>
5:42 pm - Monday March 21, 3594

አፋሕድ:- ከአብይ አህመድ ብቻ ሳይሆን ከፋኖ መሳይ "ፋኖዎች" እና ከወንድም መሳይ "ወንድሞች" ሊጠነቀቅ ይገባል!!

ጠላት ጠላት እንጂ ወዳጅ ላይሆን ራርቶ ፣

አርቆ መቅበር ነው አሽቶ እና አበራይቶ! 

ሰሞኑን በጠላት ከበባ ውስጥ ወድቀው፣ ከጠላት ጋር ከባድ ትንቅንቅ ፈፅመው፣ የህይወት ዋጋ ከፍለው፣ ወንድሞቻቸውን በጀግንነት ገብረው፣ ከበባ ሰብረው ፣ መሪያቸውን ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤን አውጥተው፣ ተዳክመው ነፃ ባወጡት ቀጠና ተዘናግተው በተቀመጡበት የዐማራ ፋኖ  ወሎ እዝ ፋኖዎች “ወገናችን”፣ “ወንድማችን”፣ ባሉት የምሬ ወዳጆ ጦር ያልጠበቁት ክህደት ተፈፅሞባቸዋል። 

ይህ እጅግ አሳፋሪ የሆነ ተግባር መፈፀሙን የሰማ ዐማራ የሆነ ሁሉ ልቡ ደምቷል። በንዴትና በቁጭት አንገቱን ደፍቷል። አጋጣሚው ግን አንድ ከባድ ምስጢር እንዲገለጥ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል። 

ይኽውም ምቹ ጊዜና አጋጣሚ የሚጠብቅ ከአብይ አህመድ የከፋ ጠላት ” ወንድም” በሚባል ጭምብል ተሸፍኖ እጉያህ ስር መኖሩን ቁልጭ አድርጎ አሳይቶሃል። ይህ ይፈጠራል ብለው ለደቂቃ ሳይጠራጠሩ ጠላታቸውን በልተው በወዳጃቸው ለተበሉ የዐማራ ፋኖ ታጋዮች ይህ ታላቅ ያልጠበቁት ዱብ እዳ ሆኖባቸዋል። 

“እግዚአብሔር ሆይ ከጠላቶቸ እጠነቀቃለሁ፣ ከወዳጆቸ ግን አንተ ጠብቀኝ” የሚል የታወቀ አባባል አለ። ከጠላት ይልቅ በወዳጅ መከዳት ያማል! 

አንድ ሊወገድ የሚገባው የዐማራው ማህበረሰብ እጅግ እየተጎዳበት ያለ የተለመደ ጉዳይ አለ። ይኸውም ጠላቱን ጨክኖ ጠላቴ ነህ ብሎ ለመጥራት የሚያሳየው ዳተኝነት በጠላቶቹ መጫወቻ እንዲሆን ፣ ለተደራጀና ለከፋ ጥቃት ዳርጎታል። 

ወያኔ ” ዐማራ ጨቋኝ ነበረ፣ የትግራይ ህዝብ ቁጥር አንድ ጠላት ነው!” ብላ ገና በጫካ ሳለች ጀመራ በማኒፌስቶ አዘጋጅታ፣ የአራት ኪሎን ቤተመንግስት ስትቆጣጠር ደግሞ ይህን አሳድጋ ” ህገመንግስት” አድርጋ “ዐማራን እና እምነቱን የኦርቶዶክስ ቤተክርሰቲያንን አከርካሪውን ለመስበር” ጠንክራ ሰርታለች። 

በመማሪያ መፃህፍት፣ በመዝሙር፣ በዘፈንና በሀውልት ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ ጠንክራ ሰርታለች። በዚህም የዐማራ ህዝብ እንደህዝብ ለዘመናት ከኖረበት ከባቢ ተፈናቅሏል፣ ተሰዷል ፣ ንብረቱ ወድሟል፣ የህይወት ዋጋ ከፍሏል።  

በአንድ ወቅት “ለትግራይ ህዝብ ከዐማራ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይቀርበዋል ” ብሏል ዶ/ር ደብረፅዮን። ይህ አቋም እንደ ድርጅት የህወሃትም አቋም ነው። 

ኦህዴድ/ኦነግና አባላቱ “ዐማራ ወራሪ ነው፣ ጡት ቆራጭ ነው፣ ከዐማራ ጋር የጋራ ታሪክ የለንም” ብለው እንደድርጅት ያምናሉ። 

እጅግ የሚገርመው ግን ይህ ሁሉ የመከራ ዶፍ ዘንቦበት የዐማራ ህዝብም ሆነ በስሙ ተደራጀን የሚሉ ድርጅቶች አንዳቸውም  ህወሃት/ኦነግ የዐማራ ህዝብ ጠላት ናቸው ብለው የገለፁበት አንድም ሰነድ እስካሁን ተፈልጎ አይገኝም። 

ከዚህ ይልቅ አስረስ ማረ “ከህወሃት ጋር ለመስራት እየተነጋገሩ” እንደሆነ በሚዲያ ገልጿል። ማርሸት ፀሃዩ ደግሞ ” ህወሃት ዳግም ብትወረን እንኳን ጥይት አንተኩስም” ብሏል። በርግጥ የብአዴን ልጆች በአያታቸው ህወሃት መጨከን ቢሳናቸው አይገርምም! 

ገዱ አንዳርጋቸው ዐማራ ጨቋኝ ነበረ። ሌሎች ብሔር ብሄረሰቦች አሁን ከዐማራ ጋር እኩል ሆነዋል። በዚህ ህገመንግስት ዐማራ ተጠቃሚ ሆኗል ብሎ ያምናል! የኢትዮዽያ ህገመንግሰት የእኩልነት መብት የተረጋገጠበት ነው ብሎ በፅኑ ያምናል! 

https://x.com/adonislo/status/1891602070756549113?s=46

በገዱ አንዳርጋቸው እና በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እንዲሁም በአብይ አህመድ መካከል የዐማራን ህዝብ በተመለከተ የአመለካከት ልዩነት ያለ መስሎ ከታየህ ዓይንህን ተመርመር!!

መቸም ክህደት አይነት አለው፤ በባዳ የሚፈፀም ክህደት እና በምታምነው ሰው የሚፈፀም ክህደት። ሁለቱም ክህደት ቢሆንም ህመሙ ግን ይለያያል። ከጠላት እጅ አምልጠህ፣ ደክሞህ እያለ፣  መድከምህን አይቶ፣ ጊዜና ቦታ ጠብቆ ፣ አስልቶ ያጠቃህ “ወንድም” በለው ” የእናት ልጅ” ብታምንም ባታምንም ከጠላት የከፋ ጠላትህ እሱ ነው! 

ወንድም ያልሆነን ሰው “ወንድም ” እያሉ የሱ ባልሆነ ስም በመጥራት እና በማሽሞንሞን የሚጠናከር ዝምድና የለም! ወንድሜ ነህ ስትለው አይ ወንድሜ አይደለህም ጠላቴ ነህ ካለህ፣ ይባስ ብሎ ጦር አዝምቶ ከወጋህ ፣ ግድ የለህም ጨክነህ በስሙ ጥራው! 

ጠላት ምንግዜም ያው ጠላት ነው! ወንድሜ ነው ብለህ አንተ ብትሸሸው ያሳድድሃል፣ ስታዝንለት ይጨክንብሃል፣ ትተኸው ወደፊት ብትራመድ ይጎትትሃል፣ ከጀርባ ይወጋሃል፣ ስታድነው ይገድልሃል፣ ስትተወው ያጠፋሃል።

ከዛ ይልቅ በስሙ ጥራው ይደነግጣል፣ ማምረርህን ያውቃል፣ በመረጠው ቋንቋ አናግረው ያከብርሃል! በመከባበር ላይ ያልተመሰረተ ወንድምነት፣ ለመናናቅ እና ለጠላትነት ብሎም ለጠላት መጠቀምያነት ይዳርጋል! 

“በቃ በል ዐማራ ትዕግስትም ልክ አለው!” እንዳለ ዳኘ ዋለ ሲበቃህ በቃ በል! ላይድን አታስታመው ፣ ትዕግሰትህን ወንድምህ ከፍርሃት ከቆጠረው፣ አዎ በቃ በል! በመረጠው ቋንቋ አነጋግረው፣ እንደባሉን ይተነፍሳል፣ ከዚያም ያከብርሃል! 

ክብር እና ነፃነት በልመና አይገኝም! ስትለምነው የፈራኸው ይመስለዋል፣ ይኮራብሃል። በሽማግሌ ብታስለምነው ያሸነፈህ ይመስለዋል፣ ይንጠራራብሃል። ግድ የለህም ትዕግስትም ልክ አለው፣ ይለይለት፣ ሰዎችም ያሉትን ይበሉ፣ ጨክነህ አስተንፍሰው! ለዘላለም ያከብርሃል! 

አለበለዚያ አትጠራጠር ከቻለ ብቻውን፣ ካልቻለ ከጠላትህ ጋር ሆኖ ያጠፋሃል። ይህንንም በተግባር አይተሃል። ለማሳያ ያክል የሚከተሉትን መራራ እውነቶች እንመልከት። 

1ኛ. ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀቤ ጦር የጠላትን ከበባ ሰብሮ ተዳክሞ ተገኝቶ “በወንድም ጦር” ተወግቷል! 

https://youtu.be/brzmDWpeM9o?feature=shared

2ኛ. የካፕቴን ማስረሻ ጦር የጎጃም እዝ “ወንድም” በሆነው በዘመነ ካሴ ጦር ከ27 ጊዜ በላይ ተወግቷል! አመራሮች ታግተዋል፣ ፋኖዎቸ ተገድለዋል፣ የጦሩ እንቅስቃሴ መረጃ ለአብይ አህመድ እንዲደርሰው እና በጠላት እንዲወጉ ተደርጓል።

https://youtu.be/7IMbxbOWm_8?feature=shared

3ኛ. ኮሎኔል ጌትነት አፈር ልሶ ከትቢያ አንስቶ ያደራጀው በጦር ወንድም” በሆነው በዘመነ ካሴ ጦር ተወግቶ እንዲበተን፣ ኮሎኔሉ የተወለደበትን ቀን እንዲጠላና እንዲሰደድ ተደርጓል! 

https://youtu.be/tm28WaIqqrE?feature=shared

4ኛ. የዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን ለማፍረስ ከአብይ አህመድ የበለጠ እንቅልፍ አጥተው እነ ዘመነ ካሴ፣ አስረስ ማረ ፣ ማርሸት ፀሀዩ ፣ ምሬ ወዳጆ፣ አበበ ፈንቴ እና መሰሎቻቸው እየሰሩ ያሉት በግልፅ ቋንቋ ድርጅቱን በጠላትነት ፈርጀው ነው!!!

ወደድክም ጠላህም በእነዚህ ግለሰቦች እና በአብይ አህመድ መካከል በዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ላይ ባላቸው አቋም ልዮነት የለም!!ሁለቱም የሚያዪበት መነፅር አንድ ነው! ይህ ማለት ብታምንም ባታምንም የአመለካከት አንድነት አለ ማለት ነው! 

5ኛ. ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው፣ ዶ/ር እንዳላማው እና ሌሎችም “በወንድሞቻቸው” እንደጠላት ተማርከው፣ ታስረው ፣ “ተፈትተው” በገዛ ሀገራቸው የማሰብ፣ የመፃፍ፣ የመናገርና በነፃነት የመደራጀት መብታቸው ተገፎ አሁንም በግዞት ይኖራሉ። 

https://youtu.be/V9juavSAt6I?feature=shared

6ኛ. አበበ ፈንቴ እሰክንድር ነጋን “በርባን”  ብሎታል።  እስክንድር ነጋ ግን አሁንም ወንድሜ ይለዋል።

እንግዲህ የጋራ ጠላት ያላቸው በዐላማ የማይገናኙ ሁለት አካላት በአንድ ላይ ቢሰሩ አይገርምም። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ሂሳብ። እንደማሳያ የዐማራ ፋኖ ጎጃም እዝ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ባሾለከው መረጃ በብረሃኑ ጁላ ጦር ጥቃት ተፈፅሞበታል! 

Therefore, even though your enemies have no objective in common, it can easily be concluded that there could be a room for tactical alliance between the two parties!!

Whether you like it or not,  now you are fighting with two enemies! ” Bro Enemies ” and “Non Bro Enemies” !
If you keep on hiding this fact, you will pay the price! On the contrary, if you face the bitter reality, you will save yourself and the Amhara Fano Struggle!

I think now things became crystal clear! The difference with the “Bro enemies” is not that simple! Now you identified your internal enemies. What is remaining is strong and equivalent strategy and clear direction on how to handle your internal enemies! 

Don’t confuse your supporters and individual Amhara Fano fighters. Be clear on your enemies! Call your enemies by their names! Because, your enemies have a clear stand! What ever you do, you are their enemy! You are entitled in bold as their number one enemy! 

በመጨረሻም ፈረንጆችም  “Don’t fear the enemy that attacks you, but the fake friend that hugs you ” የሚል አባባል አላቸው።  

የዐማራ ህዝብ የህልውና ትግል የተለያየ ፍላጎት ባላቸው፣ ከዐማራ ህዝብ ይልቅ የግል ፍላጎታቸውን ባስቀደሙ ባንዳዎች እንዳይጠለፍ የዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ከአብይ አህመድ ብቻ ሳይሆን ከፋኖ መሳይ “ፋኖዎች” እና ከወንድም መሳይ “ወንድሞች” ሊጠነቀቅ ይገባል !!

@dagmawit Getaneh

Filed in: Amharic