>

የዘመነ ካሴ ያልዘመነ ፍኖት

የዘመነ ካሴ ያልዘመነ ፍኖት

 

ከጥቃቅንና አነስተኛ የመንደር አስተሳሰቦች (አሳቢዎች)፣ ትላልቅና ሀገር የሚያሻግሩ እሳቤዎችን ማግኘት አይቻልም። 

ዘሜ ማለት ገና ከጎጥ ፓለቲካ አስተሳሰብ ያልተላቀቀ፣ ከእርሱ ውጭ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች በጠላትነት የሚያይ፣ በማሰር፣ በማሳደድና በማጥፋት የሚያምን ያልሰለጠነ ፓለቲካ የሚያራምድ ግለሰብ ነው!

በነገራችን ላይ ዘሜ ብየ የማቆላምጠው የሚያራምደውን ሃሳብና የሚሄድበትን መንገድ እንጂ እርሱን ስለማልጠላው ነው። ዘሜን መተቸትና መሞገት ጠላትነት አይደለም። ይህ ይሰመርልኝ።

ማንም የማይክደው ዘሜ አንድ በጣም የሚችለው ጥሩ ነገር አለው። በአማለይ ቃላት የታጀቡ አነቃቂ ንግግሮች (motivational speech) ማድረግ ፣ ሰዎችን መቀስቀስና ማማለል ነው። በእርግጥ ይህ ጥሩ ፀጋ ነው። ለመሪነት ግን ብቻውን በቂ አይደለም። 

ከዚህ ውጭ በአደገኛ ego የተወጠረ፣ ከፍተኛ የስልጣን (የንግስና ጥማት) ያለበት፣ ውሸታም፣ ሞራል የሌለው ግለሰብ ነው። ለዚህም ነው ከብአዴን ከድቶ ወደ ግንቦት ሰባት ኤርትራ በረሃ ከገባ በኋላ ወደ ኢትዮዽያ ተመልሶ እነደ እርያ ወደ ትፋቱ ተመልሶ ብአዴን የሆነው። የአሳማዎች ስብስብ ብአዴንም ስልጣን ሰጥቶ አሰማራው። 

አሁን ደግሞ ከዐማራ ፋኖ ወደ ሣልሣይ ብአዴን አዋላጅነት ነው የተሸጋገረው። ዘሜ ይህ ነው የሚባል የፓለቲካ እሳቤ ፣ መርህ የሚባል ነገር የለውም! ሃፍረት የሚባል ነገር እርሱ ዘንድ የለም። ትልቅ መስቀል በአንገቱ አንጠልጥሎ እነደ ዘመድኩን ሸቀለ በአደባባይ ነጭ ውሸት ይዋሻል። አክሮባት ሲሰራ አይነግርህም። ድንገት ሲታጠፍ ፍሬቻ አያሳይህም። 

እንዲህ ያሉ ግለሰቦች በፍፁም እምነት ሊጣልባቸው አይችልም። ለስልጣን ሲሉ የማይፈፅሙት ነገር የለም! ለዚህ ነው ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው፣ ዶ/ር እንዳላማው ፣ አርበኛ እስክንድር ነጋ፣ ኮሎኔል ጌትነት ሌሎችም በዚህ ግለሰብ በአደባባይ የተካዱት! እንዲህ ያሉ ሞራለቢስ ግለሰቦች እንኳን ሀገር ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ማሻገር አይችሉም! ለዚህ ጥሩ ምሳሌ እሩቅ ሳንሄድ አብይ አህመድን እናገኛለን። 

ሲጀመር ዘመነ የሃሳብ ፓለቲካ ማራመድ አይችልም። የመጣበት( ያደገበት መንገድ )  track record ይህን አያሳይም። በዲሞክራሲአዊ መንገድ በምርጫ አሸንፎ ስልጣን ስለመያዝ (ስለመንገስ) ማሰብ አይቸልም። በብአዴን ቤት የምርጫ ኮሮጆ ሲገለበጥ እያየ ነው ያደገው። የሌለውን ከየት ያመጣዋል። ለዚህ ነው ለዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ሁለት ጊዜ በእጩነት ቀርቦ ሲሸነፍ ወደ ኮሮጆ ግልበጣ የተሰማራው። 

አሁን ባለው ሀኔታ ዘመነ ካሴ ቅልጥ ወዳለ የሴራ ፓለቲካ ውስጥ ገብቶ እየዳከረ ይገኛል። ይህቺ ከህወሃት የኮረጃት ክፉ ትምህርት በደሙ ውስጥ ተሰራጭታ እያቅበዘበዘችው ትገኛለች። የእርሱ ጭንቀት ከእርሱ ውጭ ያሉ የዐማራ ፋኖ አደረጃጀቶችን እንዴት ማፍረስ (ማስገበር) እንደሚችል፣ እንዴት አድርጎ ብቸኛ ንጉስ ሆኖ ሊወጣ እንደሚችል እንቅልፍ አጥቶ ማለምና ማቀድ ብቻ ነው። ተኝቶም ተነስቶም የሚያልመው ይህንን ነው። 

Mark my words!

ዘመነ ካሴና የሳልሣዊ ብአዴን ስብስቦችን መንቅሮ ማውጣት እስካልተቻለ ድረስ  የዐማራ ፋኖ አንድነትን ማሰብ በፍፁም አይቻልም! ለዚህ ማሳያው ደግሞ እየሄደበት ያለው መንገድ ነው!

የዘመነ መንገድ የአመለካከት ልዩነት እንኳን ቢኖረንም አንድ የጋራ ዓላማ እስካለን ድረስ እንዴት ይህን ሃይል አስተባብረን የአብይ አህመድን ገዳይ ስርዓት ማሸነፍና የዐማራን ህዝብ መከራና ሰቆቃ ማሳጠር እንችላለን የሚል አይደለም። ከዚህ ይልቅ ለዐማራ ህዝብ ሊሞቱ የወጡ የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶችን ማፍረስንና ማዳከምን እንደ ግብ ይዞ የዐማራን ህዝብ ትግል በመጎተት ላይ ያተኮረ ነው። 

ጎንደር ተሻግሮ ጎንደርን በመከፋፈል፣ ወሎ ተሻግሮ ኮሎኔል ፈንታሁን ላይ በመዝመትና በማዘመት፣ ሸዋ ተሻግሮ ክፍለጦሮችን በመከፋፈል፣ ጎጃም ላይ ለዐማራ ሊሞቱ የወጡትን በሌሎች አደረጃጀቶች ውስጥ ያሉትን የዐማራ የቁርጥ ቀን ልጆች በማደናገርና በማፍረስ ተግባር ተጠምዷል።

ለመሆኑ ትግሉን የጎንዮሽ መልክ በማስያዝ ምን አይነት ድል ይገኛል? እንዲህ አይነቱ የጎንዮሽ ትግል አብይ አህመድን ወይስ የዐማራን ህዝብ ይጠቅማል? 

በእርግጥ በዙሪያህ ያሉ አማካሪዎችህ ይህን ደፍረው አይነግሩህም። እውነት ለመናገር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪህ ዘመድኩን ሸቀለ መሆኑን ባወቅነ ጊዜ እኛም አፍረን ጥፍራችን ውስጥ ተደብቀናል

ዘሜ ሆይ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ወደገደል አፋፍ ስትንደረደር እያዩህ እስክትወድቅ ድረስ ያጨበጭባሉ። እነዚህ ሰዎች ካንተ በፊት ለነበሩትም እንዲሁ ሲያጨበጭቡ ነበር። ከአንተም በኋላ ለሚመጣው ያጨበጭበሉ። ለምን እነደሚያጨበጭቡ ቆም ብለህ ብትጠይቃቸው አጨብጭቡ ስላልከን ነው የሚሉህ። እባክህ ስላጨበጨቡልህ አተዝፈን። 

To tell you the truth, አሁን አንተ የተከተልከው መንገድ እጅግ ቀላል መንገድ ነው። ብዙም እውቀት አይጠይቅም። በእርግጠኝነት ሌሎቹ እንዳተ ያላደረጉት ሞራል ያላቸው ሰዎች ስለሆኑና ለትግሉ የወለዱት ልጅ ያህል ስለሚሳሱ ብቻ ነው። ተሻግረህ እነርሱ ያደራጁትን ስታፈርስ ፣ ተሻግረው አንተ የገነባኸውን ሲያፈርሱ ያላየኸው ማፍረስ ከባድ ሆኖ ሳይሆን ስብእናቸው እና ሞራላቸው ስላልፈቀደላቸው ብቻ ነው።

” የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊባጅ

የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጅ”

ወደሚል ከንቱ መጓተት ለምን ትገፋቸዋለህ? ለምንስ ትፈታተናቸዋለህ? ላንተ የተፈቀደው ዐማራን አደራጅቶ ማታገል ለሌሎች የዐማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ያልተፈቀደው ለምንድነው? በዚህስ ማን ማንን ያሸንፋል? 

አዝማሪዋ

“እንረስ ካላችሁ ተባብረን እንረስ፣

እንተወው ካላችሁ ተውት ዳዋ ይልበስ፣

የእናንተ ፈርሶ ነው የኛ ቤት የሚፈርስ፤”

እንዳለችው ነገሩን ወደሌላኛው ጫፍ ባትጎትተው ለአንተም ይሻልሃል። እዚህም ቤት አላያያዝነውም እንጂ እሳት አለ! 

ሁላችንም እንደምናውቀው አንድን ቤት መስራት የማፍረስን ያህል ቀላል አይደለም። 

ቤት ማፍረስ ምንም አይነት እውቀት አይጠይቅም! ቤት መስራት ግን እውቀት ይፈልጋል። የመስሪያ ቦታ መምረጥ፣ ለስራው የሚያስፈልግ ማቴሪያልና ገንዘብ ማሰባሰብ፣ የቤት ዲዛይን መምረጥና መስራት፣ ዝርዝር weight/load analysis፣ ልኬት፣ እያንዳንዱን በቅደም ተከተል በጥንቃቄ ሰፍሮ ማስቀመጥ ይጠይቃል። ቤት ሲሰራ ወራትና ዓመታት ይፈጃል። ሲፈርስ ግን አንድ ቀን ይበቃዋል። ያልሰለጠነ ግሪሳ በማሰማራት በሰዓታት ውስጥ ማፍረስ ይቻላል። 

ሰሞኑን እስክንድር ወጥቶ ወርዶ መልምሎ አንድ ነፍሳቸውን ለዐማራ ወገናቸው እንዲሰጡ አሳምኖ በዓባይ ሸለቆ ያደራጃቸውን የዐማራ ፋኖ ታጋዮች ዘሜ በማፈራረሱና በማስገበሩ እዛ ሰፈር አታሞ ሲደለቅ ተመልክቸ አዘንኩ። እልልታው ልክ የሰው በላው የአብይ አህመድ ገዳይና ደፋሪ ሰራዊት እጅ የሰጠ ይመስል ነበር። 

ለመሆኑ እነዚህን ልጆች የዐማራን ህዝብ እንዲታደጉ አንቅቶ ያደራጀው ነው ጀግና ያፈረሰው? 

ከዚህ ቀደም ዘሜንና አብይ አህመድን የሚያመሳስላቸውን ጉዳዮች አመላክቸ ነበር። እንደ አብይ አህመድ እናቱ ትነግሳለህ ማለቷን እንጃ እንጂ የስልጣን ጥማታቸው እና ይህን ለማሳካት የሄዱበት መንገድ ተመሳሳይ ነው። 

በጊዜው አብይ አህመድ ሙሴ ነው፣ አሻጋሪያችን ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በተቀጣሪ የሚዲያ ግሪሳ / army ሰፊ የገፅታ ግንባታ ተሰርቷል። አሁንም በተመሳሳይ ዘሜ አሻጋሪአችን የሚል ተመሳሳይ ዘመቻ እያየን እንገኛለን። 

እኛም እንላለን ዘሜ ሆይ እባክህ መጀመሪያ ራስህን ችለህ ተሻገር። 

ዘሜ ሆይ በመጠላለፍና በሴራ ያሰቡትን ያህል ርቆ መጓዝ እንደማይቻል ከህወሃት፣ ከብአዴንና ከኦህዴድ ባለስልጣናት ለመማር ሞክር። 

ዘሜ ሆይ እባክህ 

“ጉድጓድ አትቆፍር፤ ከቆፈርክም አርቀህ አተቆፍረው፤ የሚገባበት አይታወቅምና!”

 

ዳግማዊት ጌታነህ

Filed in: Amharic