የብርትኳንን ጉዳይ ለማስተባበል የተሄደበት ርቀት ፣ 24 ሰዓት ባልሞላ ግዜ
1. ቪድዮው ከዩቱብ እንዲወርድ ተደረገ፡፡ የሜታ ( ፌስ ቡክ) ቪድዮውን ኮፒ ራይት ያለው ክላሲካል ነውና የተጠቀመው ፣ ይህ ቪድዮ ይታገድ ፣ይውረድ የሚል ጥያቄ ገብቶ ፣ ሜታ ቪድዮውን ማጥፋት ጀመረ
2. የኢቢኤስ ሰዎች በፖሊስ ተጠርተው እንደተዋከቡ ሰማን
3. የደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ማስተባበያ ሰጠ፡፡ ንግግሩ እርስ በርሱ የተጣረሰ ነበር፡፡ ተማሪዎች የተጠለፉ ግዜ እንኳን በዚህ ፍጥነት መግለጫ አልሰጠም ። እስካሁንም ዩንቨርስቲው የሰጠ አይመስለኝም፡፡ለዚህ ግዜ ግን ከጀት መፍጠኑ ይደንቃል (facebook.com/10000935586451……)
4. ጃዋር መሀመድ፣ ከፍርድ ቤት መግበት ቤት አስወጥቶ ፣የፍርድ ቤት የውሳኔ ደብዳቤ አስነበበን፡፡ የደምቢዶሎ ተማሪዎችን ጠለፉ ተብለው የታሰሩት በውሸት ነውና የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እዩ ብሎ ከፍርድ ቤት መዝገብ ቤት የወጣ የዳኞች ውሳኔን አስነበበን፡፡(facebook.com/photo/?fbid=10……)
5. የደምቢዶሎ ፖሊስ ጣብያ ሰውዬ፣ “አረ የታገተም ሰው የለም ሲል መግለጫ” ሰጠ፡፡ ቢያንስ ፓርላማ ላይ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበትና መንግስትም መረጃው “አለኝ “ማለቱን ማስታወስ እንኳን አልቻለም፡፡(facebook.com/belay.manaye/v……)
6. የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያና ዲጂታል መታወቅያ ተብለው ተሰሩና ፣ ያው የልደት ቀኗን እንኳን በትክክል መጻፍ ስላልቻሉ መሳቂያ ሆነ facebook.com/photo/?fbid=28……
7. ከተማረችበት ትምህርት ቤት የወጣ መረጃ ነው ተብሎ ከየ ዩንቨርስቲው የሷ ስም ያለባቸው ሰነዶች ተለጠፉ ፡፡ ብዙዎቹ የተሰረዙ የተደለዙ ስለነበሩ ውሃ ማንሳት አልቻሉም
8. እሷን ይመስላሉ የተባሉ ሴቶች በሙሉ ፎቷቸው እየታሰሰ ፣ “ይቻት እሷ ነች እኮ” ይደረቅ ሙግት ቀጠለ
9. ኦኤም ኤንና መሰል ስንትና ስንት ሚድያዎች ወዲያው የማስተባበያ ፌኩሜንታሪ ሰሩ facebook.com/photo?fbid=109……
10. የመንግስት የሚድያ ሰራዊት ቀኑን ሙሉ ሲራወጥ ዋለ (facebook.com/photo?fbid=115…… facebook.com/photo?fbid=115……
11. ቀጠለና የአዋሳ ነዋሪ ነበረች የሚል ማሳሳቻ ለመስጠት ብዙ ዶክመንቶች ወጡ፡፡ ያው ውሸት ሽባ ስለሆነ ቆሞ መሄድ አቃተው፡፡
12. 24 ሰዓት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ስንት መስሪያ ቤቶች እና ስንት ካድሬዎች እንደተራወጡ ማየቱ በራሱ ሚናግረው ነገር አለ፡፡ ግልጽ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ፣ ይሄ ዜና ከመውጣቱ ከሶስት ቀናት በፊት አሊ ዶሮ ላይ አንድ ባስ ሙሉ ተሳፋሪዎች መታገታቸውን እነ ቢቢሲ ዘግበውት ነበር፡፡bbc.com/news/articles/……? እዚህ ባስ ውስጥስ ስንት ብርትኳኖች ይኖሩ ይሆን?
እኔን ግ ራ የገባኝ ግን ማስተባበል የተፈለውገው ምንድነው? ተማሪዎች አልታገቱም ነው? ወይስ መከራ አልደረሰባቸውም ነው ? ወይስ ምንድነው? ሳስበው ግን ልጅቷ ትልቅ ሚስጥር አውጥታለች፡፡ ተማሪዎቹን ያገቱት እዛው ግቢ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ውጭ ካሉት ጋር በመቀናጀት መሆኑን እሷም መኪና ውስጥ የገባችው ፣ በዛ ምክንያት እንደሆነ ነው፡፡ ማስተባበል የተፈለገው ይሄን ይሆን? እኒ ግን የማዝነው እና የሚያሳስበኝ ሌላ ነው፡፡ ነገ፣ ነገ ነው ሚያስፈራኝ፡፡ ስልጣን ተንሸራታች ነው፡፡ ንጉሡ ይጥለኛል ባላሉት አካል ነው ስልጣናቸውን ያጡት፡፡ ኮሎኔል መንግስቱም፣ “ ወንበዴ “ እያሉ በሚንቋቸው ሽፍቶች ነው አልጋቸውን ያጡት፡፡ ህወሀትም፣ ጠፍጥፋ በሰራችው ኦህዴድና ብአዴን ነው እንደ ሸክላ ተቀጥቅጣ ፣ እንደአመድ ቡን ብላ የበነነችው፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ እጃቸው ላይ ደም አለ ያላቸውን 60 ሚኒስትሮችና ሌሎችንም ሲበሏቸው ፣ ቀናት አላቆያቸውም፡፡ ህወሀትም፣ “ ደርግ ብላ “ ያቄመችባቸውን ትንፋሽ እስኪያጥራት ተበቅላዋለች፡፡ ኦህዴድና ብአዴንም ፣ ህወሀትን በጥይት ቆልተዋታል፡፡ከደርግ በቀል፣ የህወሀት በቀል የከፋ ነበር፡፡ ከህወሀት በቀል ያሁኑ ህወሀት ላይ ታውጆ የነበረው ጦርነት እጅግ ዘግናኝ ነበር፡፡ የወደፊቱንም ሳስበው እጅግ ያስፈራኛል፡፡ እጅግ የተቆጣ ፍትሕ ፈላጊ ሕዝብ ሲንተከተክ እያየሁ ነው፡፡ የሚገርመው ግን መንግስታት አንዱ ከአንዱ አለመማራቸው ነው፡፡ ግን ወደፊት አስፈሪ ቀን ይታየኛል፡፡ ነብይ መሆን አይስፈልግም፡፡
እጃችሁ በደም ለተጨማለቀ ሁሉ፣ መጭዋ ቀን ግን የጭንቅ ቀን ናት፡፡ መፈጠርን የምታስጠላ ፡፡ ጨለማዋ እየተገፈፈች ፣ ብርሃኗ እየቀረበች ነው፡፡ የተፈጥሮ ጉዳይ ስለሆነ ክፋት መሸነፉ አይቀርም፡፡ አቤት የዛን ግዜ ግን ፣ እፈራለሁ፡፡ የሚጮህባችሁ የንጹሃን ደም ፣ የሰማይና የምድር ፍርዳችሁ፡፡
(ዘአዲሰ እነደፃፈዉ)