>

ቤት አከራዮች በትንሹ ከ100 መቶ ሺ ብር በላይ የግብር እዳ ተጠየቁ።

 

ቤት አከራዮች በትንሹ ከ100 መቶ ሺ ብር በላይ የግብር እዳ ተጠየቁ።

ኢትዮ 360

የአዲስ አበባ ከተማ ቤት አከራዮች ባለፉት አምስት አመታት የከፈሉት ግብር በቂ አይደለም በሚል በመቶሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

አስቀድሞ ይላሉ ምንጮቹ ቤታቸውን አከራይተው የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎችን አምስት አመት ወደኋላ ሄደን ኦዲት እናደርጋለን በሚል የሰው በላው ቡድን አዲስ ህግ ማውጣቱን ያስታውሳሉ።

እናም ይህንን ህግ ካወጣ በኋላም የዞት የመጣው ነገር ቢኖር ቤት አከራዮች ለአምስት አመት ይከፍሉት የነበረው የአከራይ ግብር በቂ ስላልሆነ እያንዳንዱ አከራይ በትንሹ ከ 100,000 ብር በላይ በእዳ እንዲጠየቅ ማድረጉንም ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ እስከ 300ሺና ከዛ በላይ የተጠየቁ የከተማዋ ቤት አከራዮች መኖራቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

አስገራሚው ነገር ግን ይላሉ ምንጮቹ የቤት አከራዮቹ በየአመቱ የሚከፍሉት ግብር ተመኑ ይወጣው በዚሁ ስብስብ ሆኖ ሳለ አሁን በቂ ግብር አልከፈላችሁምን ምን አመጣው ብለው ይጠይቃሉ።

ከእያንዳኑ አከራይ በየአመቱ የሚቀበሉት ግብር መጠንም እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ እንዳልሆነም ያነሳሉ።

ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ደግሞ የከተማዋ ቤት አከራዮች የተቀመጣላቸውን የግብር እዳ ሲከፍሉ ቆይተው አሁን ደግሞ ተጨማሪ አምጡ ማለት የሰው በላውን በገንዘብ እጦት መሰቃየትንና የዝርፊያ መጠኑ አይን ባወጣ መልኩ መቀጠሉን ማሳያ ነው ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።

ኢትዮ 360

(ኢትዮ 360 -ሐምሌ 9/2017)

 

 

Filed in: Amharic