እየተገባደደ ባለው በ2024 ዓ.ም ፋኖ ያከናወናቸው ታላላቅ ስራዎች
የፋኖ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ከትግል ልምዱ በላይ የሆነ ወታደራዊ ሥርዓት ይዟል፡፡ በተለይም የምርኮኛ አያያዙ ዓለማቀፍ የጦር ሕጎችን ያከበረ ሆኖ በመገኘቱ የጠላትን የታችኛው መዋቅር ቀልብ በመግዛት ከስር ለማፍረስ ጠቅሞታል፡፡ የብልጽግና ሰራዊት ‹የምርኮኛ አያያዛችሁ ጥሩ እንደሆነ ሰምተን ነው እጅ የሰጠነው› ብሎ ስለፋኖ ወታደራዊ ዲሲፕሊን እስከመመስከር ደርሷል፡፡ ይህ ትልቁ የድል ማሳያ ነው፡፡
• የፋኖ ትግል ሥነ-ምግባር ያለው ሕዝባዊ ትግል መሆኑን ዓለማቀፉ ማኀበረሰብ በግልጽ እየታዘበ ነው፣
• የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ እስራኤል ዲፕሎማቶች የፋኖ መሪዎችን ለማነጋገር፣ የትግል ሀሳባቸውን ለማዳመጥ ተገደዋል (ይህም ለትግሉ ዕውቅና እንደሰጡ ይቆጠራል)
ጠላት ልምድ ያላቸው ሰራዊቶቹን እና ዕዞቹን ጨርሶ በየወሩ በሚባል ደረጃ የኮማንዶ እና የወታደር ምረቃ እና ምልመላ ላይ ተጠምዷል፡፡ የሰው ኃይል ቋቱ ተመናምኗል፡፡ ጠላት ቢጨንቀው ፋኖን ለመከፋፈል በሴራ ቢጠመድም ሊሳካለት አልቻለም፡፡ የአማራ ፋኖ አቅም ከጠላት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም በላይ አልፎ ሂዷል፡፡
ከብዙ ወሳኝ ድሎች ውስጥ እጅግ በአጭሩ አስር ነጥቦችን አውጥተን በተመለከትነው የ2024 የአማራ ፋኖ ስኬት ውስጥ፡- የፋኖን የአንድ ዓመት የድል ጉዞ በሦስት ነጥቦች ጠቅለል አድርገን ልናየው እንችላለን፡፡ የአማራ ፋኖ በዚህ ትግል ውስጥ ጀግንነት፤ ተሻጋሪ ድል እና የትግል አቃፊነትን አሳይቷል፡፡
ለአማራ ሕልውና ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ አገረ-መንግሥት ሕልውናም ዋስትና የመሆን አቅሙን አሳይቷል፤ እያሳየም ነው፡፡
ይህም ሲባል፡-
• የፋኖ ጀግንነት፡– ከዋና ዋና የውጊያ ቀጠናዎች አልፎ እስከ አፍንጫው በታጠቀ የሪፐብሊካን ጋርድ በምትጠበቅ (አዲስ አበባ) ከተማ በውስን አደረጃጀትና በተመጠነ አቅም በሻለቃ ፋኖ ናሁሰናይ አንዳርጌ መሪነት ኦፕሬሽን በመስራት አቅሙን አሳይቷል፤ (ይህ በፋኖ ትግል ታሪክ የዓመቱ ልዩ ኦፕሬሽን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ አጼዎቹ ክፍለ ጦር እና የሸዋ ጠቅላይት ግዛት ዕዝ አጼ ዳዊት ክፍለ ጦር የተውጣጡ የአማራ ልጆች፣ ሚያዚያ 4/2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ላይ የመጀመሪያዋን ጥይት በመተኮስ ትግሉን አሳድገውታል)
• የፋኖ ተሻጋሪ ትግል ራዕይ፡– የፋኖ ትግል ‹‹አማራ ክልል›› ተብሎ እንደአጥር ከተከለለው ወጥቶ፣ በኢትዮጵያ ዋና መዲና (መሀል ሸዋ) ላይ የትግል መረቡን መዘርጋት ችሏል፤ ይህም የትግሉ ዕድገት የታየበት፤ ፋኖ ተሻጋሪ የትግል ራዕይ እንዳለው ያሳየበት ነው፡፡
• የፋኖ ትግል አቃፊነት፡- የፋኖ ትግል ከአማራ አንድነት ባሻገር የኢትዮጵያ የለውጥ ኃይሎችን እንደሚያሳትፍ፣ ለዚህ ትግል ስኬት ስትራቴጂያዊ አመራር በመስጠት የተለያዩ የድርጅት ስራዎች መሰራት የጀመሩበት ወሳኝ የድል ዓመት ነበር፡፡
በ2024 ዓ.ም. የአማራ ፋኖ ፋኖ ትግል በጀግንነት፣ በተሻጋሪ የትግል ራዕይና በትግል አቃፊነት በተግባራዊ እንቅስቃሴዎቹ አስመስክሯል፡፡
በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ፡-
• የአማራ ሕዝብ መጠቃትና መገፋት ቆጭቶት የተነሳ ኃይል መሆኑን አስመስክሯል፣
• በትግሉ ውስጥ የማይተካ ሕይወቱን ገብሮ ፋኖነነት የአማራ መዳኛ መሆኑን እያስመሰከረ በድል መጓዙን ቀጥሏል፣
• ከፍተኛ የሆነ የውጊያ ተነሳሽነትና የመዋጋት ልምዱን በተጨባጭ እያሳየ ነው፣
• በአማራ ሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት በሚፈልጉ ሌሎች ብሄሰረቦች ዘንድ በተስፋ የሚጠበቅ ተቀባይነት ያለው ኃይል ሆኗል፣
• የአማራ ፋኖ ኢትዮጵያን ከፍርሰት ይታደጋል ተብሎ የሚጠበቅ፣ የሐገረ-መንግሥቱ መዳኛ ይሆናል የሚል እምነት ተጥሎበታል፡፡
ይህን ስንመለከት “መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የትግል መርህ ምን ያህል ትክክለኛ መስመር እንደሆነ ያሳያል፡፡
Amsalu Asnake (PhD)
@amsalu77