>

የእስክንድር ነጋ መሰረታዊ ችግሮች፤ ለቅን አማሮች...

የእስክንድር ነጋ መሰረታዊ ችግሮች፤ ለቅን አማሮች…

 

ትእግስት ዘገየ

 

የእስክንድር ነጋ አንዱና ዋናው ችግሩ ሁሉም ሰው ለሽ ብሎ ተኝቶ ሳለ እርሱ ቀድሞ ይነቃል! ለምሳሌ፡ሁሉም ተሰብስቦ አብይ ፣ አብይ ፣ ሙሴ፣ ሙሴ ሲል ፣ እርሱ ግን ብቻውን ምንድነው የምታወሩት? አብይ እኮ ሙሴ አይደለም! ፈርዖን ነው! አለ።

የአብይ አህመድ ጭምብል ብዙ ሳይጓዝ በአስክንድር ነጋ ተገፈፈ! አብይ አህመድን ርቆ ሳይጓዝ እርቃኑን አስቀረው! ይህን ያየው አብይ አህመድ ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው! በአደባባይ ከእስክንድር ጋር “ወደ ለየለት ጦርነት እንገባለን!” አለ ።

አብይ አህመድ ከፍሎ ያሰማራው እንዲሁም ወዶ ገብ ግሪሳ ተቆጣ ፣ ሁለገብ ዘመቻ ተከፈተበት! ጭር ሲል የማይወድ፣ የመቃወም ሱስ ያለበት፣ እብድ ተባለ! እርሱ ግን በአቋሙ ፀና። ተሳደደ፣ ታሰረ፣ ተገረፈ!

እርሱ ግን የያዘውን እውነት ይዞ በውጭ የተባበሩት መንግስታት ድረስ እና በሀገር ውስጥ ተንከራተተ! የሚሰማው አላገኘም! ሲብሰው ነፍጥ አንግቦ ጫካ ገባ! በቃ ሸፈተ!

ያኔ እብድ ፣ ጭር ሲል የማይወድ ሲለው የነበረ የአዲስ አበባ ህዝብ አሁን በተራው እያበደ ብቻውን እያወራ ይገኛል! “ምከረው ፣ ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው። ” እንደተባለ።

አይገርምም: አሁንም ታዲያ ታሪክ ራሱን ደገመ! ሣልሣይ ብአዴንን ለማዋለድ አንዳንድ “ስመ ጥር ፋኖዎች” / የብአዴን ልጆች ውር ውር ሲሉ ከሰው ሁሉ ቀድሞ እስክንድር በንስር አይኑ አያቸው! ነቃባቸው!! ጥቂት ሳይጓዙ ጭምብላቸውን ገፈፈባቸው! ተወራጩ! ተናደዱ ! ተበሳጩ!

በሣልሣይ ብአዴን እሰክንድር ላይ ሁለተኛው ጦርነት ተከፈተበት!

They were so furious! Man!

ያገኙትን ሀሉ ወረወሩበት! ተረባርበው፣ ግሪሳ አሰማርተው ፣ ተሳዳቢ ቀጥረው፣ በተለያየ ሚዲያ 24/7 ጭቃ ቀቡት! የተለያዩ ስሞች ሰጡት!

የቀድሞ የብአዴን ወጣት ሊግ አባላት በተለይ ዘመነ ካሴ፣ አስረስ ማረ እና አበበ ፈንቴ እንደ አብይ አህመድ ሁሉ ስሜታቸውን መቆጣጠር አልቻሉም! አበበ ፈንቴ እንደ አብይ አህመድ ሁሉ እየተወራጨ በአደባባይ ” በርባን” አለው!

እስክንድር በእርግጠኝነት ነርቫቸውን ነክቶታል!አከርካሪያቸውንም ባልጠበቁት ጊዜ ሰብሮታል!

አእምሮ ካለህ ይህ ሁሉ የተቀናጀ ዘመቻ በአንድ ግለሰብ ላይ ለምን ተከፈተ? ብለህ ጠይቅ!

በተለይ በማረጃ ቴሌቭዥን በዘመድኩን ሸቀለ፣ በሮሃ ሚዲያ በመዐዛ መሀመድ ፣ በግዮን እና ABC ቴሌቪዥን የተናበበ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈቱበት! እነምሬ ወዳጆ እና አዛውንቶቹን በማደናገር አፋቸውን እንዲከፍቱበት አድርገው ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ሰሩ።

የሚሰራ አእምሮ ካለህ….

# እነዚህ ሚዲያዎች ምን አገናኛቸው?

# እስክነ‍እድር ነጋ ከትግል ሜዳ እንዲወጣ አብይ አህመድ እና የሣልሣይ ብአዴን አዋላጆች በጥምረት ለምን አበክረው ፈለጉ?

# እነዚህ ሚዲያዎች ዐማራውን እለት እለት በድሮን በጅምላ ከሚፈጀው አብይ አህመድ ይልቅ ለምን እስክንድር ነጋ ላይ አተኮሩ? ብለህ ጠይቅ!

የሣልሣይ ብአዴን አዋላጆች እና የብልፅግና ተቀጣሪ ሚዲያዎች እንዲሁም ከ250 ሺህ በላይ ብልፅግና ቀጥሮ ያሰማራቸው የማህበራዊ ሚዲያ አርሚ/ግሪሳዎች ስምሪት ተስጥቷቸው ፍፁም ባልዋለበት እየወነጀሉ ሲያብጠለጥሉት ይውላሉ። እንደ ክርስቶስ ይሰቀል፣ ይሰቀል፣ ይሰቀል የሚሉ ድምፆች ጎልተው ይሰማሉ። ክርስቶስ በሀሰት ወንጅለው የሰቀሉት ተረፈ አይሁድ ዛሬም አደባባዪን ተቆጣጥረውታል።

አዎ በእርግጥ እስክንድር ችግር አለበት! አርፎ እንደሌላው ለሽ ብሎ አይተኛም! ቀድሞ ይነቃል!

ትእግስት ዘገየ

 

Filed in: Amharic