>

አምስተኛው ረድፍ (The fifth column)

አምስተኛው ረድፍ (The fifth column)

 

በቁጥር 11 የምንሆን የቀድሞው የአፋሕድ የውጭ ሀገር አስተባባሪዎች በተከታታይ ባወጣነው መግለጫ ላይ ድርጅቱ በአምስተኛ ረድፈኞች ተጠልፏል ማለታችን ይታወሳል።

 

ለመሆኑ:- 

 

=> “አምስተኛ ረድፍ” ማለት ምን ማለት ነው…?

=> ታሪካዊ አመጣጡስ ምን ይመስላል…?

= “አምስተኛ ረድፍ” የብአዴን ሰርጎ ገቦች መለያ
ባህሪያቸው ምንድነው…?

ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን፦

አምስተኛው ረድፍ (the fifth column) የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ከ1936 እስከ 1939 በስፔን በተካሄደው የጦርነት ጊዜ ነበር።

ማድሪድ ከተማ በአራት አቅጣጫ በሚተሙ ወታደሮች ከበባ ውስጥ በወደቀችበት ጊዜ ብሔርተኛው ጄነራል ሞላ በማድሪድ ከተማ የሚኖሩ በውስጥ አርበኝነት ስለሚያገለግሉት ደጋፊዎቹ ሲናገር፣ “እኛ ማድሪድን በአራት ረድፍ እያጠቃናት ነው፤ በከተማይቱ ደግሞ አምስተኛ ረድፍ አለን” በማለት ከገለጸው የተወሰደ ነው።

ሆኖም አምስተኛ ረድፍ የሚለው ቃል በርካታ ታላላቅ ሰዎች ይዘቱን ሳይለቁ በተለያዩ አግባቦች ተጠቅመውበታል።

በ1940 ፓሪስ በናዚ ጀርመን በፍጥነት በወደቀችበት ጊዜ፣ በወቅቱ የፓሪስ ሲቪል አስተዳደር እና ወታደራዊ ክንፍ ኦፊሻሎች አንዱ ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ ተወነጃጅለዋል።

በአብዛኛው ወገን የሚታመነው ግን ለፓሪስ ውድቀት የናዚ ጀርመን ጥንካሬ ሳይሆን፣ በፓሪስ ውስጥ የነበሩ በአምስተኛ ረድፍ የተሰለፉ የናዚ ጀርመን ደጋፊዎች ናቸው።

እንዲሁም ጃፓን በፐርል ሃርበር ያደረገችውን ጥቃት ተከትሎ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ሴክሬታሪ ፍራንክ ኖክስ በሰጡት መግለጫ፣ “በጣም ውጤታማ የአምስተኛው ረድፍ የጦርነት ስራ የተሰራው በሃዋይ ነው” ነበር ያሉት።

አንድሪው ሱሊቫን ፀሃፍት እና የፖለቲካ ተንታኝ የኢራቅ ጦርነትን የተቃወሙ ግራ ዘመም ፖለቲከኞችን “አምስተኛ ረድፈኞች” ሲል በዘገባው አካቷቸው ነበር።

ሌላው በፓሪስ የደረሰውን የአሸባሪዎች ጥቃት ተከትሎ፣ የምዕራቡን ዓለም የሚያጠቁ በምዕራቡ ዓለም ውስጥ የተወለዱ፣ የተማሩ፣ ያደጉ እና የሚኖሩ አክራሪ የእምነት ኃይሎችን አምስተኛ ረድፍ ሲሉ ሰይመዋቸዋል።

እንዲሁም በጃንዋሪ 12 ቀን 2016 የቱርኩ ፕሬዝደነት ጣይብ ኤርዲጋን፣ የቱርክ ዩንቨርስቲ መምህራን በቱርክ መንግስት እና በኩርድ አማፂያን መካከል በቱርክ ምዕራብ ምስራቅ የሚደረገው ጦርነት እንዲቆም ያስተላለፉትን ጥሪ፣ የቱርክን ደህንነት ዝቅ ያደረገ የውጭ ኃይሎች የአምስተኛው ረድፍ አስፈፃሚዎች ናቸው ሲሉ ከሰዋቸዋል።

አምስተኛ ረድፈኞች በሕቡዕ ወይም በድብቅ የሚደራጁ ኃይሎች ናቸው። ከሚፈጽሟቸው ተግባሮች በማጣቀሻዎች ከሰፈሩት በከፊል የሚጠቀሱት፣ ሕዝብን በልዩ ልዩ ምክንያት በመከፋፈል ማበጣበጥ፤ የግድያ ተግባር መፈጸም፤ንብረት ማውድም፤ ለጠላት ስለላ ማድረግ፤ ጠላት ሰርጎ እንዲገባ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤የራሳቸውን ጥቅም በማስቀደም በማንኛም ዋጋ ሕዝብ በቅሬታ ውስጥ እንዲዳክር ማድረግ፤ ቅቡልነት ያላቸውን ዕሴቶች መካድ፣ ማስካድ እና ተመሳሳይ ሥራዎችን የሚፈጽሙ ናቸው።

ጠቅለል ሲል አምስተኛ ረድፈኛ (the fifth column) ማለት ፤ አንድ በሚስጥር የተደራጀ ቡድን ፣ ለጠላት በመወገን የራሱን ሕዝብ ጥቅም በማንኛውም መልኩ ከመሀል ሆኖ የሚቦረቡር ማለት ነው፡፡

እንደዚህ ዐይነቱ ጠላት ደግሞ ከለየለት የውጭ ጠላት የበለጠ አደገኛ ነው፡፡

በአፋሕድ ውስጥ ሰርገው የገቡ አምስተኛ ረድፈኞች የምንላቸው እንዲህ አይነቶቹን ነው።

የአማራ ሕዝብ በአራት አቅጣጫ ከበባ ውስጥ ገብቶ እየተወጋ ባለበት ሁኔታ አምስተኛ ረድፈኞች ከውስጥ ሆነው የገዛ ሕዝባቸውን ይወጉታል/ያስወጉታል።

አምስተኛ ረድፍ የሚለው ሀይለ ቃል የውስጥ ቦርቧሪዎችን ለመግለፅ የተመረጠ ቃል ነው።
ለጠላት በመወገን የራሱን ሕዝብ ጥቅም በማንኛውም መልኩ ከመሀል ሆኖ የሚቦረቡር ማለት ነው፡፡

አፋሕድ ውስጥ ሰርጎ የገባው የአማራ ትግል ነቀርሳው ኃይል አምስተኛ ረድፍ በሚል የምንገልፀው በዚህ ግብሩ ነው።

የኛ ምክር 

የአፋሕድ አምስተኛ ረድፈኞች የሚሰሙን ከሆነ ጥቂት ምክር ቢጤ ጣል እናድርግና ፅሁፉን እንዝጋ።

ረድፈኞች ከእናንተ ጋር የአንድ ቤተሰብ እና የአንድ ወገን ልጆች ብንሆንም በአስተሳሰብ አንገናኝም ። ጎራችን ለየቅል ነው።

የአንድ ወጥ ባህል ልምድና አካባቢ ውልዶች ብንሆንም ግባችን የተለያየ ነው ። ባንድ መልክ ያደግን ብንሆንም በተዥጎረጎረ ባህሪይ ጎልምሰናል። ለእኛ የሚጣፍጠን ፍፁም አማራዊ ነጻነት ለእናንተ ይመራችኋል ።

የአማራ ህዝብ ያለበት አስከፊ የህልውና አደጋ፣ ትግሉ ቆራጥነትን የሚጠይቅ ነው። እኛ ለህልውና ትግሉ እንኖራለን እንጅ፤ በህልውና ትግሉ አንኖርም።

ነፃነት የሚባለውን ክቡር ነገር ለማግኘት ጠላትን ብቻ ሳይሆን የወዳጅ ጠላትንም መፋለም የግድ ይላልና ትግላችን “ከአምስተኛ ረድፈኞች ” የብአዴን ሰርጎ ገቦች ጋርም መሆኑ መታወቅ አለበት።

የአማራ ህዝባዊ ትግል ማስተባበሪያ መምሪያ ማዕከል በእውቀት ላይ የተመሠረተ የህልውና ትግል ማድረጉን ይቀጥላል!

ትግሉን ላንጨርስ አልጀመርነውም!!

 

Filed in: Amharic