አምባገነንነት የውድቀት መጀመሪያ ነው!
አብይ አህመድ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ስርዓቱን ስለተቸ አሳደደ፣ አሰረ፣ አሁንም በእስር እያሰቃየው እያማቀቀው ይገኛል። አብይ አህመድን እና ስርዓቱን የተቹ፣ የተለየ አመለካከት ያራመዱ እንደነ መስከረም አበራ ያሉ በርካታ የዐማራ ልጆች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
የዐማራ ፋኖ በጎጃም ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን አሳደደ፣ አንገላታ፣ አሰረ፣ ” ተፈትቶ ተሾሟል” ቢባልም አሁንም እንዳይተነፍስ ተደርጎ በጥብቅ ክትትል በቁም እስር ላይ ይገኛል።
በተመሳሳይ የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን ለምን ተተቸሁ ብሎ እያሳደደው ይገኛል።
መራሩ ሃቅ በሶስቱ አምባ ገነኖች መካከል የቦታ እና የፈፃሚ እንጂ የግብር ልዩነት የለም! በሚያራምዱት ሃሳብ፣ ትችት፣ ሙግት፣ በአመለካከት ልዩነት ሰዎችን ማሳደድ፣ ማሰር፣ ማሸማቀቅ በማንም ይፈፀም ወንጀል ነው! አምባገነንነት፣ ማን አለብኝነት ህዝብንም መናቅ ነው!
የዐማራ ህዝብ እለት እለት የቁርጥ ቀን ልጆቹን እየገበረ ስርዓቱን አምርሮ እየታገለ ያለው የኦሮሞን አምባገነን በዐማራ አምባገነን፣ የጠገበውን ጅብ በተራበ ጅብ ለመተካት አይደለም!
ዐማራን ከጨቋኙ የአብይ አህመድ እስራት ነፃ አወጣለሁ የሚል የዐማራ ድርጅት መጀመሪያ የአስተሳሰብ እና የአመለካከት ልዩነቶችን በማስተናገድ ራሱን ከጠባብ አመለካከት ነፃ ያውጣ!
ለዐማራ ህዝብ ነፍሱን አሲዞ ሊሞት የወጣን ፋኖ እና ጋዜጠኛ ማሰር፣ ማሳደድ፣ ማሸማቀቅ በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም! ስለሆነም በጌጥዬ ያለው ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!
የሰብዓዊ መብት፣ የሃሳብና የአመለካከት ነፃነት መከበር ለድርድር አይቀርብም! ወደድንም ጠላንም በጫካ እያለ ይህንን የሰው ልጆች በተፈጥሮ ያገኙትን ነፃነት ማከበር ያልተለማመደ ድርጅት ዐማራን አይመጥንም። ከአብይ አህመድ እና ከህወሃት በተሻለ ዐማራን መምራት አይችልም!
አምባ ገነንነት የቁልቁለት ጉዞ፣ የውድቀት መጀመሪያ ነው። ውጤቱም ዘለዓለማዊ ኪሳራ ነው። በማንም ይፈፀም አምገነንነትን እንጠየፈዋለን! አምገነኖችን አምርረን እነታገላለን!!!
ለማስታወስ ያህል
-
ጠላቶችህን በቅጡ ሳትለይ ወደ ጦርነት ብትገባ ስትዋጋ ትኖራለህ እንጂ አታሸንፍም!!
“If you know the enemy and know yourself, you need not fear the result of a hundred battles. If you know yourself but not the enemy, for every victory gained you will also suffer a defeat. If you know neither the enemy nor yourself, you will succumb in every battle.”
Sun Tzu, The Art of War
ለማስታወስ ያህል
1ኛ. ህወሃት
2ኛ. ኦነግ/ኦህዴድ
3ኛ. ብአዴን
4ኛ. ደህዴን
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች ላለፉት ሰላሳ በላይ ዓመታት (30+ Years) ሀሰተኛ ትርክት/ Narrative ፈጥረው፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጀው፣ በጅምላ የጨፈጨፉ እና ያስጨፈጨፉ፣ ቤቱንና ንብረቱን አውድመው በገዛ ሀአገሩ ላይ ስደተኛ፣ ተሳዳጅ፣ ተንከራታች እና ለማኝ ያደረጉ፣ አሁንም እያደረጉ ያሉ የዐማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸው! አመራሮቻቸውም እጆቻቸው በዐማራ ህዝብ ደም የተጨማለወለቀ በተገኙበት ተይዘው ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ወንጀለኞች ናቸው!
አንድ በዐማራ ስም ተመስርቶ ለዐማራ እየታገልኩ ነኝ የሚል ድርጅትም ሆነ አመራር ከነዚህ የዐማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የሚያደርጋቸው ማናቸውም ንግግርም ሆነ ድርድር ታሪካዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ክህደትም ጭምር መሆኑ በግልፅ መታወቅ አለበት!!
የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል / ዐፋብኃ ሳይወለድ የሞተው ከህወሃት ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ በመገኘቱ ነው። የዐማራ ፋኖ በጎጃም ገና በማለዳው የከሰረው “ከህወሃት ጋር ለመስራት እየተነጋገርን ነው” ብሎ በአስረስ ማረ በኩል ለህወሃት ባሳየው ስስ ልብ ነው። ዘመነ ካሴም በቁሙ ፓለቲካዊ ሞት የሞተው በዐማራ ጥላቻ ላይ የተመሰረተው የህወሃት ፓለቲካ መስራች /master mind ከሆነው “ዐማራንና ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያንን አከርካሪ ሰብረናል” በሚለው ዲስኩር ከሚታወቀው ከስበሃት ነጋ፣ እንዲሁም ተከብቤአለሁ ብሎ በአንድ ቀን ብቻ 86 ዐማራዎችን ካስጨፈጨፈው ጃ-War መሃመድ ጋር በአደባባይ ሲተሻሽ በመታየቱ ነው።
የዐማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትም ድርጅታዊ ኪሳራ ውስጥ የገባው በዋናነት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ከብአዴን ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ እጅ ከፍንጅ በመያዙ ነው። ከዚህም ባሻገር የድርጅቱ የውጭ አስተባባሪ ከሚቴ በብአዴን ሰርጎ ገቦች መጠለፉ፣ እንዲሁም መረጃ ለማግኘት ሚዲያዎች ከድርጅቱ ጋር እንዲፈራረሙ የሚጠይቅ አስገዳጅ መመሪያ ከድርጅቱ መውጣቱ ድርጅቱን ከድጡ ወደማጡ እንዲገባ፣ በአጭር ጊዜ የገነባውን ተቀባይነት/credibility በአይን ጥቅሻ እንዲያጣ አስገድዶታል።
ብአዴን ነፃ ያወጣው ወይም የሚያወጣው አንድም ዐማራ የለም! ብአዴን ያስመለሰው ወይም የሚያስመልሰው የዐማራ ርስትም የለም! ብአዴን ዐማራን ለታሪካዊ ጠላቶቹ ከማንበርከክ ያለፈ ታሪክ የለውም። ብአዴን የዐማራ ታሪካዊ ርስቶችን የማስረከብ እንጂ መሬት የማስመለስ ታሪክ አልነበረውም፣ የለውም! አይኖረውም!
ብአዴን ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ዐማራን ለታሪካዊ ጠላቶቹ ያስገበረ፣ ዐማራ መቃብር ፈንቅሎ እንዳይወጣ የዐማራን መቃብር ሲጠብቅ የኖረ፣ አሁንም በዚህ ተግባሩ የቀጠለ፣ ከራስ ፀጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ከሆድ የተሰሩ፣ ጭንቅላት የሚባል ነገር ያልፈጠረባቸው፣ ከዐማራ ተፈጥረው ዐማራን የሚጠሉ ምስለኔዎች የሚመሩት ድኩም ድርጅት ነው።
ብአዴን አለቆቹን ለማስደሰት ዐማራ ቅስሙ ተሰብሮ፣ ቆዝሞ፣ አንገቱን ደፍቶ የሚያሳይ ትልቅ ሃውልት በዐማራ ክልል ዋና ከተማ ባህርዳር ላይ አስገንብቶ ያበረከተ ምስለኔነቱን በአደባባይ ያስመሰከረ የዘመናችን የአድርባይነት ጥግ ማሳያ የሆነ ርካሽ ድርጅት ነው!
አሁንም ለኦህዴድ ምርኩዝ በመሆን በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ/ Genocide ከፊት መስመር ተሰልፎ በበላይነት እያስፈፀመ ያለ በዐማራ ህዝብ ደም የተጨማለቀ ድርጅት ነው። ይህ የዐማራ ካንሰር አሁንም ለዐማራ ህዝብ የመከራ ቀን መራዘም ከጠላት ወግኖ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።
ስለሆነም ብአዴን እንደ ህወሃት፣ ኦነግ/ኦህዴድ ሁሉ አምርረን የምንታገለው፣ በወንጀል የተጨማለቀ ፣ በዐማራ ህዝብ ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ሁሉ ከህወሃት እና ኦነግ/ኦህዴድ ጋር በህግ የሚጠየቅ እንጂ የምንተባበረው፣ በአንድ ጠረዼዛ ዙሪያ ተቀምጠን የምንደራደረው ድርጅት አይደለም!!!
ይህ ያልገባው ማንኛውም በዐማራ ስም እታገላለሁ የሚል ግለሰብም ሆነ ድርጅት አሁንም እደግመዋለሁ እንኳን የዐማራን ህዝብ ራሱን አይወክልም ፣ራሱን አይመጥንም!!!
@Dagmawit Getaneh