ጋዜጠኛና የታሪክ አዋቂ ታዲዎስ ታንቱ ፤ በከፍተኛ ህመም ላይ ናቸው
ጋዜጠኛ ይድነቃቸው ከበደ
ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ ታዲዎስ ታንቱ በጽኑ ህመም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ እና በካቲተር (የመሽኛ ትቦ) እየታገዙ ከፍተኛ ህመም ላይ እንደሚገኝ ከቀናቶች በፊት መረጃው ለሕዝብ ይፋ መሆኑ የሚታወቅ ነው ።
ይህን ተከትሎ ፤ በጠብቆች እና በቤተሰብ ከፍተኛ በሆነ ተደጋጋሚ ውትወታና አቤቱታ በኋላ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ ፤ በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ህክምና እንዲከታተሉ ትዕዛዝ መስጠት ችሏል ።
ይሁን እንጂ ፤ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ወደ ህክምና በመውሠድ ፋንታ ፤ ካቴተራቸውንም በማውጣት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንዲሆን በማድረግ ፣ ወደ አባሣሙኤል ማረሚያ ቤት ከቃሊቲ ክሊኒክ አውጥተው ወሥደዋቸው ነበር ።
ሆኖም ግን፤ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ ታዲዎስ ታንቱ ህመማቸው እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ ሥለፀናባቸው ወደቃሊቲ ማረሚያ መልሠው አምጥተዋቸል ። የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቁር አንበሣ ወስጄ ህክምና እንዲያገኙ አድርጊያለሁ በማለት ለፍ/ቤት ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ከእውነት የራቀ በተግባር ያልተደረገ ነው።
አሁን ላይ ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ ፤ በከፍተኛ ህመም ላይ እንደሚገኙ ፣ እንዲሁም ተገቢውና አስፈላጊውን ህክምና እናዳያገኙ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።ይህም በመሆኑ በጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ ላይ እየደረሰ ያለው በደል ሁሉም ይወቅልን በማለት ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል ።
አቶ ታዲዮስ ታንቱንም እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ?!