>
5:42 pm - Wednesday March 21, 4604

የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ትግል ባለቤት፣ ደጋፊዎችና አጋሮች በሙሉ፤

የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ትግል ባለቤት፣ ደጋፊዎችና አጋሮች በሙሉ፤

  •                                       የአፋህድ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ   ፕሮፌሰር ጌታ አሥራደ                                                             አገር ሰሪው የአማራ ሕዝብ የሕልውና አደጋ ተጋርጦበታል።

የዚህ ታላቅ ሕዝብ ልጆች እንደመሆናችን መጠን ስለስልጣን ስለግል ዝና የምናስብበት እና የምናወራበት ጊዜው አሁን አይደለም።

ቅን መሆን ከቻልን ችግሮቻችንን ተነጋግረን መፍታት እንችላለን።

በአሁኑ ሰአት በሕይወት በመኖርና ባለመኖር መካከል ትግል ላይ ያለው የአማራ ህዝብ ተቋማዊ ትግል ይፈልጋል። ታግሎ የሚያታግል አታጋይ ድርጅት መፍጠር፣ መገንባት አስፈልጓል።

ሂደቱን ጀምረን በጥሩ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። የዘላቂ ድል አሸናፊነት ድርጅት ስለመሆኑ የዓለም ትግል ሞክሮዎች ያስተምሩናል።

በመሆኑም ሁሉንም ጫና ተቋቁመን የአማራ ፋኖ ሕዝብ ድርጅት (አፋሕድ) ተመስርቶ ዓለማቀፍ ዕውቅና ያገኘባቸውን ሁነቶች አሳክቷል። በማሳካት ላይም ነው።

አፋሕድ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ዘንድ፥ በአብሮነት በሚያምኑ እንዲሁም ከሐገረ-መንግሥቱ ጋር ግጭት የሌለባቸው የሌሎች ብሄረሰቦች የፖለቲካ ልሂቃን ጭምር ተስፋ የተጣሉበት ድርጅት ነው።

እናም

በድርጅቱ ያልተካተቱ ቁርጠኛ የአማራ ፋኖ ወንድሞቻችን ያለ ድርጅት የሚደረግ ትግል ዋጋ የለውምና ወደድርጅቱ እንዲገቡ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ለማድረግ እወዳለሁ።

እኔና የትግል ወንድሞቼ በጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን በኩል የሰጠነው ማብራሪያ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ትግላችን ሰር ነቀል ለውጥ በማምጣት ዘላቂ የሆነ ሥርዓተ መንግስት መገንባት ነው!!
youtu.be/xs0Xsmgz-Go?si…

Filed in: Amharic