እድለኛው እስክንድር ነጋ !
እስክንድርን በብአዴን አታማው፣ በወያኔ አታማው፣ በኦሮሙማ አታማው፣ በብልፅግና አታማው፣ በመንግስት ስልጣን አታማው፣ በግል ጥቅም አታማው ፣ በበርገር አታማው፣ በሃብት አታማው፣ በሙስና አታማው። እስክንድርን በምን ልታማው ትችላለህ? በምንም!
እስክንድር የአምሓራነት ልኬት ነው። ፈሪሃ እግዚያብሔር ያለው፣ በመርህ የሚገዛ፣ ለእውነት ሟች፣ ለሕዝቡና ለአገሩ ሕይወቱን ለመስጠት የማይሳሳ፣ ኩሩ! ሞራላዊ ክብሩን የሚጠብቅ፣ አንደበቱን የሚገዛ ፣ የአያት ቅድመ አያቶቻችን ምሳሌ የአማራነት ሞዴል ነው።
በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ይልቅ ያለፍርድ የሔደች ዶሮዬ ትቆጨኛለች ብሎ መርህ እንዳይፋለስ የጎጠኞችንና የጠባቦችን ስድብና ዛቻ ችሎ በመስመሩ ላይ ዛሬም በፅናት እንደቆመ ነው።
በዚህ ዘመን እስክንድርን መሆን በጣም ከባድ ነው። በመርህና ለእውነት በመታመን እንዲፀና ፈጣሪ በተለየ ጥበቃ አዳልቶለታል።
ለዚህ ነው እስክንድር ድል አድርጓል፤ ኃላፊነቱን ተወጥቷል የምለው። ቀሪው እዳ የእኛ እና የሕዝብ ነው። እስክንድርን የማገዝና ያለማገዝ እዳው የእኛ ነው። እስክንድር እንደ ግለሰብ ከሚጠበቅበት በላይ እርቆ ሄዶ ሰርቶ አሳይቷል። እስክንድር ከህሊና እዳ ነፃ ነው! እድለኛ ነው።
አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም። እስክንድር ሕዝብ ከድንዛዜና ከድብርት ወጥቶ በሰላማዊ መንገድ ለመብቱ እንዲታገል ፋና ወጊ ሆኖ ድርጅት መስርቶ ንቃት ፈጥሮ ታግሎ አታግሏል። በዚህ ዘመን ማድረግ አይቻል ይመስል የነበረውን የትጥቅ ትግል አስጀምሮ መንግስት ተብዬው ላይ ማስተኮስና አመፅ ማስነሳት ችሏል። ለግብ እንዲበቃ ግን የሌሎችንም ተሳትፎና ጥንካሬ ይጠይቃል። ቸርች ይመስል እያኮረፈ እየወጣ ሌላ እየከፈተ የድርጅት አለቃ መሆን የሚያምረው ብቻ ከበዛ ምንም ማድረግ አይቻልም። ህፃናት ይመስል በትንሽ በትልቁ መናጠቅና መንጫጫት ከበዛ ምንም ማድረግ አይቻልም። ጥሩ ተመሪ መሆንም የመሪነት ያህል ትልቅ ሚና አለው። የአያት ቅድመ አያቶቻችን የጥንካሬ ምስጢር እሱ ነው።
በበኩሌ አሁን እስክንድር ይሄን ቢያደርግ ብዬ የምለው ነገር የለኝም። ያለውን ሁሉንም ሰጥቷል። ምሳሌ ሆኖ እንዲኖር ስለምፈልግ ደህንነቱን ብቻ ነው የምፈልገው። ከውጤት በላይ የጥረት አድናቂ ነኝ!
@tigst