ምን አይነት ኢትዮጵያ ትመኛለህ?
ምን አይነት ኢትዮጵያ ትመኛለህ?
እኔ፦
መምህር ፋንታሁን ዋቄ
1. የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የምከበርባት አገርና ይህን የሚያስከብር መንግሥት የሚመራት አገር፤
2. ሃይማኖት፥ ባህል፥ ጾታ፥ ቋንቋ፥ ያለፈ ታሪክ፥ አሠፋፈርና የኑሮ ዘይቤ ሁሉ የሰውነትና የዜግነት ማንነቴ ላይ ምንም ተጽእኖ የማያሳድሩብተ ሥርዓተ መንግሥትና ሥርዓተ ማኅበር የሚገለጽባት አገር፤
3. የአገር አስተዳደር አከላለል ከቋንቋና ከፖለቲካ ነጻ ሆነው በልማት ቅልጥፍና፥ በንዑስ ማንነት መዋሃድ መሳለጥ ሚዛን ብቻ የሆነባት አገር፤
4. ፖለቲካ መንግሥት ከሃይማኖት፥ ከጎሣ ቡድን፥ ከቋንቋ፥ ከፖለቲካ ሠራሽ ማንነትና አግላይ ትርክቶች ነጻ ሆኖ ለሰው ክብር፥ ለፍትሕና ለሕዝብ ሰላምና መዋሀድ የሚሠራ የሆነባት አገር፤
5. ወታደር ትጥቅ ይዞ አገር ውስጥ የማይታይባት፥ ድንበር ብቻ በወታደር የሚጠበቅባት አገር፤
6. ፖሊስ ሀብታምና መንግሥት ዱላ ሆኖ ከማገልገል ወጥቶ ሕዝብ የሚጠብቅባት አገር፤
7. ፍትሕ በማሥበራዊ፥ በምንግሥታዊ፥ በሃይማኖታዊና ባህላዊ መዋቅራት ውስጥ ሁሉ እውቅና አግኝቶ የሚተበርበት አገር፤
8. አገርና ሕዝብ ለምግብ፥ ለመድኃኒት፥ አገርን ከውጭ ወረራ ለመከላከል በሚያስችላቸው ግብአቶችና እውቀቶች ሁሉ ከጥገኝነት ነጻ የሆኑባት የሉዓላዊ ሕዝብ አገር
9. ከባእዳን ጋር ተመሳጥረው አገራቸውን የሚወጉ፥ ሕዝባቸውን በሐሰተኛ ትርክትና በተውሶ የፖለቲካ ርእዮት የሚያምሱ አገር-ጠል እና ውጭ ናፋቂ “ምሁራን” ተብዬ የጠላት አገልጋዮች በአገር ክህደት የሚቀጡባት አገር
10. የሐሰት ትርክት ከፍተኛ የአገር ወንጀል የሚደረግባት፥ የፖለቲካ ቁማርና ማጭበርበር በሚት የሚያስቀጣባት አገር።
ይህን አይነት አገር አንዴት እናገኛለን?
የብሔር ፖለቲካና ብሔርተኝነት አይሰጠነም።
ብልጽግና ሕወሃት፥ ኦነግ አይሰጡንም።
ከውጭ የምንዋሰው የፖለቲካ ርእዮትና ውጭ ናፋቂ ምሁራን አይሰጡንም የዚህን አይነት አገር የምናገኘው፦ ሁላችንም ተነስተን
ለክብረ-ሰብእ ስንቆም
ከዘረኛ የቡድን ዕሳቤ ባርነት ራሳችንን ነጻ ስናወጣ
ለፍትሕ ስንሟገትና እኛም በአቅማችን ፍትሓዊ ስንሆን
ከስስት፥ ከቅሚያ፥ ከልዩ ማንነት የፋሽት ፖለቲካ መለየት ብቻ ሳይሆን ጠላታችን ነው ብለን ስነዋጋው
አገራችንን በመስዋዕትነታችን እንደምንጠብቃት ከፋፋዮችን ጠላቶቻችን ናቸው ብለን ስንስማማ
ዐመሓራነትን ከደምና አጥንት ስሌትና ቀመር አስወጥተን ለሁሉም የሰው ልጆች የሚመጥን እሤት ነው ብለን የራሳችን ስናደርገውና አብረን ስንቆም፥
አንዲሁም ዐመሓራነትን ከሕወሃትና ኦነጋዊነት ከብሔርተኝነት መርዝ ስንጠብቀው
(ፋንታሁን ዋቄ/ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም)