ይህ መራር ሃቅ ነው: ዋጠው እና ተፈወስ!
ሰሞኑን የጀነራል ተፈራ ማሞ የፓለቲካ DNA ምርመራ ውጤት ብአዴን መሆኑን ሲሰሙ ብዙ ሰዎች በድንጋጤ ደርቀው ቀርተዋል። እስከሁን ድንጋጤው ያልለቀቃቸው፣ ያላመኑ፣ አሁንም እባክህ አምላኬ በህልምህ ነው በለኝ የሚሉ አሉ።
ሆኖም ግን ይህ የምርመራ ውጤት የጀነራል ተፈራ ማሞ ብቻ ነው ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ይህ የፓለቲካ DNA አስረስ ማረ፣ ዘመነ ካሴ፣ ማርሸት ፀሃዩ፣ አበበ ፈንቴና ሌሎችም ውስጥ ይገኛል። መቸም short memory ከሌለህ በስተቀር ከጀነራሉ ቀደም ብሎ አስረስ ማረ በአንከር ሚዲያ ቀርቦ “ከህወሃት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነን” ብሎ ነግሮናል። ማርሸት ፀሃዩም “ህወሃት ዳግም ብትወረን እንኳን ከህወሃት ጋር አንዋጋም” ሲል ለህወሃት ያለውን ጥልቅ ፍቅር በይፋ ነግሮናል። የጎጃም ፋኖ ከህወሃት ጋር ንግግር መጀመሩን የሚያጋልጥ የተጠለፈ የስልክ ልውውጥ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ተዘዋውሮ ብዙ ሰው አድምጦታል። ከታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ
እጅግ የሚገርመውና ብዙ ሰው መቀበል የተቸገረው በዐማራ ጥላቻ ያበደችው፣ለመጀመሪያ ጊዜ ዐማራን እንደህዝብ በጨቋኝነት ፈርጃ ለብሔር ብሔረሰቦች ያስጠናችው የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ደራሲዋ ህወሃት ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ እንዴት ከጀነራል ተፈራ ማሞ ልብ ሳትጠፋ ቀረች? የሚለው ነው።
ላለፉት ሃምሳ በላይ አመታት ዐማራውን የጨፈጨፈች ፣ ያፈናቀለች፣ ባዶ እጁን አስቀርታ በገዛ አገሩ ላይ ለማኝና ስደተኛ ያደረገችው ህወሃት፣ ዐማራውን ርስት አልባ ማድረጓ ሳያንሳት አሁንም ራያን፣ ወልቃይትን፣ ጠገዴ ፣ ጠለምትን ሳላስመልስ እንቅልፍ በዐይኔ አይዞርም የምትል ህወሃት፣ እንዲሁም “ለትግራይ ህዝብ ከዐማራ ይልቅ የሱዳን ህዝብ ይቀርበዋል” ያለው ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ከዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (ከሻለቃ መከታው፣ ከኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃቤ፣ ከአርበኛ ደረጀ፣ ከካፕቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ከእስክድር ነጋ ፣ ከጌታ አስራደ ወዘተ. ) ይልቅ ለጀነራል ተፈራ ማሞ ከቀረቡት የፓለቲካ ሽርሙ*ናው አስከፊ ደረጃ ለመድረሱ ትልቅ ማሳያ ይሆናል ማለት ነው።
ከታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ
ብአዴናዊነት ከንሰርም በላይ ነው! የማይድን በሽታ! Somebody said “Once ብአዴን always ብአዴን!” It is really true!
ብአዴን ከዐማራ ተፈጥሮ ዐማራን ሲታገል የኖረ፣ ዐማራ መቃብር ፈንቅሎ እንዳይነሳ በህወሃት ተቀጥሮ መቃብር ሲጠብቅ የኖረ፣ ዐማራን ከጠላቶቹ ጋር ተባብሮ የገደለ፣ ያፈናቀለ፣ ያደኸየ፣ የዐማራን ወጣት በየእስር ቤቱ አጉሮ ያማቀቀና ያኮላሸ፣ ተላላኪ፣ ሾተላይ ድርጅት ነው። ካድሬዎቹም ለዐማራ ህዝብ ቅንጣት ታክል ርህራሄ የሌላቸው ከሆዳቸው ያለፈ ራዕይ የሌላቸው፣ ለራሳቸው ክብር የሌላቸው፣ ያገኘ ሁሉ የሚጭናቸው የህዳር አህዮች ናቸው።
ወደድንም ጠላንም አሁን ያለው የዐማራ ፋኖ ትግል ጥርት ያለ መልክ ይዟል። የዐማራ ህዝብ ከዋና ጠላቱ ከአብይ አህመድ በተጨማሪ ከዐማራ ተወልደው ዐማራን ከሚታገሉ የሣልሣይ ብአዴን አዋላጀች ጋር እንዲታገል ተፈርዶበታል!
ብአዴን ከሙታን መንደር መቃብር ፈንቅሎ ዳግም ሊነሳ የመጀመሪያውን የደወል ድምፅ በጀነራል ተፈራ ማሞ በኩል አሰምቶሃል። ግድ የለህም ጆሮህን እመነው! የሰማኸው ብአዴን ከሙታን መንደር ያሰማውን ድምፅ ነው!
ይህ መራር ሃቅ ነው: ዋጠው እና ተፈወስ!
@Dagmawit Getaneh