት ከኦነግም በላይ ኦነግ ሆኖ በከፍተኛ ሁኔታ እረፍት የነሳ የመረራው ኦፊኮ ሆኖ ቁጭ አለ። መረራም መሀል ቁጭ ብሎ ጥላቻ ሲሰበክ በፈገግታ የሚያጅብበት ዘመን መጥቶ ቁጭ። አትጋብ አትገበያዩ ሲባል ያ በእኩልነት በነጻነት ያምናል የምለው ፓለቲከኛው መረራ እግሩን አጣምሮ በጭብጨባ ስምምነቱን ሲገልጽ ሳይ ከልቤ አዘንኩ። ከፍ ብሎ ፓለቲካን ተምሮ ፓለቲካን ያስተማረው የፓለቲካ መሪ የሆነው መረራ አብይን በዲቃላነት በግማሽ አማራነቱ ሊያስጠላ ሲሞክር ሳይ መረራ ድራማ ሲሰራ እንደከረመ አወኩ።
አንድ ቀን ቁልፍ ቦታ ይዞ ኢትዮጵያ ኦሮሞን ሲዳማውን አማራውን ወደፊት ይዞ ይሄዳል ።ለኢትዮጵያ ታስራል ተቃይቷል በደልን ግፍን ጠንቅቆ ያውቃል ብዬ የማስበው መረራ መሀከለኛው መንገድ ነው የኔ መንገድ የሚለውን አብይ ለሱ ሀሳብ ይቀርባል ብዪ የማስበው አብይ መንግስት ላይ ያለ የሌለ ድላውን ያወርድ ጀመረ ። ማረኝ ሌንጮ ማረኝ ዳውድ ኢብሳ አስባለ። በዚያ አፋኝ ገዳይ ፍጽም ዘረኛ አምባገነን መንግስት በትህነግ ኢህአዴግ ዘመን አንድ ጊዜ እንኳን ምርጫ ያላለፈው መረራ በዶር አብይ ዘመን ትንሽ በሯ ገርበብ ባለች ጊዜ ምርጫ አልሳተፍም አለ። እንግዲህ ከትህነግ ኢህአዴግ ኦሆዲድ ብልጽግና ብሳ ማለት ነው። አይገርምም።
ሌላው መረራ ፓለቲካ የተማረው ፓለቲካ ያስተማረው መረራ በወለጋ ያ ሁለ አማራ በገዛ ወንድሞቹ እንደ በሪ ሲታረድ እንደ ሙሁር እንደ አንድ የኦሮሞ ፓለቲካ ኤሊት ተው ማለት ያባት ነው። አንድ ነገር ትንፍሽ ብሎ አያውቅም ለምን ለሱ ከሱ ብሔር ውጭ ሌላው ሰው በታች ስለሆነ ነው። እንግዲህ የኦሮሞ ደም ደሜነው ብሎ ጎንደር ላይ የሞቱት ወጣቶች ነጻነት ለበቀለ ገርባ ያሉ በቅጡ አስረኛን ያልደረሱ ወጣቶች ከሱ የተሻለ የሞራል ከፍታ ላይ እንዳሉ ልብ በሉልኝ። መረራ ፕሮፊሰሩ እንግዲህ ከነኝ ወጣቶች ነው አንሶ የተገኝው። ይሄ ይገርምሀል እንዴ የመረራ መሽቶ ሲነጋ ከዚህም ይከፋል። እንግዲ መንግስት እንደማያስጥላቸው የገባቸው የአማራ ወጣቶች ሁለት ሞት የለም ብለው ኦነግን ሲገጥሙት መረራ ብቅ አለልሀ የእስክንድር ፋኖ በህዝቤ ላይ ግፍ ሰራ ኡኡኡ ይልልህ ጀመረ።
ሌላ ልጨምርልህ የአማራ ክልል የጸጥታ ሀላፊ የነበረው አበረ አዳሙ( የሞተው)በቤንሻንጉል በአማራ ላይ እየተፈጸመ ለነበረው ግፍ የክልሉ ሆነ የፊደራል መንግስት ማስቆም ሲያቅታቸው ልዩ ሀይሉን ይዞ ችግሩ ለመፍታት ለመገንዘብ ቤንሻንጉል መግባቱን በነበረው ኢንተርቪው ላይ ሲገልጽ አንደኛ ወጥቶ ህገመንግስቱን የጣሰ ነው እንዴት ያለ ክልል ፈቃድ ብሎ ኡኡ ያለው መረራ ነው ለሱ የአማራ ነፍስ በአማራ የሚሰራው ግፉ ሁላ አይታየውም ። እራሱን ልከላከል ሲል አይመቸውም።
ማጠቃለያ :-መረራ እኩልነት አያውቅም መረራ ከሱ ብሔር ውጭ ለሌላው ደንታ የለውም። መረራ ዛሪ ተፍቋል መረራ ሌላው ብሔር ሊደግፈው ሳይሆን በየሔደበት ሊያዋርደው ሊቃወመው የሚገባ ሰው ነው። በተለይ የአማራ ኤሊት መጃጃልህን አቁመህ በልኩ ልትነግረው ይገባል።
ቸር እንሰንብት