>

ፅናትህን ልብህ አድርገው ፤

ፅናትህን ልብህ አድርገው ፤

 

አየህ ምልክትህን ለማጥፋት ሲራወጡ፣
ጽናትህን ሊቀሙ፣ ሲቋምጡ፣ ሲያምጡ።

እሱ እንደሆነ አንድ ጊዜ – ስሙን ተክሏል።
”ጽናት” ብለህ – የምትጠራው፣
”ታጋይ” ብለህ ‘ምታከብረው፣
እስር ግርፋት ያልበገረው ፣

ለወገኑ ስቃይ፣ መሬትን ‘እፍ’ ብሎ ለመተኛት ያልገደደው፣

እዚያው በረሐ ላይ ከወንድሞቹ ጋር የሚገኘው፣

የወረቀት ነብር  ያልሆነው፣

ቃልን ከተግባር ጋር ያገናኘው፣

እስክንድር ነጋ ነው።

ሆዳምና ብአዴኖች፤ ከያሉበት ተሰባስበው፣
ተጠቃቅሰው፤
ክፉ ሴራ በጣፋጭ ለውሰው።

ሲያጃጅሉህ፣ ሲያዋክቡህ
የተሰራ በላይህ ላይ ሊንዱብህ፣

ሲያቃትቱ፣ ሲያጣጥሩ፤
ሲቆፍሩ፣ ሲቦረቡሩ፤

ይሉኝታ የሚባል ያልገባቸው፤

እያየሃቸው ዝም ካልካቸው፣
ካልመረርክባቸው…!

እነዚህ በጣም ጨካኞች ናቸው።

እናም… ወዲያ አትበላቸው፤

አውቀህ ነቅተህ ተከታተላቸው።

ስንት ጊዜ ይሸውዱህ?
በቁመናህ ይገዝግዙህ!?

ምልክትህ ላይ ቁማር ሲጫወቱ፥

አቋምህ ላይ ሲዛበቱ።

እንደ አዞው – ያነባሉ…
እያ’ባ’ሉ።

‘ደም’ የተከፈለበትን መስዋዕትነት፥

ውሃ እየቸለሱበት።

ዝም አትበላቸው!

ፅናትህን ልብህ አድርገው ፤

ያን ጊዜ ነው ‘ምታሸንፈው!

 

”ዕውነት” ውስጥህ ከሌለ ግጥም አይመጣምና  በእስክንድር ነጋ ላይ ለተከፈተው ዘመቻ በግጥም የተሰጠ ምላሽ

ግርማ እንድሪያስ ሙላት

girma077@gmail.com

Filed in: Amharic