>
5:39 pm - Monday February 13, 8699

ኢትዮጵያን ያዋረደ ኹሉ ዕጣ ፈንታው ውርደት ነው፡፡

ኃላፊዋም ሆነች ተከታዩ የኢትዮጵያ ማፈሪያዎች (ባንዳዎች) ናቸው

ኢትዮጵያን ያዋረደ ኹሉ ዕጣ ፈንታው ውርደት ነው፡፡

ከይኄይስ እውነቱ

ርእሰ ጉዳዬ የትግሬ ወያኔና የኦነግ/ኦሕዴድ ዋና አሽከሮች በመሆን ኢትዮጵያን በማፍረሱ እና የዐምሐራን  ሕዝብ በማስጨፍጨፉ ሒደት አባሪ ተባባሪ የሆኑትን፣ ‹ብልግና› የሚባለው የዱርዬዎች አገዛዝ ‹ፕሬዚዳንት› የነበረችውን እና አሁን የሆነውን ግለሰብ ይመለከታል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ራሳቸውን በፈቃዳቸው ያዋረዱ ምናምንቴዎች በመሆናቸው ክብርና ማዕርግ መስጠት የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅ ስለሚሆን ለከሃዲ (ለባንዳ) በሚመጥን አገላለጽ እየተናገርሁ አጠር ያለ አስተያየቴን አቀርባለሁ፡፡ 

አንዳንድ ሰዎች ብአዴን የሚባለው የዓለሙ ማፈሪያ ቡድንና አባላቱ ሲነሡ የሚነዝራችሁ እንዳላችሁ ታዝበናል፡፡ በጽኑ ደዌ የተያዛችሁ በመሆኑ ለእናንተ ከማፈርና ከማዘን ያለፈ ምን ማለት ይቻላል? የዐምሐራ ፋኖ ትግል አንዱና ዐቢዩ ፈተናም የብአዴን ሠርጎ ገብነትና ከዚህ ነውረኛ ቡድን ጋር ያለ ንኪኪነት መሆኑ አይካድም፡፡  አንዳንዶቻችሁ በምታገኙት መድረክ እንዲህ ስትሉ ትደመጣላችሁ፤ ‹‹ ‹የኛ ሰዎች› ላይ በነቀፋ ትበረታላችሁ፤ ወያኔና ኦነግ የራሳቸውን ሰዎች አሳልፈው አይሰጡም፡፡ ገመናቸውን ይሸፍናሉ፡፡›› በቅድሚያ ‹የእኛ ሰዎች› ማለት ምንድን ነው? ‹እኛ› የሚለው ኢትዮጵያን ወይም የዐምሐራን ሕዝብ ወክሎ የተነገረ ቃል ከሆነ እነዚህ ሰዎች በየትኛውም መመዘኛ ‹ኢትዮጵያዊ ወይም ዐምሐራ› አይደሉም፡፡ እነዚህ ‹ካልዓን› ፍጥረታት ከውልደታቸው አሁን እስከሚገኙበት ጻእረ ሞት ዘመናቸው ኢትዮጵያን በማፍረስ፣ ዐምሐራን ከገጸ ምድር ለማጥፋት ሌት ተቀን ሲሠሩና እየሠሩ የሚገኙ በመሆናቸው ‹የእኛ› ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ባንፃሩም የነውረኛ ምናምንቴን ገመና መሸፈን ወንጀልም ኃጢአትም ነው፡፡ እንደ አገር የገዘፈን ነውር እየሸፈኑ፣ ባንደበት ለመግለጽ የሚከብድ ወንጀል የፈጸሙ ጉዶችን ከተጠያቂነት ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ ቀጣዩ ትውልድ ምን ሊማር ይችላል? በመሆኑም አጋንታታዊ ቡድኖች የሆኑት ወያኔም ሆነ ኦነግ/ኦሕዴድ ለበጎ ምሳሌነት ሊቀርቡ አይችሉም፡፡ ለፖለቲካ ትክክለኛነት ሲባል ነውርን መሸፈን እውነተኛ ኅብረትና አንድነትን አይፈጥርም፡፡ በሐሰት ላይ የሚመሠረት ፖለቲካም ሆነ ድርጅት በድቡሽት ላይ የተመሠረተ ቤት ነው፡፡ እነዚህ ብአዴኖች እንደ አስቆረቱ ይሁዳ ለንስሓም ዕድል የሌላቸው ናቸው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ለከንቱ ክርክራችሁ ዲያቢሎሳዊ ጥቅስ ለመጥቀስ የምትሯሯጡ እንዳላችሁ አስተውለናል፡፡ ማተብ ካላችሁ የኢትዮጵያ ወይም የዐምሐራው ሕዝብ ሰቆቃ የሚገዳችሁ ከሆኑ ተዉ እረፉ፡፡

በወያኔና ተወራጁ ኦነግ/ኦሕዴድ ዘመን የአገር ፕሬዚዳንትነት በጽሑፍ የይስሙላ ሹመት ሲሆን፣ በተግባር ደግሞ የበለጠ ሥልጣን አልባ የጐሣ ኮታ ማሟያ ቦታ መሆኑ የዐደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን የሚያስቀድም፣ ክብርና ልዕልናዋን፣ ዕድገትና ልማቷን፣ ሰላምና ጸጥታዋን ወዘተ. የሚመኝ ኢትዮጵያዊ በነዚህ ፋሺስታዊ አገዛዞች ይህንን ማዕርግ አይመኘውም፤ አይፈልገውም፡፡ ምናልባት ቀዳዳ ካገኘሁ ታሪክ ሠርቼ አልፋለሁ የሚል ጥብዐት ያለው ሰው ካልሆነ በቀር፡፡ መጫወቻ አሻንጉሊት እንደሚሆን በሚገባ ይረዳልና፡፡ 

‹ለሴትየዋ› የኢትዮጵያ ሕዝብ በርካታ ዕድል ሰጥቷት ነበር፡፡ በብአዴን ነቀርሳ የተያዘች ናትና ልትጠቀምበት አልቻለችም፡፡ ታሪኬ ውርሴ በመጥፎ እንዲነሣ አልፈልግም ብትልም ሥራዋ ሁሉ እስከተሰናበተችበት ዕለት ከአጽራረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ጋር መሰለፏን በጉልህ የሚመሰክር በመሆኑ በዮዲት ጉዲት መንፈስ መታሰቧ አይቀሬ ነው፡፡

እነዚህ ኹለት ነውረኛ ግለሰቦች የረዥም ጊዜ ሙያቸው ‹ዲፕሎማቶች› (career diplomats) መሆናቸውና በተለያዩ አገሮች አምባሳደር ሆነው መሥራታቸው ይነገራል፡፡ በዚህ ችሎታቸው ላገር ምን አስተዋጽኦ አድርገዋል የሚለው የዚህ ጽሑፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ በቀድሞ ሙያቸው በበጎም ሆነ በመጥፎ የሚነሣ ተግባራቸው አሁን ለተነሣንበት ርእስ አግባብነት የለውምና፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን እንደሚያስተምሩን በመንፈሳዊ ሕይወት፣ እንኳን ኀጢአት ያለፈ ጽድቅም ረብ የለውም፡፡ አሁን የሰይጣን ገንዘብና አገልጋይ ከሆኑ ምን ትርጕም አለው? የተጠቀሱት ነውረኞች መጨረሻቸው አድርባይነት፣ አሽከርነት፣ ምናምንቴነት ሆኖ፣ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አፍራሽ ኃይሎች (ሥጋ ከለበሱ አጋንንት) ጋር በአባሪ ተባባሪነት ሠርተዋል፡፡ በዳተኝነትና በሚያስደነግጥ ዝምታቸው፣ ዐምሐራን ማጥፋት ቀዳሚ ዓለማው አድርጎ ለሚንቀሳቀስ ፋሺስታዊው አገዛዝ አገልጋይ በመሆን የዐምሐራ ሕዝብን አስፈጅተዋል፡፡ ብአዴንነት የምድራችን ዝቃጭነት/ቆሻሻነት ነው፡፡ ብአዴንነት ከሃይማኖት መልካም እሤቶች፣ ከሰብአዊነት፣ ከፍትሕ፣ ከሥነ ምግባርና ግብረ ገብ መራቆት ነው፡፡ ብአዴንነት ለሰዎች መከራና ስቃይ ግዴለሽ መሆን (absence of sympathy and empathy) ነው፡፡ ብአዴንነት የዘረኞች ‹ሽንትነት› ነው፡፡ ብአዴንነት አእምሮን/ሕሊናን ለዘረኛ ፋሺስቶች አስረክቦ ግዑዝነትን ገንዘብ ማድረግ ነው፡፡ ባጭሩ ብአዴንነት ከሰውነት መጉደል ነው፡፡ ሰብአ ትካት (የኖኅ ዘመን ሰዎች) በፈጸሙት ነውር እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በመፍጠሩ እንደተጸጸተ ሁሉ አሁንም ብአዴን የሚባሉ ‹ካልዓን/ልዬ› ፍጥረታትን በመፍጠሩ እንደሚጸጸት ይሰማኛል፡፡ እነዚህ ኹለት ጉዶች በጥቂቱ የጠቀስነውን የብአዴን ባሕርያትን ነው የሆኑት፡፡ እንዲህ ተርመጥምጦ መልካም ዝና መልካም ውርስ ማሰብ የጤና ሊሆን አይችልም፡፡ የነዚህን ብአዴናውያን ነውር የበለጠ የሚያከብደው ፊደል ቈጥረናል ማለታቸውና ሽበታቸው የእንጨት መሆኑ ይመስለኛል፡፡ የነውረኛ ጽዋ ተርታ በታሪክ ጥቁር መዝገብ ተጽፎ የተከታታይ ትውልድ ተወቃሽ ማፈሪያ መሆን ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ያዋረደ ወይም ካዋረዱ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ያገለገለ ሁሉ ዕጣ ፈንታው ውርደት ብቻ ነው፡፡

በመጨረሻም ጭንቀታችን በቁማቸው ለሞቱት ሳይሆን የዐምሐራውን ሕዝብ ህልውና አስከብሮ አገራችን ኢትዮጵያን ከዘረኛ ፋሺስቶች ይታደጋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የዐምሐራ ሕዝብ (ፋኖ) ትግል ሊሠምር የሚችለው ራሱን ከወያኔና ኦነግ ዓላማ በተለይም ከአሽከራቸው ብአዴን ሙሉ በሙሉ ሲያጠራ ብቻ ነው፡፡ በርጉም ዐቢይና ተላላኪዎቹ ሕዝቡን ከማስጨረሱ በፊት ብአዴናውያኑን ያለምንም ርኅራኄ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ በአራቱም ክፍላተ ሀገራት ያለው ሕዝብ እነዚህን ነውረኞች ታቅፎ የመቀመጥ ትዕግሥት ከየት አገኘ? ባንፃሩምና ከ‹ብልግናው› አገዛዝ ተፋትተናል የሚሉም ካሉ (አመኔታ ሳይሰጡ) በትግሉ ውስጥ ምንም ድርሻ እንዳይኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አርፈው ከተቀመጡ በራሱ ትልቅ አስተዋጽኦ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ‹የ ያ ትውልድ› የሚባሉትና የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቆሻሻ፣ የአድማ፣ የሤራና የመጠላለፍ አልፎ ተርፎም የዘረኛነት ያደረጉት ነውረኞች (ንስሐ የገቡትን አይመለከትም) በፋኖ ትግል ውስጥ ድርሽ እንዳይሉ መጠንቀቅ ያሻል፡፡

ከባለቤቱ ያወቀ… ነው ቢባልም የማይተካ ሕይወታችሁን ለተቀደሰ ዓላማ እየሰጣችሁ ያላችሁ በአራቱም የዐምሐራ ጠቅላይ ግዛቶች የምትገኙ የዐምሐራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አመራሮችና ሠራዊቱ፣ ዐዲስ አበባ ውስጥ (የመጨረሻውን ምዕራፍ ሳይጠብቅ) ዒላማና ዓላማ ያላቸው ተከታታይ ኦፐሬሽኖች የሚያስፈልጉ አይመስላችሁም? ነፍሳቸውን በገነት በመንግሥተ ሰማያት ያኑርልንና፣ የወንድሞቻችን የነ ፋኖ ናሁ ሠናይ ኦፐሬሽን የመጨረሻ እንዳልሆነ እረዳለሁ፡፡ ይሄን የሰይጣን ቊራጭና ግብረ አበሮቹ በእውር ድንብርም ቢሆን እንደፈለጉ እንዲፈነጩና ሕዝባችንን እንዲፈጁ የሆነው እኮ አንድም የሚያስደነግጣቸው ጠፍቶ ይመስለኛል፡፡ አንድ ወንድማችን በፋሺስቶቹ እየተካሔደብን ያለው ጦርነት ዘረፈ ብዙ ነው እንዳለው ሌሎቹንም ጦርነቶች ለማስቆም ስለሚረዳ በተለይ የሺዋ ፋኖዎች አስቡበት፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ፡፡

Filed in: Amharic