የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የቃል ኪዳን ሰነድ
- የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ምስረታ የመስራቾች ቃል ኪዳን ሰነድ /የአማራ ቃል ኪዳን/ ሰኔ 2016 ዓ.ም ነበር በተመረጡ ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ድምፅ በቃለ መሃላ ተፈርሞ የፀደቀው።
የምስረታ ቃል ኪዳን ሰነዱን /የአማራ ቃል ኪዳን/ በሙሉ ደምፅ ፈርመው ያፀደቁት ዘጠኝ ስራ አስፈፃሚዎችም ፦
1ኛ. የአማራ ፋኖ በጎጃም አቶ ዘመነ ካሤ (ተወካይ አስረስ ማረ ) እና ዝናቡ ልንገረው
2ኛ. የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ – ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ እና አቶ ምህረት ወዳጆ
3ኛ.የአማራ ፋኖ በጎንደር – አቶ ባየ ቀናው (ተወካይ በኋላ ራሱ )
4ኛ.የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ -ሻለቃ ሃብቴ ወልዴ
5ኛ. የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት -መከታው ማሞ
6.የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ሠራዊት -አቶ እስክንድር ነጋ
7.የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ – አቶ አሰግድ መኮነን ሲሆኑ አፋሕድን በሙሉ ድምፅ በፊርማቸው ሲያፀድቁ የገቡት ቃለ መሃላም :-
📌ይሕ ውሳኔ ያለ አንዳች ልዩነት በሙሉ ድምፅ የተወሰነ ቃል ኪዳን ነው፣
📌 የግልም ሆነ የውስን ቡድናዊ ንጥል ፍላጎቶችን በመተው ለተፈጠረው ውሕድ መሪ ድርጅት እና ሕዝባዊ አላማችን ተገዥ በመሆን በታማኝነትና በፅናት እንታገላለን
📌የቀደሙት መዋቅሮችም ሆነ ስያሜዎች ከዚህ ሰአት ጀምሮ ቀጣይነት የላቸውም፤ከስምምነቱ ወደኋላ ማለትም አይቻልም፤ከዚህ የተለየ ሁኔታ ከተፈጠረ መሪ ድርጅቱ ትግሉንና ድርጅታዊ ሕልውናውን ለመጠበቅ ተገቢና የማያዳግም የእርምት እርምጃ ይወስዳል፤
📌ትግላችንን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት /አሕድ/ መሪ ድርጅት ሁኖ ይመራል፤
📌ይሕንን ታሪካዊ ውሳኔ “የአማራ ቃል ኪዳን ” በሚል ሰይመነዋል ፤ ለቃል ኪዳናችንም እንታመናለን፤
📌ይሕንን ቃል ኪዳን ለገባ በአማራዊ ባህልና ወግ “ቃል አለመጠበቅ” ነውር በሃይማኖትም ሃጢያት መሆኑን በመገንዘብ በሕልውና ትግሉ ውስጥ ላፍታም ቢሆን ወደ ኋላ ላለመመልከት በመወሰን ለአላማችን መሳካት እስከ መስዋዕትነት በፅናት ለመስራት በአማራ ሕዝብና በፈጣሪ ስም ቃል እገባለሁ ፤ የሚል ነበር ።
እንዲህ ባለ ቃለ መሃላ በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ምስረታ የመስራቾች ቃል ኪዳን ሰነድ /የአማራ ቃል ኪዳን/ ሰኔ 2016 በተመረጡ ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ድምፅ ተፈርሞ የተመሰረተውን ድርጅት ነው ክሕድት የማይሰለቸው ዘመነ ካሤ የከዳው ። ድርጅቱን ብቻ ሳይሆን መላው አማራን ነው የካደው ።
ክሕደት -ሐሜትና ነውር -ጌጡ የሆነው ዘመነ ካሴ እና አንጃዎቹ መሐላ ፈፅመው የመሰረቱትን ድርጅት (የአማራን ቃል ኪዳን ) ክደው ያፈነገጡት። ዘመነ ካሤ የድርጅቱ መሪ ካልሆነ በሚል የድርጅቱን ግልጽ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ውጤት ባለመቀበል ከድርጅቱ አፈንግጠው በመውጣት በተናጥል በአፍራሽ ተግባር ላይ የተሰለፉት።
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ቃል ኪዳን ሰነድ /የአማራ ቃል ኪዳን/ በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ወደ ድርጅቱ ሊቀመንበር ምርጫ ተገበቶ ለሊቀመንበርነት ዘመነ ካሴና ታላቁ እስክንድር በእጩነት ቀርበው እስክንድር 5 ለ 4 በሆነ የድምፅ ብልጫ ነበር የተመረጠው ።
ይሔኔ ነው ዘመነ እኔ መሪ ካልሆንኩ ሙቼ እገኛለሁ በሚል ስልኩን አጥፍቶ የተደበቀው። የሚገርመው አስመራጩ ማርሸት ፀሃዩ ለእጩነት በመጀመሪያ የተጠቆመው ታላቁ እስክንድር ሁኖ እያለ በሁለተኛነት ከተጠቆመው ዘመነ ካሴ ነበር የድምፅ ቆጠራውን የጀመረው ። ያም ሁኖ ዘመነ ሊመረጥ አልቻለም። ያሰቡት አልሆን ሲል ማርሸትም ዘመነም ስልክ ዘግተው ጠፉ። በምርጫ ሲሸነፉ የአማራን ቃል ኪዳን ካዱ ።
በእርግጥ በአለም ላይ 8 ቢሊየን ህዝብ አለ እኔ በ7,999,999,999 ድምፅ ብልጫ ብበለጥም እኔ ያልኩት ካልሆነ በምንም መመዘኛ አልስማማም ከሚል ጌጃ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የማይታሰብ ነው።
ሌላው ገራሚው ነገር ዘመነ ካሤ የአማራን ቃል ኪዳን ከመክዳቱም በላይ በማግስቱ በድምፅ ምርጫ ያሸነፈውን እስክንድር በጠላትነት ፈርጆ እስክንድር ነጋ ከአብይ አሕመድ ጋር ሲነጋገር እጅ ከፈንጅ ይዘነዋል የሚል የንዴት መግለጫን አወጣ። ይኼ መግለጫም የዘመነን ፀረ አማረነት ፍንትው አድርጎ ያሳየ መግጫ ነበር። ከዚህ መግለጫ በኋላም በጎጃም ያሉ የነፃነት ታጋዮች እየታደኑ ተገደሉ፧ ተሳደዱ፤ታፈኑ። እስካሁንም ድርስ በጎጃም ሕዝባዊ ናቸው የሚባሉ የነፃነት ታጋዮች ከጀርባ እየተወጉ ነው ።
ሃቀኛ የአማራ ልጆች ግን ከዋነኛው ጠላትና ከወስጥ /የወገን ጠላት ጋር እየተፋለሙ ቃል የገቡለትንና በደም የመሰረቱትን ድርጅት ከዚህ አድርሰውታል ። በፅናታቸውና በጥበባቸው በአገር ውስጥ ሆነ ከአገር ውጭ ያለ የትግላችን ደጋፊ እውነታውን እንዲገነዘብ አድርገዋል።
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት በደም የተመሰረ ነው !!!
ከአፋሕድ ጋር ወደፊት !!!
@gasha media