>

"ሰበር ዜና" ወይስ "ሰበር ሽርሙ*ና" ?

“ሰበር ዜና” ወይስ “ሰበር ሽርሙጥና” ? 

ይድረስ ለተሰበሩ “ሰበር ዜና” አብሳሪዎች

አሁን አሁን የተያዘ ፋሽን እና እንደትልቅ ዜና በአንዳንድ የዐማራ ፋኖ ትግል ባልገባቸው ወይም የተሸጡ “የዐማራ ፋኖ አመራሮች” ከአንድ ድርጅት ወጥቶ ወደ ሌላ መግባት፣ አንዱን አደረጃጀት በትኖ ፣ አፍርሶ እና አዳክሞ ሌላ ማደራጀት፣ አንዱ የሌላውን ፋኖ ማስኮብለሉን እንደ ትልቅ ጀብድ/ ድል “በሰበር ዜና” እየነገሩን ይገኛሉ።

አሁን ይህ ምኑ ነው “ሰበር ዜና “? የሚሆነው? ለማን ነው ሰበር ዜና የሚሆነው? ለዐማራ ህዝብ ወይስ ለአብይ አህመድ? 

እህት ዓለም (ወንድምዓለም) የተሰበርሸው (ከው)  አንቺ (አንተ) እንጂ የተሰበረ ዜና የለም!! 

የማንኛውም የዐማራ ህዝብ የህልውና ትግል የገባው የፋኖ አመራር ቀዳሚ ትኩረትና ግብ የሰው በላውን ስርዓት ከስሩ መንግሎ በመጣል የዐማራን ህዝብ እንደ ህዝብ የመኖር ነፃነት ማረጋገጥ መሆን አለበት! ይህን ለማሳካት የዐማራ ፋኖ የሚከተለው አደረጃጀት በምንም መመዘኛ የፋኖዎች ቀዳሚ አጀንዳ / ትኩረት ሆኖ ማነታረክ እና የነፃነት ትግሉን መጎተት የለበትም! 

እንዲህ ያሉ አስተሳሰባቸው ከአፍ እስከ አፍንጫ የሆኑ፣ የዐማራን ህዝብ የህልውና ትግል ወደፊት ከማስፈንጠር ይልቅ እርስ በርስ በመጓተትና በመነታረክ የአገዛዙን እድሜ በማስቀጠል ለሰው በላው ስርዓት ከፍሎ የማይጨርሰው ውለታ የሚውሉ፣ ስርዓቱ በመቶ ሺዎች ሰራዊት አሰማርቶ፣ በሜካናይዝድ ፣ በድሮንና በአየር ሃይል ያላገኘውን ድል፣ “በሰበር ዜና” ስም ፋኖን በማዳከም ለስርዓቱ ገፀ በረከት የሚያቀርቡ የውስጥ አርበኞች፣ የዐማራን ህዝብ መከራና ስቃይ የሚያራዝሙ ሾተላዮች ልንነቃባቸው፣ አጥብቀን ልናወግዛቸው ይገባል። 

ሲጀመር የድርጅቱ ዓላማ ሳይገባቸውና ሳያምኑበት ለምን አባል ሆኑ? አባል ከሆኑ ደግሞ ድርጅት እንደሸሚዝ እየቀያየሩ ትግሉን ከመጎተትና ህዝቡንም የፋኖ ተዋጊዎችንም ግራ ከማጋባት ይልቅ በዋናው ግብ ላይ በማተኮር ድርጅት ውስጥ ችግር እንኳን ቢኖር በሰለጠነ ውይይት እና በግምገማ ያልሰሩ አመራሮችን በማውረድ የተሻሉትን ደግሞ ወደ ፊት በማምጣት ድርጅትን ማስቀጠል ይቻላል። 

እንዲህ ያሉ ግለሰቦች አቋም የሌላቸው፣ የማይታመኑ፣ ባኮረፉና ትንሽ በጎረበጣቸው ቁጥር በቀላሉ የሚሸበሩ እና የሚሰበሩ፣ ተሰብረው ሰበር ዜና የሚያስነግሩ፣ የዐማራ ህዝብ ትግል የደረሰበት ደረጃ ያልገባቸው ወይም ሆን ብለው ቀዝቃዛ ወሃ በመቸለስ ትግሉን ለማዳከም ከአገዛዙ ተልእኮ የተቀበሉ ሾተካዮች ናቸው። አቋም በሌላቸው፣ ወላዋይ በሆኑ ሰዎች የሚመራ ትግል መዳረሻው አይታወቅም! 

ያለ አታጋይ መሪ ድርጅት፣ አቋም ያለው ጠንካራ አመራር እና ወታደራዊ ዲሲፕሊን የፈለገ ጠንካራ ቢሆን ፋኖ ከሰፈር ጎረምሳ ያለፈ ሚና አይኖረውም! ከመንደርና ጎጥ ያለፈ ራዕይ ሊኖረው አይችልም!

ድርጅት እና ጠንካራ አመራር ሲኖርህ የምትታገልበት መርህ፣ ዓላማ፣ የጠራ መነሻና መዳረሻ እንዲሁም ዲሲፕሊን ይኖርሃል! ዲሞክረሲን እና የሰለጠነ የአስተዳደር ስርዓት ትለማመዳለህ። አቅም ካለህ ትመራለህ ፣ አቅም ከሌለህ በተሻሉ ሰዎች ትመራለህ። በሂደት ትማራለህ፣ ስትበቃ ትመራለህ ፣ የተሻለ ቦታ ታገኛለህ። ስታጠፋ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ትጠየቃለህ ፣ ትቀጣለህ! ቅጣቱን ደግሞ ትቀበላለህ እንጂ የስኒ ማእበል አታስነሳም! ምክንያቱም አንተ ከዐማራ ህዝብ ትግል አትበልጥም! ሰታለማ ፣ ጀብድ ስትፈፅም ደግሞ ማበረታቻ ያስፈልግሃል፣ ትመሰገናለህ፣ ትሾማለህ ፣ ትሸለማለህ! 

አታጋይ መሪ የመታገያ ድርጅት፣ አመራር እና ዲሲፕሊን ከሌለህ እመነኝ አስር ሚሊየን ሰራዊት ቢኖርህ ጠላትህን አታሸንፍም!  እንኳን አራት ኪሎ ድረስ አራት ኪሎ ሜትር አትጓዝም! እንኳን አራት ኪሎን ባህርዳርን አታይም! 

Organization, Leadership and Decipline are the three most important pilars.

ብልህ ከሆንክ ከጠላትህም ቢሆን ጠንካራ ጎኑን አይተህ ልትማር ትችላለህ። ህወሃት 50 ዓመት የተጓዘችው መሪ ድርጅት፣ ጠንካራ አመራር እና በድርጅታዊ ዲሲፕሊን የታነፀ ተዋጊ ሃይል ስለነበራትና አሁንም ስላላት ነው! 

የዐማራ ፋኖ ትግል ማተኮር ያለበት በዋናው ጠላት በሰው በላው የአብይ አህመድ ስርዓት ላይ ነው። በየትኛውም አደረጃጀት አብይ አህመድን ማስወገድ ይቻላል። የዐማራ ህዝብ ችግር እለት እለት የመከራ ዶፍ የሚያዘንብበት የአብይ አህመድ አገዛዝ እንጂ የፋኖ ሃይሎች አብይ አህመድን ለማስወገድ የሚከተሉት አደረጃጀት አይደለም! እንደፈለክ ተደራጅ፡ አብይ አህመድና ስርዐቱን ግን ከስሩ መንግለህ ጥለህ የዐማራን ሀዝብ ነፃነት አብስር! Done!!

ከዚያ አለኝ የምትለውን አደረጃጀትም ሆነ አይዲዮሎጂ / ideology አቅርብ! ያን ጊዜ ህዝቡ የሚስማማውን፣ የሚሻለውን፣ የሚበጀውን ይመርጣል! ያልበላህን አትከክ! ለህዝቡ እኔ አውቅለታለሁ አትበል! የዐማራ ህዝብ የሚበጀውን ያውቃል፣ ይመርጣል! 

ከዋናዎቹ የዐማራ ህዝብ ጠላቶች ከሻአብያ ፣ከህወሃት ፣ ከኦነግ እና ከሌሎች ሃይሎች ጋር አብይ አህመድን ለማስወገድ እስከተቻለ እና የዐማራን ህዝብ ነፃ ለማውጣት እስከጠቀመ ድረስ tactical alliance ፈጥሬ እታገላለሁ እያልክ  ፣ አብሮህ ለዐማራ ህዝብ ሊሞት ጫካ የገባ በሌላ አደረጃጀት ውስጥ የሚታገለውን ወንድምህን ጠልፎ ለመጣል አትድከም! 

በመጠላለፍ ያሸነፈ ታጋይ፣ የሚያሸንፍ ትግል እና የሚገኝ ዘላቂ ድል የለም! ዛሬ ተሳክቶልህ ወንድምህን ትጠልፍ ይሆናል፣ ነገ ደግሞ በተራህ ትጠለፋለህ! ወደድክም ጠላህም ከወንድምህ ተለይተህ ብቻህን ስትሆን ጠብቆ ሰው በላው አብይ አህመድ ብቻህን ይበላሃል። ጠላፊም ተጠላፊም በየተራ በስርዓቱ እንደጥሬ ከመቆርጠምና ከመበላት አያመልጡም! 

ከዚህ ይልቅ ተባብሮና ተከባብሮ፣ አሉ የሚባሉ ልዩነቶችን አቻችሎ፣ ፍርዱን ለብልሁ ለዐማራ ህዝብ በመተው ትግሉ ወደፊት እንዲራመድ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው የእያንዳንዱ የዐማራ ፋኖ በዋናነት ደግሞ የእያንዳንዱ የፋኖ አመራር ግዴታ ነው! 

ወደ ጎን በመጓት ወደፊት መራመድ አይቻልም! ወደጎን መጓተት የስርዓቱን እድሜ ከማራዘምና ከማስቀጠል ፣ የዐማራን ህዝብ መከራ እና ስቃይ ከማብዛት ያለፈ ጠብ የሚል ነገር አያመጣም! 

በመጨረሻም መቸም ይቅርታ ለቃሉ የሸር*ጣ መጨረሻ ዲቃላ እና የማይድን በሽታ ስለሆነ የዐማራን ህዝብ ያለበት መከራ አነሰኝ ያለ ይመስል ሌላ ችግር እንዳታሰታቅፉት ለህዝቡና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ!

@dagmawit

(ዳ.ጌ)

Filed in: Amharic